Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ሆዳቸው ዓምላካቸው፤ ክብራቸው ነውራቸው
ሆዳቸው ዓምላካቸው፤ ክብራቸው ነውራቸው Print E-mail
Sunday, 03 February 2008
Image(የውብዳር)

ባለፈው ጽሑፌ በአንዳንድ የግል ባንኮች ውስጥ የሚታየውን ዓይን ያወጣ ምዝበራና የሥልጣን ብልግና ለንባብ እንደማበቃ ቃል መግባቴን አልዘነጋሁትም፡፡ እነዚህን ጉድ የተሰኙ ታሪኮችን ለንባብ ለማብቃት ስወስን ዓላማው ምንድነው? ብዬ ማሰቤን አላቋረጥኩም፡፡ ጉዳዩ ከተራ አሉባልታ የዘለቀ ነው፡፡ ዓላማ ሊኖር ይገባል፡፡  ዋናው ዓላማዬ የሚመለከታቸው ሁሉ እየሰሩት ያለው ነገር የማይታወቅ አለመሆኑንና የአደባባይ ምስጢር እንደሆነ እንዲገነዘቡት ነው፡፡
ብዙዎቹ የባንክ ኃላፊ..ች ከተዘፈቁበት የንቅዘት ባህር ውስጥ እንደልባቸው ሲንቦራቹ ለራሳቸው የሚሉት የማፅናኛ ቃል ያላቸው ይመስለኛል፡፡ ራሳቸውን ናአይዞህ ማንም አላወቀብህም፤ ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል ነውና፤ እስኪታወቅብህ እንደልብህ ብላ፤ ጥገብ፤ ተንደላቀቅ፤ አላግባብ ይሁን አይሁን ሳትጨነቅ ሰብስብ፤ን ብለው የሚናገሩት ይመስለኛል፡፡ አላወቁም እንጂ ጫወታቸው የሰጎን ድብብቆሽ ዓይነት ነው፡፡ ሰጎን ራሷን ከአዳኝ እደብቅ ብላ ጭንቅላቷን ብቻ አሸዋ ውስጥ ቀበረች አሉ፡፡ ሌላው ግዙፍ አካሏ ግን አውላላ ሜዳ ላይ ነው፡፡ ድንቄም ተደበቀች፡፡ እነዚህ የባንክ ኃላፊ..ችም በሥራቸው የሚገኙ ሁሉ፣ ሊነገር የሚችለውንና የማይችለውን ብልግናቸውን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ እንደሚያውቁ አለማወቃቸው አላዋቂ..ቹ እነርሱ መሆናቸውን ያሳያል፡፡

እርግጥ ነው እያወቁም ቢሆን ቀን እስኪያልፍ ብለው አይተው እንዳላየ ሆነዋል፤ የዋህ መስለዋል፤ አላዋቂ አድርገው ራሳቸውን ቆጥረዋል፤ በማያስቀው በግድ ስቀዋል፤ በማያስለቅሰው ያለውዴታ አልቅሰዋል፤ ሳይበሉ አግስተዋል፡፡ ያ ማለት ግን አንድ ቀን ግፉ የበዛ የመሰላቸው ጊዜ በራሳቸው ፈርደው መታገል አይጀምሩም ማለት አይደለም፡፡ ይልቅስ እንደሚጀምሩ አለመዘንጋት ትልቅ አዋቂነት ነው፡፡

ሌላው ዓላማዬ በቅርቡ አንድ ጎምቱ የአገራችን የፋይናንስ ባለሙያ በዚሁ ጋዜጣ  በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ እንደገለፁት ዕውነትም ስህተት ባለማወቅ ይፈፀማልና ስህተቱ ካለማወቅ የተፈፀመ ከሆነ ከወዲሁ መስተካከል ያለበት እንዲስተካከል ለማሳሰብ ነው፡፡ በነገራችን ላይ እንደ እሳቸው አገላለፅ ባለማወቅ የሚጭበረበሩት ባንኮች ብቻ አይደሉም፡፡ በወቅቱ ተበዳሪዎ..ችም ባለማወቅ እንደሚጭበረበሩ ባለሙያው ቢገልፁት ይበልጥ አባባላቸውን ሚዛናዊ ያደርጉት ነበር፡፡ ለመሆኑ እሳቸው ይህንን ዕውነት ለመግለፅ ያልፈለጉት ወደ የት ለመሸሽ ነው? ሁሌ አጭበርባሪ..ች ተበዳሪዎ..ች ብቻ ናቸው ለማለት ነው? ኸረ አያስኬድም..

    እንደ ዓላማ ብዬ የያዝኩት ሌላው ጭብጥ ናፀጉራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታልን እንዲሉ፤ ከውጭ ሲታዩ የውድቀታቸው አካሄድ እምብዛም የማይታወቅ፣ ነገር ግን አሉ ሲባሉ ወድቀው የሚገኙ ውስጣቸው ምስጥ እንደበላው እንጨት ተቦርቡረው ያለቁ ተቋማት የሄዱበት አካሄድ ከዚህ የተለየ አይደለም፡፡ ውስጥ ለውስጥ በተለያዩ ንቅዘቶች አልቀው ሲወድቁ ብቻ ነው የሚታዩት፡፡ የነገሮች በዚህ መልክ መበላሸት ወደ ጡዘት ደረጃ ደርሶ ማለቂያው አሳዛኝ ከመሆኑ በፊት መፍትሔ መሻት ጠቢብነት ይመስለኛልና ይህን ለማስታወስ ነው፡፡

ለማንኛውም እነዚህ የባንክ ኃላፊ..ች ይህ አደባባይ የወጣ ነውራቸውን ከማስተካከል ይልቅ ማንን ፈርቼ የሚለው አባዜ ከተፀናወታቸው በቅርብም ይሁን በሩቅ የመዝራትና የማጨድ ሕግ አይለወጥምና የዘሩትን ማጨዳቸው አይቀርም፡፡ ገበሬ እንክርዳድ ዘርቶ ንፁህ ስንዴ ለማጨድ ማጭዱን ስሎ አይሄድም፡፡ ያቀዋልና ምን እንደዘራ ያንኑ ለማጨድ ይወርዳል-ይህ የማይለወጥ ሕግ ነው፡፡

ለማንኛውም ወደተነሳሁበት ጉዳይ ልመለስና ዛሬ ላስነብብ የፈለግኩት በአንድ የግል ባንክ ውስጥ እየተፈፀመ የሚገኘውን ግራ የሚያጋባ አሰራር ነው፡፡

በአንድ ወቅት የተላከውን ቂቤ ምሥጢረኛው ሰው ቀድሞ እንደሚያደርገው ከትክክለኛው አድራሻ ወስዶ እንደማስረከብ፡፡ የእኛስ ሚስቶችና ልጆች አንዳንድ ቀን ይጠላባቸዋል ወይ? በሚል ይመስላል ሰብስቦ ወደ ቤቱ፡፡ እንኩዋን ለማድረግ ለማሰብ የሚያስፈራውን ድርጊት ቢፈፅምም እሱስ ከሌላው ምን እየተማረ ከረመ? የተማርኩትን አንዴ ብሞክረውስ ምን ይመጣል? ያለ ይመስላል፡፡ ብዙ ጉድ ያውቃልና የተማመነውን ተማመነ፡፡

ለርሱም ይህ አጋጣሚ የመወንጨፊያ ማማ ሆነለት፡፡ በዕድገት ሒሳብ ቀስ ተብሎ ብዙ ሳይወራ ወደሌላ ክፍል ተዛወረ፡፡ ጉዱን የሚያውቁ ወደ ውጭ ሳይሆን ወደ ውስጥ ስቀው በአግራሞት አለፉት፡፡ ነውር ለክብር ሲሆን እንዴት አያስገርም፡፡

የዚሁ ባንክ የጠቅላላ አገልግሎት ኃላፊ ታሪክ ሌላው አስገራሚና ግራ የሚያጋባ ነገር ነበር፡፡ ሰውየው በዚህ ኃላፊነት በነበረበት ወቅት በሙያውና በችሎታው ላይ ሳይሆን በኑሮውና በብልፅግናው ላይ ያሳየው እመርታ ብዙ..ዎችን ያነጋገረ ነበር፡፡ ለምን ቢሉ የባንኩ የዕቃ ግዥ የሚመለከተው እሱን ነበር፡፡ በሚሊዮን ብሮች የሚቆጠረውን ግዥ በአጋፋሪነት የሚያስተናብረው እሱው ነው፡፡ ብዙ..ዎች አቅራቢ..ዎች ለርሱ መንገራቸውን እርግጠኛ አይደለሁም እንጂ ዓይን ያወጣ የኮሚሽን ቀበኛ እንደሆነ ያወሩበታል፡፡ እርሱ ግን የተማመነውን ተማምኗልና ምንም አይመስለውም ነበር፡፡

አንድ ቀን ግን ጉድ ፈላ፡፡ ባንኩ ለቅርንጫፎቹ ሁሉ ለማከፋፈል እንዲገዛ የታቀደው ጄኔሬተር ማንነቱን አጋለጠው፡፡ በመቶ ሺ..ዎች በሚቆጠር ብር የተፈፀመው የጄኔሬተሮች ግዥ ያላሰበው ዱብ ዕዳ ጣለበት፡፡ የሚታመናቸውም ለጊዜው አላስጣሉትም፡፡ ዓይን ያወጣ ዝርፊያ ነበራ፡፡ ጀግኔው አሮጌ ጄኔሬተሮች አዲስ ቀለም ተቀብተው ሲመጡ ለመረከብ ጊዜ አልፈጀበትም፡፡ ጉዱ የፈላው ለአገልግሎት ወደሚመለከታቸው ተሰራጭተው ሲሞከሩ ብላሽ ሆነው በተገኙ ጊዜ ነው፡፡ ጫጫታው ከየቦታው ሆነ፡፡ ጫናውን በሌላ ዘዴ ማምለጥ ስላልተቻለ ጥይት ማበረጃ ሆኖ የቀረበው ይኸው የጠቅላላ አገልግሎት  ኃላፊው ሆነና አረፈው፡፡

ከሥልጣኑ ያባረሩት አስመስለው ለተወሰነ ጊዜ ሱባኤ እንዲገባ አደረጉት፡፡ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ነገሮች የተረሱ በመሰሉበት ወቅት ተገቢው ካሳ ተፈፅሞለት በክብር የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅነትን ቦታ ሰጡት፡፡ ባለውለታ ነበራ፡፡ ከአጋፋሪነቱ ባሻገር ብቻውንም አልበላ፡፡ የዚህ ግዜ ነበር አንዳንዱ ትክት ያለው፣ እኛም መስረቅ እንደምንችል እናሳያቸው እንዴ፡፡ ካልሰረቁ መሾም እኮ አልተቻለም፤ ማለት የተጀመረው፡፡ ምን  ይደረግ ቀመሩ ክብር በነውር ነዋ፡፡ ሰው ከሰው ሊደበቅና ነውረኛ መሆን ይችል ይሆናል፡፡ ነውሩን ለራሱ እንዴት ብሎ እንዲቀበል ያደርገዋል? ሕሊና ከሌለው በቀር፡፡

ባንኩ በብድር መያዣነት የያዘውን መጋዘን ባለቤቱ ዕዳውን መክፈል ስላልቻለ በደንቡ መሰረት መጋዘኑ በተደጋጋሚ ሐራጅ ቢቀርብም በተፈለገው ፍጥነት ሊሸጥ አልቻለም፡፡ ስለዚህ እስከሚሸጥ ድረስ መጋዘኑን የሚጠብቅ ዘበኛ ተቀጥሮ ቆየ፡፡ ብድሩን የሰጠው ቅርንጫፍ ጉዳዩ ነውና ይከታተላል፡፡ በመሐል የቅርንጫፉ ኃላፊ አንድ ነገር ውል ይልበታል፡፡ ደላላ ፈልጎ የሚከራይ ሰው ያፈላልጋል፡፡ ደላላው በአጭር ጊዜ ውስጥ ተከራይ ያገኝና ከባንኩ ዕውቅና ውጭ የቅርንጫፉ ኃላፊ የሱን ደሞዝ ሦስት እጥፍ በሚሆን ገንዘብ በማከራየት የአመት ይቀበላል፡፡ ደላላውም የአገልግሎቱን ይቀበላል፡፡ ዓመት በዚህ መልክ አለፈ፡፡ ኮንትራቱ ሲታደስ ደላላውም የድርሻዬን ብሎ መጣ፡፡  ውስጥ አዋቂ ነዋ፡፡ አንዴ ተከፍሎሃል ጥፋ ከፊቴ ይባላል፡፡ ደላላውም ይህንን ጉድ ለባንኩ ዋና ፅሕፈት ቤት በመንገር ያዝረጠርጠዋል፡፡

ጉድ ተሰኘ፡፡  የተለመደውም ማጣራት ተከናወነ፡፡ ጥቆማው ትክክለኛ ስለነበር ሰውየውን ገለል በማድረግ የተለመደው የማረሳሳት ሥራ ተከናውኖ በመጨረሻ በክብር ወደ ዋናው ከተማ እንዲዛወር ሁኔታዎ..ች ተመቻቹለት፡፡ እርሱ ምን አጠፋ፡፡ የባንኩ የአስተዳደር እሴት (NORM) ይህን ዓይነቱን ነውር የሚኮንን አይደለም፡፡ እንደ ተገቢ የሚቆጥር እንጂ፡፡ በዛው አንፃር በሥነ ምግባራቸው የማይነወሩትን ታማኞችን ግን ለማስተናገድ አቅሙ አይፈቅድለትም፡፡ ብልጣ ብልጥነት ትልቅ አዎ..ንታዊ መመዘኛ ነው፡፡ ምዝበራንና ዝርፊያን ማወቅ  ውድ ክህሎት ነው፤ በነርሱ ዘንድ፡፡

በባንኩ ውስጥ ጥሩ የኋላ ታሪክ አልነበረውም፡፡ በተለያየ ጊዜ በሰራቸው የሥነ ምግባር ጉድለቶች የተነሳ ብዙዎ..ች ከንፈራቸውን እስኪመጡለት ድረስ ሳይነበብ ብዙ ጊዜ በመደርደሪያ ላይ እንደቆየ መፅሐፍ ተረስቶ ከርሞ ነበር፡፡

በአንድ ወቅት  የባንኩ ትልቅ ሰው ፊት በራለት፡፡ እሱም ያቅበታል ሞገስን አነኘ፡፡ ለመነሻ አንድ ቅርንጫፍ ላይ ተመደበ - በሥራ አስኪያጂነት፡፡ ቡዙም ሳይቆይ ዕድገት በሚመስል መልኩ ወደ ሌላው ቅርንጫፍ ዞረ፡፡ ከዚያ በኋላ ያ ብዙ ጊዜ የታማበት ባሕርይ በይፋ መታየት ጀመረ፡፡ ብድር እንደጉድ ተበተነ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ ግን ምን ያህሉ በሐቀኝነትና በማያሳማ ሁኔታ ተከናወነ ቢባል ፡ መልሱ ዝም ነው - ጊዜ ባይፈታውም ያወጣዋል ፡፡ ብንለው ይበልጥ ሳይገልፀው አይቀርም፡፡ ጉዳያቸውን እሱጋ ሄደው የከወኑ ሁሉ፡፡ ምንም እንኩዋን ብድር ማግኘት ቢሳካላቸውም በርሱ ዓይን ያወጣና ዕፍረት- አልባ ጥያቄ አንድ አስገራሚ ሥም አወጡለት ፡፡ ልክ እንደ መንግሥት  የራሱን ቀረጥ መሰብሰብ ሲጀመር አቶ ቫት አሉት፡፡ የሚሰራው ሥራ የሚያሳፍርና ነውር መሆኑ አልሰማው አለ፡፡ ከዋናው መሥሪያ ቤት ለሚመጡ ትላልቅ ሰ..ዎች የማይነገር አቅርቦት ሁሉ በማቅረብ አማላጅነቱን ተያያዘው፡፡ በነውር ውስጥ እንዳለ ቢታወቀውም እሱ ምኑ ሞኝ ነው በሌላ በኩል የብረት ግድግዳ መገንባቱን አላቋረጠም፡፡

አስቀድሞ የርሱን ቫት ለመክፈል የተስማማና ምሬት ያደረበት አንድ ተበዳሪ በሁለተኛ ዙር ከሚለቀቀው ብድር እንደሚከፍለው አግባብቶ የመጀመሪያውን ይወስዳል፡፡  ዕፍረት የማያውቀው ሥራ አስኪያጅ ቫቴን ካልሰጠኸኝ ሁለተኛውን አልለቅም ይላል፡፡ ተበዳሪው የጀመረው የኮንስትራክሽን ሥራ ይቆምበታል፡፡  በዚህ መሐል ሁለቱም በአንድ ግብዣ ላይ ይገናኛሉ፡፡ እንደተገናኙ የመረረው ተበዳሪ ጉዳዩን እንዲፈፀምለት በወዳጅነት ለማግባበት ይሞክራል፡፡ ያኛው ግን አልፎ ተርፎ ከዕድሜው ጭምር የማይጠበቅ ፀያፍ
ዘለፋን ይሰነዝራል፡፡ የመረረው ተበዳሪ አሁን ከሚችለው በላይ ሆነበት፡፡

ያንን መሬት የጠበበው ክቡር እምክቡራን የባንክ ባለሥልጣን ፣እንደ ሕፃን ልጅ ወድዶ እስኪጠላ ደበደበው፡፡ አሳዛኝ መጨረሻ፡፡ አሳፋሪ መደምደሚያ፡፡ አስነዋሪ ክስተት፡፡
ተበዳሪው የተማረረው በግለሰቡ ብቻ ሳይሆን ግለሰቡን እዚያ ሥፍራ ወስዶ የተከለውና ሳያውቅም ሆነ አውቆ በርታ ያለውን ባንኩን ነበረ፡፡ ተበዳሪው በወቅቱ የደበደበው ሰውየውን ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ጡጫ ያረፈው በባንኩ ሥምና ክብር ላይ ነበር፡፡ የእከሌ ባንክ ሥራ አስኪያጅ ተደበደበ፡፡ ለምን ቢባል፡፡ ለወሬም አያመች፡፡ እንደተለመደው ጉድ ተባለ፡፡ ከፍተኛ ሹማምንት እዚያው ድረስ በመሔድ የማረጋገት ሥራ ሰሩ፡፡ ቢሆንም በባንኩ ላይ የተተፋውን ምራቅ ሊጠርጉ አልቻሉም፡፡ ሰውየውን ገለል አደረጉት፡፡ ያች የተለመደች ብልጠት ተጀመረች፡፡

ጥቂት ሰንበት እንዳለ በተበዳሪ..ዎች መካከል ትዕዛዝ መሰል ቅስቀሳ ተካሄደ፡፡ ከርሱ በፊት እንደተደረገላቸው ሁሉ እሱንም በክብር እንዲሸኙት ታዘዙ፡፡ የእንጀራ ጉዳይ ነው ፡፡ ዛሬን አሌ ቢሉ ነገን የት ይገባሉ ? ገንዘባቸውን አዋጥተው፡፡ ሞቅ ያለ ድግስ ደግሰው፡፡ ለሽኝት ጠሩት፡፡ ተበላ ተጠጣ፣ መኪናም ተሸለመ ፣ያምቡሌም ተጨፈረ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ባንኩም በበኩሉ ወደ ዋናው ከተማ አዙሮ በክብር መደበው፡፡ ለመሆኑ እናንተዬ ይኼ ነገር  ግራ አያጋባም ትላላችሁ? በዚህ ባንክ ውስጥ ነገ አንዱ በተመሳሳይ ቦታ የሚገኝ ኃላፊ ቢወሰልት፣ ቢቀጥፍና ቢዘርፍ ትክክል አይደለህም የሚለው ይኖራል? ኃላፊዎ..ቹስ ይህንን ክስተት ለማረም የሞራል ብቃቱስ አላቸው ቢባል ማን ያምናል? ክብር በነውር፤ ሹመት በቅሌት፤ የሚገኝ ከሆነ ማን ከነውር ውጭ ለመስራት ጥረት ያደርጋል? መልሱን የሚመለከታቸው ቢመልሱና ብናውቀው መልካም ነበር፡፡

በአንድ ወቅት በባንኩ ውስጥ ከምድር ተነስቶ ግማሽ ሚሊዮን ብር ተዘረፈ ተባለ፡፡ የሃገር ውስጥ ሃዋላ ከአንድ ማዕከላዊ ሥፍራ በሚሰራጭ የተጭበረበረ  ትኬት ከተለያዩ የአዲስ አበባ ከሚገኙት ቅርንጫፎች ገንዘብ ተመዘበረ፡፡ ላይ ታች ተባለ፡፡  ቀበኛው ግን አልተገኘም፡፡ ለአንድ ባንክ ግማሽ ሚሊዮን ብር ምን ላይሆን ይችላል፡፡  ዕውነቱ ግን ገንዘቡ የህዝብ ገንዘብ መሆኑ ነው፡፡ አንዲት ሳንቲምም ብትሆን በንዝህላልነት ከጠፋች ተጠያቂ መኖር ነበረበት፡፡ በዚያ ባንክ ውስጥ ይህንን ዕውነት ከቁም ነገር የሚቆጥር አልነበረም፡፡ በወቅቱ የሚመለከተው ኃላፊ በብቃት ማነሱና በቸልተኝነቱ ተሳብቦ እንደተለመደው ገለል እንዲል ተደረገ፡፡ ብዙም አልቆየም፡፡ ያ የጠፋው ገንዘብ ለእርሱ ወደ ትልቅ ሹመት የሚፈናጠርበት መወንጨፊያ ማማ (Spring board) ሆነለት፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ያልተጠበቀ ሹመት፡፡ ጉድ ነው ተባለ፡፡ ይህ እንዴት ሆነ ሲባል ደግሞ  ናደም ከውሃ ይወፍራልን ተባለ፡፡ ወይ ከደህና ተወለድ ወይ ከደህና ተጠጋ ጊዜ ያለፈበት አባባል ቢመስልም፤ እዛ ግን ገና እንደ አዲስ የሚሰራበት ነው፡፡ በነገራችን ላይ ይህን የደም ውፍረት ይሉት ነገር በሌላ ፅ..ፌ ላይ በስፋት እመለስበታለሁ፡፡

ይህንስ እንግዲህ ምን ትሉታላችሁ? ክብር በነውር አግባብ ነው? ሹመት በቅሌት ትክክል ነው? ለመሆኑ ይህ አሰራር ሰራተኛውን ለማትጋትና ለማበረታታት (Motivate) ለማድረግ ዓይነተኛ ዘዴ ተደርጎ ተወስዶ ይሆን? ቢገርመኝ ነው መጠየቄ፡፡ መንግሥትስ በተለይ የፌዴራሉ ሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ስለዚህ ምን የሚለው ነገር አለ? ወይስ ክልሌ አይደለምና አያገባኝም ብሎ ማለፍ አለበት? አይመስለኝም፡፡ መነሻ ራዕዩ በአገሪቱ ውስጥ ግልፅ አሰራር (Transparency) መልካም አስተዳደር (Good Governance) ከሙስና የፀዳ አካሄድ እንዲሰፍን የበኩሉን መወጣት ነውና ዝም እንደማይል ዕምነቴ ነው፡፡ ለዛሬው በዚህ አበቃሁ፡፡ በሚቀጥለው በተለይ የባንክ ኃላፊ..ች የጥቅም ግጭቶችን (Conflict of Interest) ፈተና እንዴት እየወደቁ እንዳሉ ለማሳየት ያዘጋጀሁትን ማቅረቤን እቀጥላለሁ፡፡
 
< Prev   Next >