| የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር የመኪና አደጋ ... |
|
| Sunday, 03 February 2008 | |
|
የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር የመኪና አደጋ ደረሰባቸው በአደጋው አንድ ሰው ሞቷል
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ዶክተር መርጊያ በቃና ባጋጠማቸው የመኪና ግጭት በህይወትና በንብረት ላይ ጉዳይ ደረሰ፡፡ የዶክተሩ ሾፌር በዋስ ተለቀዋል፡፡ ዶክተር መርጊያ የመኪና ግጭት ያጋጠማቸው ከአዲስ አበባ ወደ ደብረዘይት በሚወስደው መንገድ በአቃቂና ዱከም ከተሞች መካከል ገላን ከተማ ነው፡፡ የአይን እማኞች እንደገለፁት ገላን ከተማ አምባሳደር ልብስ ስፌት ፋብሪካ አጠገብ የመኪና አደጋው የደረሰው ጥር 22 ቀን 2000 ዓ.ም ከምሽቱ 4 ሰዓት አካባቢ እንደሆነ የገላን ፖሊስ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ ዶክተር መርጊያ የነበሩባት መኪና (ዲስከቨሪ) የተጋጨችው ከዲኤክስ መኪና ጋር ሲሆን የዲኤክስ ሾፌሩ ህይወታቸው ማለፉ ታውቋል፡፡ የገላን ፖሊስ ስለ አደጋው በዝርዝር ባይገልጽም የዲኤክሷ አሽከርካሪ ብቻቸውን እንደነበሩና ህይወታቸው እንዳለፈ ገልጿል፡፡ ዶ/ር መርጊያ ወደ ሆስፒታል እንደተወሰዱ አስታውቋል፡፡ የዶክተር መርጊያ ሾፌር ከአደጋው በኋላ በቁጥጥር ሥር ውለው አቃቂ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርበው በዋስ እንደተለቀቁ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በአሰግድ ተፈራ |
|
| Last Updated ( Sunday, 03 February 2008 ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Forums |
| Contact Us |