| የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ... |
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ከ93 ሚሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል አሰባሰበ በተያዘው የበጀት ዓመት ሥራ ይጀምራሉ ተብለው የአክስዮን ሽያጭ በማከናወንና መመስረታቸውን ይፋ ካደረጉት የግል ባንኮች መካከል አንዱ የሆነው የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ የተፈረመ ካፒታልና የተከፈለ 93 ሚሊዮን ብር ማሰባሰቡን አስታወቀ፡፡
በኦሮሚያ የቢዝነስ እንቅስቃሴ አለባቸው ተብለው በታመነባቸው ገጠራማ ወረዳዎች ቅርንጫፎችን በመክፈት ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቀው ይህ ባንክ እስካሁን ድረስ ከ4 ሺህ በላይ የሚሆኑ ግለሰቦችና ድርጅቶች አክሲዮን ገዝተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ባንክ ለማቋቋም በብሄራዊ ባንክ በኩል በተደረገው ህግ መሰረት ሥራ ለመጀመር ባንኩ የተከፈለ 100 ሚሊዮን ብር እንዲኖረው የሚያስገድድ በመሆኑ የኦሮሚያ ባንክ ይህንን በማሟላትና የተመረጡትን የቦርድ አባላት በማጽደቅ ወደ ሥራ የሚገባ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ ባንክ ሌላ አምራች የሚሆኑ የግል ባንኮች በአክሲዮን ሽያጭ ላይ የሚገኙ ሲሆን አክሰስ ባንክ በሚል መጠሪያ የተቋቋመው የግል ባንክ ለመቋቋም የሚያስፈልገውን መስፈርት ካሟላ በኋላ ስያሜውን እንዲቀይር በብሔራዊ ባንክ በመገደዱ አክሰስ የሚለውን ዘመን ባንክ በሚል መጠሪያ ቀይሮ ሥራው ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አክሰስ ባንክ ስያሜውን እንዲቀይር የተገደደው በናይጄሪያ ተመሣሣይ ስም ያለው ባንክ አለ በሚል ነው፡፡ አሁን በመቋቋም ላይ ያሉትን ጨምሮ ባሳለፍናቸው 12 ዓመታት ከተቋቋሙት የግል ባንኮች ጋር ሲደመር በአገሪቱ ውስጥ ያሉትን የግል ባንኮች ቁጥር አስራ ሁለት ያደርሰዋል፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |