| አገር አቀፍ የሴቶች ማኅበራት... |
|
|
| Sunday, 03 February 2008 | |
|
አገር አቀፍ የሴቶች ማኅበራት አለመኖራቸው ጥቅምን አስቀርቷል
በኢትዮጵያ የተጠናከሩና ብዙሃኑን ሴቶች የሚያካትቱ አገር አቀፍ የሴት ማኅበራት አለመኖራቸው ሴቶች በሰው ኃይል ልማት በኩል በሚካሄዱ ፕሮግራሞች ተጠቃሚ እንዳይሆኑ ማድረጉ ተመለከተ፡፡ በአፍሪካ፣ በእስያና ኖርዌይ መካከል ባለሙያዎችን በማለዋወጥ የልምድና የዕውቀት ሽግግር እንዲያደርጉ ለማድረግ ታስቦ በሚካሄደውና ፣ፍሬድስኮፕሴ፣ በተሰኘው የኖርዌይ ተቋም በሚታገዘው ፕሮግራም በኢትዮጵያ 11 ያህል ድርጅቶች እየተሳተፉ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ሴቶች ማኅበር አማካኝነት በተካሄደውና ከ13 የአፍሪካ አገራት የተውጣጡ 50 የሚሆኑ የ2008 ልምድ ልውውጥ ተሳታፊዎች ለሁለት ሳምንታት ያካሄዱት ስልጠና ሲጠናቀቅ የድርጅቱ የአፍሪካ ተወካይ አቶ ፍቅሬ ኃይለመስቀል ልምድ ልውውጡ በሰው ኃይል ልማት በኩል አገራትን ለማልማት አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ሆኖም እንደ ዩጋንዳ ባሉ አገራት የተጠናከሩና ሌሎች ማኅበራትን ያቀፉ ትልልቅ የሴቶች ማህበራት በመኖራቸው በልምድ ልውውጡ የሚሳተፉ ድርጅቶች ቁጥር ከፍ ያለ መሆኑ፣ ከፕሮግራሙም የተሻለ እየተጠቀሙ እንደሆነ አቶ ፍቅሬ አመልክተዋል፡፡ በሥነ ስርዓቱ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ሙሐሙድ ድሪር በበኩላቸው ባደረጉት ንግግር ተቋሙ በአፍሪካ አገራት መካከል የባለሙያ ልውውጥ ማድረጉ የግለሰቦችንና ተቋማትን በማጠናከር በኩል ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ፕሮግራሙ በአገራት መካከል መግባባትን፣ የባህል ልውውጥን እንደሚያስፋፋ በተለይ በባህላዊ እሴቶች የዳበሩ የአፍሪካ አገራትን በማቀራረብ ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡ ከአፍሪካ አገራት የመጡትንና ለሁለት ሳምንታት በአዲስ አበባ ቆይታ ያደረጉትን ባለሙያዎች የኢፌዴሪ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ባህላዊ እሴቶችን በማጠናከር በኩል እንደሚሰራና በተለያዩ አገራት መካከል የሚካሄደውን የባህል ልውውጥ እንደሚያበረታታም ገልፀውላቸዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |