Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow ለሙሰኞች የሚሰጠው ፍርድ አነስተኛ ነው
ለሙሰኞች የሚሰጠው ፍርድ አነስተኛ ነው E-mail
Sunday, 03 February 2008
በሪፖርተር  ጥር 18/2000 ዓ.ም. ላይ በሙስና ተጠርጥረው ተያዙ የሚል ዜና አንብቤያለሁ፡፡

ይቺ ደሃና ከ7ዐ ሚሊዮን በላይ ህዝብ የሚኖርባት አገር በግለሰቦች ተዘርፋ ማለቋ ነው፡፡ አንድ በሙስና የከበረ ግለሰብ ሦስት ዓመት ብቻ ታስሮ ይፈታል፡፡ ከእስር እንደተለቀቀም ኢንቨስተር ነኝ ይላል፡፡ ከእስር በኋላ ቀሪውን ህይወቱን አደላድሎ ይኖራል፡፡ በስሙ የሚነገድበት ህዝብ ግን በረሀብና በኋላ ቀርነት እየማቀቀ ይገኛል፡፡
በሙስና ተከሰው ፍርድ የሚሰጣቸው ሰዎች ቅጣታቸው ከጥፋታቸው አነስተኛ ነው፡፡ ይህ ህጉ ሊሆን ይችላል፡፡ ሆኖም ከአገሪቷ አለአግባብ መመዝበር አንፃር ቅጣቱ ከፍ ሊል ይገባል፡፡

(ቢኒ፣ ከጨርቆስ)

የአፍሪካ አንድነት

በረቡዕ ሪፖርተር ጋዜጣ ፖለቲካ ገጽ ላይ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት አመሰራረትን፣ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩ የአፍሪካ አገሮች ለነፃነታቸው ባደረጉት ትግል ላይ የነበረው ድጋፍ፣ ከዚያም በአፍሪካ አገሮች የውስጥ ችግርን ለመፍታት የተንቀሳቀሰባቸውን መንገዶች የሚያሳይ ፅሁፍ ተመልክቻለሁ፡፡

የአፍሪካ አንድነት ድርጅትን ከማቋቋም ጀምሮ ድርጅቱ በተለያየ መልኩ እንዲጠናከር ኢትዮጵያ በተለያየ ጊዜ ያደረገቻቸውን ጥረቶች፣ የድርጅቱን መቀመጫ አዲስ አበባ ላይ ለማድረግ በተለያየ ወቅት በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተደረጉ ትግሎችን ጽሑፍ ያብራራል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ እየተደረገ ባለበት በአሁኑ ወቅት የፅሁፉ መቅረብ መልካም ነው፡፡

(ዳናዊት፣ ከገርጂ)

ለቤተ-እስራኤላውያን ትኩረት

ባለፈው እሁድ የጋዜጣው እትም ዲያስፖራ ገፅ ኢትዮ-እስራኤላውያን ካሉበት ጭንቀት ለማውጣት እየተከናወኑ ስላሉ ተግባራት ተዘግቧል፡፡ ኢትዮ-እስራኤላውያኑ በተገቢ አያያዝ ስላለመያዛቸው በተደጋጋሚ በሚወጡ ዘገባዎች እየተስተዋለ ነው፤ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር በአንድ ወቅት ለፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት ጭምር በትምህርት ቤቶች አካባቢ በኢትዮ-እስራኤላውያን ላይ እየተደረገ ስላለው አሳፋሪ አይነት መገለል እስከመግለፅ ደርሰው ነበር፡፡

የተሻለ ኑሮ ፍለጋና ከጥንት ወገኖቻቸው ለመቀላቀል በሚል ወደ እስራኤል የሄዱት ዜጐች ለብቻቸው ተገለው እንደሚኖሩም በተደጋጋሚ ሰምተናል፡፡ በሀገሪቱ መንግሥት የተቋቋመና ባለፈው ሳምንት ዘገባችሁ የቀረቡ አይነት ተቋማት የሚያደርጉትን ጥረት ሊቀጥሉ  በአጠቃላይም የኢትዮ-እስራኤላውያን ጉዳይ ትኩረት ያሻዋል፡፡

(ኒቆዲሞስ፣ ከሠራተኛ ሠፈር)

ኬንያን ለመታደግ

በረቡዕ ዕትም በወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ የአፍሪካ ህብረት የሚኒስትሮች ልዑካን ቡድን ወደ ኬንያ እንደሚሄድ አስነብባችሁናል፡፡ “ያገሩን ሰርዶ በአገሩ በሬ” እንደሚባለው ሌሎች የውጭ አካላት በአፍሪካውያን የውስጥ ችግር ጣልቃ ከሚገቡ አፍሪካውያን ቢወያዩበት የችግሩን ብልት ለማውጣትና የመፍትሄ ሃሳብ ለማቅረብ የተሻለ ይሆናል፡፡

