Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow በውጭ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ...
በውጭ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ... Print E-mail
Sunday, 03 February 2008
በውጭ የሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን የትምህርት ሚኒስቴርን ረቂቅ ተቃወሙ

በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእስልምና እምነት ተከታዮች ትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ተቋማት የአምልኮ ሥርዓትን በሚመለከት በቅርቡ ያወጣው ረቂቅ ፣በህገ መንግሥቱ የተመለከተውን የሃይማኖት ነፃነት መብት የሚጥስ፣ ከኢትዮጵያ ውጭ በሚገኙ ሙስሊሞችና በመንግሥት መካከል የሚፈጠርን አለመግባባት ከግምት ውስጥ ያላስገባ፣ ነው ሲሉ ተቃወሙት፡፡
አባላቱ ፣በድር ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ፌዴሬሽን ' በተሰኘው በዲያስፖራ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተቋም አማካኝነት ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ ሚኒስቴሩ ከማንኛውም እምነት የፀዳ (ሴኩላር የሆነ) ትምህርት ለመስጠት በሚል ያወጣው ረቂቅ መመሪያ በ1983 ዓ.ም. የተደረገው የመንግሥት ለውጥና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ድል የተረጋገጠውን የሃይማኖት እኩልነት የሚፃረር ነው፡፡

ቀደም ሲል በተረጋገጠውና ትምህርት ከሃይማኖት የፀዳ እንዲሆን በተደረገው ሕግ ሙስሊሞች እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ የትምህርት ዕድል ተጠቃሚ ለመሆን እንደበቁ ለችግር እጅ ሳይሰጡ ለሚጠበቅባቸው ኃላፊነት ራሳቸውን እያዘጋጁ ሳሉ መመሪያው መውጣቱ አግባብ አይደለም፡፡

ተቋሙ ሙስሊሙን ካወያየ በኋላ የተሰጠውን ዝርዝር መግለጫ በማውጣት መመሪያው አሁን በወጣበት መልኩ ተግባር ላይ እንዳይውልም ጠይቋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር ህዳር 2ዐዐዐ ላይ የትምህርት ተቋማት የአምልኮ ሥርዓትን በሚመለከት ያወጣውን መመሪያ የበድር ዓለም አቀፍ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ፌዴሬሽንና አጋር ማህበራት መመሪያውን የተለያዩ የትምህርት ተቋማት ያላቸውን ልዩ ባህሪያትና ይዘት ያላገናዘበ፣ የኢትዮጵያ ህገ መንግሥት ለአገሪቱ ዜጐች ያረጋገጠውንና መሠረታዊ የሆነውን የዜጐችን የሀይማኖት ነፃነት የሚክድ፣ የአገሪቱ የትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲ የሚያስቀምጣቸውን ነጥቦች አላግባብ በሆነ መልኩ የተረጐመና ስለሴኩላራዊ አገዛዝና ሴኩላራዊ ትምህርት አሰጣጥ የተሳሳተ ግንዛቤ የተከተለና በዓለም ላይ ያሉ ሌሎች የትምህርት ተቋማትን ተሞክሮ ያልተከተለ በማለት በወጡት የአቋም መግለጫ ተቃውመውታል፡፡

በቅርቡ በትምህርት ሚኒስቴር ረቅቆ ለውይይት የቀረበውና ሀይማኖታዊ ሥርዓትን ማህበረሰብ እንዳሳሰበውና ራዳር የኢትዮጵያን ሙስሊሞች ፌደሬሽንም ከአጋር ሙስሊም ማህበራት ጋር በመተባበርና ኮሚቴ በማቋቋም ጉዳዩን ካጤነ በኋላ የአቋም መግለጫውን ሊያወጣ እንደቻለ አስታውቋል፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ የአለባበስ፣ የአምልኮና የአመጋገብ እንዲሁም ትምህርት የሚሰጥበት የጊዜ ሰሌዳ በሚመለከት መመሪያው ያስቀመጣቸው ዝርዝሮች የሙስሊሙን ህብረተሰብ የሀይማኖታዊ ግዴታና ልዩ የፀሎት ባህሪ ከግምት ያላስገባ እንደሆነ መገለጫው አመልክቷል፡፡

የረቂቁ ይዘት የሙስሊሙን ተማሪና አጠቃላይ የመስሊሙን ህብረተሰብ የሐይማኖት ነፃነት የሚጋፋና ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ ነው፡፡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች በ1999 ዓ.ም. ሚያዚያ ወር የሙስሊም ተማሪዎችን ችግር በሚመለከት ከአገሪቱ  ባለሥልጣናት ጋር በመወያየት በተፈጠረው መግባባት ላይ ረቂቁ አሉታዊ ተፅእኖ ይኖረዋል፡፡

የዲያስፖራ ኢትዮጵያውያኑ መግለጫ ጨምሮ እንዳመለከተው ትምህርት ሚኒስቴር አሁን ባለው መልኩ መተግበር የለበትም፡፡ ረቂቁ ያነሳቸው አለባበስ፣ የአምልኮና የምግብ ጉዳዮችን የተመለከቱ ጉዳዮችም በግለሰቦችና በእምነት ተከታዮች እንጂ አስተዳደራዊ ሥራን ለማከናወን በተቀመጠ ተቋም መወሰን የሌለበት በመሆኑ ሊስተካከል ይገባል፡፡ በተጨማሪም ረቂቁ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በሚያግባባ መልኩ ሊስተካከል ይገባል፡፡

መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ ሊከታተለው እንደሚገባና የሃይማኖት አባቶችም በዚህ ረገድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

ረቂቁን በተመለተ የትምህርት ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት ክፍልን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >