Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 08th
Home arrow Sections arrow መንግሥት፡-
መንግሥት፡- Print E-mail
Sunday, 03 February 2008
Imageልማታዊ ባለሃብቶችን ያበረታታ!

ቦዘኔ ባለሃብቶች እና የቢዝነስ ዋልጌነትን ይቆጣጠር!!

በተሰማሩበት መስክ፣ በገቡት ቃልና በተሰጣቸው የሥራ ፈቃድ የሚሰሩና ውጤት የሚያሳዩ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ እየተፈጠሩ ናቸው፡፡
በአንድ ወቅት ምን ይሰሩ ነበር? ምን ገንዘብ ነበራቸው? ቢባል እጅግ አነስተኛና ዝቅተኛ በመሆኑ አውቃለሁ፤ የሚል የማይገኝበት ሲሆን በሌላ ጊዜ ግን ጥረው ግረው ባለሃብት ሆነው ራሳቸውን አሳድገው አገርን የሚረዱ ባለሃብቶች መንግሥት በእጅጉ ሊያበረታታቸው ይገባል፡፡

እውቀታቸውን በየጊዜው እያሳደጉ፣ ኩባንያዎቻቸውን በየጊዜው እያጠናከሩ፣ ከሌሎች ባለሃብቶች ጋር ብቻ ሳይሆን ከውጭ አገርም ባለሃብቶች እየመጡና በሽርክናና በጋራ ሥራ እየተሰማሩ የሚንቀሳቀሱ ባለሃብቶች በተራ የሥራ ዕድል ፈጠራ መገምገሚያ ብቻ የሚደነቁ ሳይሆን የአገር ሃብት በመጨመር የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት፣ የሥራ ዕውቀት በማስፋፋት፣ የግል ኢኮኖሚ ዘርፉ እግር እንዲተከልና እንዲጠናከር በማድረግ ለአገርና ለሕዝብ አስተዋጽኦ አድርገዋል፡፡

ይህ ብቻም ሳይሆን ሥራው ዛሬ ተጀምሮ ነገ የሚቆም ሳይሆን ቀጣይነትን የሚያረጋግጥ ስለሆነ ከልጅ  ልጅ እየተላለፈም አስተማማኝ ኢኮኖሚ በመፍጠር ድርሻውን ይጫወታል፡፡

ጅማሪያዊ ማበረታቻና አይዞህ ባይነት ሳይሆን ለእንደነዚህ ዓይነቶች ልማታዊ ባለሃብቶች መሬት በቀላሉና በስፋት እንዲያገኙ፣ ገንዘባቸውን ለአስፈላጊ የሥራ መስክ እንዲያውሉት፣ ገንዘባቸውን በመሬት ሊዝ እንዳይባክን በነፃና  እንዲያገኙ፣ ፈቃድ በቀላሉና በአጭር ጊዜ እስኪሰጣቸውና ገንዘባዊ ተቋማት በተፋጠነ ቢሮክራሲያዊ አሰራርና በሚያበረታታ መልክና ይዘት እንዲደገፉ ማድረግ ይገባል፡፡

ከፍ ብለን ያወራነው ስለ ልማታዊ ባለሃብቶች ነው፡፡ ቦዘኔ ባለሃብቶችም አሉ፡፡ ስራቸው ቀጣይነት የለውም፣ ሥራቸው ሃብት አይፈጥርም፣ ሥራቸው እውቀት አያስተላልፍም፣ ሥራቸው ግብርና ቀረጥ አይከፍልም፣ ሥራቸው ትብብርና በጋራ ሥራ አያምንም፡፡ እንዲያውም ድርጅት እያፈረሱና እየፈጠሩ የውጭ ባለሃብትን እያሰሱ የሚውሉ ናቸው፡፡ ሥራቸው ከእጅ ወደ አፍ ነው፡፡ ሥራቸው ተቋም አይፈጥርም፡፡ የሌሉ ዕለት አለቀለት ቢሮአቸው ሞባይል አልያም መኪና ነው፡፡ ቢሮአችን የሚሉት ሕንፃ ቢኖራቸውም አገልግሎቱ እንደ ቢሮ አይደለም፡፡

ችግሩ ግን ይህ ብቻ አይደለም፡፡ ከፍተኛ የቢዝነስ ዋልጌነትም ያሳያሉ፡፡ እናለማለን ብለው መሬት ይወስዳሉ፤ ይሸጡታል፡፡ ሲወስዱትም ለመሸጥ ነበር፡፡ እንገነባለን ብለው ከባንክ ገንዘብ ይበደራሉ፡፡ ዓላማው ግን ለመሸጥና በሽያጩ ለመጠቀም ነው፡፡ ወይ እነሱ በተሰጣቸው መሬት አይገነቡ፤ ወይ መሬቱ ሌላ አልተጠቀመበት፡፡ በአጓጉል ይቀራል፡፡

ይህ ብቻም አይደለም፡፡ የድፍረታቸው ድፍረት መሬት ሲሻሻጡ በካርታ አይደለም፡፡ ወይ የውሸት ካርታ ነው፤ ወይ በደረሰኝ ነው፡፡ የቢዝነስ ዋልጌነት ሲባል ሌላ ትርጉም ካልተሰጠው በስተቀር ይህንና ይህን ዓይነቱ ነው፡፡

መንግሥት እንደነዚህ ዓይነቶቹን ምን ማድረግ አለበት? ጥብቅ የሆነ እርምጃ መውሰድ አለበት፡፡ ታክስ መክፈላቸውን መከታተልና መቆጣጠር አለበት፡፡ የተሰጣቸውን መሬት ካልገነቡ ሊነጥቃቸው ይገባል፡፡ ሕገወጥ መሻሻጥ ካለ ሊሰርዘው ያስፈልጋል፡፡ ማበረታቻ ያገኙት ካለ ሊሰረዝ ያስፈልጋል፡፡ የኢኮኖሚ ዕደገት የሚያረጋግጡ መንግሥታት አካሄዳቸው እንደዚሁ ነው፡፡ ልማታዊ ባለሃብቱን ያበረታታሉ፣ ቦዘኔነትና ዋልጌነትን ይቆጣጠራሉ፣ ያሳድዳሉ፣ ይቀጣሉ፡፡ ዋልጌና ቦዘኔ ሥራ ያጣ ነው ካልን ተሳስተናል፡፡ ሥራ ያጣውስ ይታዘንለታል፡፡ የባለሃብት ቦዘኔና ዋልጌ ግን አይታዘንለትም፡፡ እንዲያውም....

ይህ አስቸኳይ እርምጃ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው፡፡ በርካታ የአገር ሃብት እየባከነ ነው፡፡ ለዚሁም አዲስ አበባንና ዙሪያዋን ማየት ብቻ በቂ ማስረጃ ሊሆን ይችላል፡፡ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የተገዙ የጭነት መኪኖች በየቦታው ዝገው ሲቀመጡ ይታያሉ፡፡ መሬት ታጥሮ ሳር በቅሎበት የግንባታ መኪኖች ዝገው ይገኛሉ፡፡ ሪል ስቴት እንሰራለን፣ እንገነባለን፤ ተብሎ በትልቅ መሬት ላይ የሚዘጋ ቤት የከተማ ሽንት ቤቶች የሚመስሉ ሰርቪሶች ተሰርተው ይሸጣሉ፡፡ ሪስ ስቴት የለም፡፡

ባንክ ይውረሰውና ይሽጠው ቢባልም ዋጋ የሚያወጡ በርካታ ማሽኖች፣ መኪኖች፣ ተጀምረው ያላለቁ ግንባታዎች፣ ከአላማቸው ውጭ ታጥረው መናኸሪያ ወይም የሰፈር መፀዳጃ የሆኑ ኢንቨስትመንት ተብዬዎች በዝተዋል፡፡

በአስቸኳይ እርምጃ ይወሰድ፡፡ ልማታዊ ባለሃብትና ቦዘኔ ባለሃብት ይለይ፡፡ የልማት ቢዝነስና የቢዝነስ ዋልጌነት ለየብቻው መሆኑ ይታወቅ፡፡
 
< Prev   Next >