በዚያው ልክ በአገራችን እየተካሄደ ያለው 1ዐኛው የአፍሪካ ህብረት መደበኛ ስብሰባም የአፍሪካ መሪዎች አንድ የመፍትሄ እርምጃ ሊያመጡና የአፍሪካውያንን የውስጥ ለውስጥ ችግር ሊፈቱ ይገባቸዋል፡፡ የኬንያን ነገር ለሌሎች የአፍሪካ አገሮችም ጥሩ መማሪያ ሊሆን ይገባዋል፡፡ እኛም በምርጫ 97ቱ ሳንማር አንቀርም!

(ምስራቅ፣ ከ22 ማዞሪያ)

ለእድገት እስከሆነ ድረስ ያልተለመደን ማስለመድ ቢቻልስ

ዲሞክራሲ እናሰፍናለንና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እናካሂዳለን በሚል የአንድ አገር መንግሥት ውስጥ ምርጫን ለማስፈፀም የተቋቋመው የምርጫ ቦርድ ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በዜና አምድ ስር እንደዘገባችሁት “ተቃዋሚ ፓርቲዎች የምዝገባ ቅስቀሳ በመገናኛ ብዙሃን ማድረግ የተለመደ አሰራር አይደለም” ብሎ መናገሩ እንደአገርም እንደ ፅህፈት ቤትም አሳፋሪ ነው፡፡

አለመታደላችን ሆኖ እንጂ ሚዲያ ማለት የህዝብ ሃብት ማለት ነው፡፡ ህዝቡ ሃሳቡን የሚገልፅበትና መረጃ የሚያገኝበት በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ፓርቲዎች ሃሳባቸውን የሚያስተላልፉበትና ፍትሃዊ በሆነ መልኩ አጠቃላይ ህብረተሰቡ መረጃ የሚያገኝበት ነው፡፡ የተቃዋሚ ፓርቲዎችንም ሆነ መሪውን ፓርቲ የሚመርጠው ህዝቡ ሆኖ ሳለ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ሚዲያን ለምዝገባ ቅስቀሳ መጠቀም እንደአስገራሚ ነገር ተቆጥሮ ያልተለመደ አሰራር መባሉ ኋላ ቀርነት ነው፡፡

ምርጫ ዴሞክራሲያዊ ሂደት ነው፡፡ ለዲሞክራሲያዊ ሂደት አንዱ መሳሪያ ደግሞ ሚዲያን መንግሥትም ሆነ ተቃዋሚዎች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ መጠቀም ሲችሉ ነው፡፡ ይህንን የምርጫ ቦርዱ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሳያውቁት ቀርተው ነው ወይስ? ለሃገር እስከጠቀመ ድረስ ያልተለመደ አሠራርን እንዲጀመርና እንዲለወጥ ማድረጉስ ማንን ይጐዳል?

(ማህደር ስንታየሁ፣ ከመርካቶ)

ያልተጠናከረ አስተዳደር ሥርዓት

በሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ጥር 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የዘውዲቱን ሆስፒታል በከፊል መዘጋት የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ አያውቁትም በሚል የወጣውን ዜና አይቼዋለሁ፡፡

ለእንደዚህ ዓይነቱ የመረጃ ክፍተት መፈጠር ዋነኛ ምክንያቱ የተጠናከረ የአስተዳደር ስርዓት አለመኖሩ ነው፡፡ ጉዳዩን በተለይ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነትም የማያውቀው ከሆነ የመሥሪያ ቤቱን የአስተዳደር ድክመት አጉልቶ የሚያሳይ ይሆናል፡፡ ሚኒስትሩ ጉዳዩን አለማወቃቸው በራሱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን የህዝብ ግንኙነት ክፍል አሰራር ዝርክርክነትና የመረጃ አሰባሰብ ድክመት ያሳያል፡፡

ዛሬ የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ የሆስፒታሉን በከፊል መዘጋት አያውቁት ከነበረ በየሆስፒታሉ ከቁሳቁስም ሆነ ከሰው ኃይል አንፃር ያሉ ችግሮችን ያውቃሉ ለማለት አያስደፍርም፡፡ የአሰራር ግልፅነት እየተባለ በየቦታው የሚሰበክለት “ግልፅነትም” እንደው ለይስሙላ መሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱን ትዝብት ላይ የሚጥለው ነው፡፡

(ሩሃማ፣ ከፒያሳ)
 
< Prev   Next >