Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow ኮሚሽኑ ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ
ኮሚሽኑ ሁለት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አዋለ Print E-mail
Sunday, 03 February 2008
የፌዴራል የስነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ከህገወጥ የመሬት ይዞታ ጉዳይ ጋር በተያያዘ፣ በምርመራ ላይ ያለ ማህበር ምርመራውን የማቋረጥ ነፃ እናደርጋችኋለን በማለት መጠኑ ያልታወቀ ገንዘብ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የያዛቸውን አንድ የኮሚሽኑን ሠራተኛና የፌዴራል ፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡ በኮሚሽኑ የስነ ምግባር ትምህርትና ህዝብ ግንኙነት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አለፈ በቁጥጥር ስር የዋለው የኮሚሽኑ ሠራተኛ ቀደም ሲል ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል፣ ተጠርጣሪዎችን አጅቦ ወደ ፍርድ ቤት የማቅረብና ከምርመራ ጋር በተያያዘ ድጋፍ በማድረግ ያገለግል የነበረ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህገወጥ መንገድ ተደራጅተዋል በሚል በምርመራ ላይ ከሚገኝ አንድ የማህበር አመራር ላይ 4ዐዐ ሺ ብር ጠይቀው ጥር 15 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ግሎባል ሆቴል አካባቢ ለጊዜው መጠኑ ያልታወቀ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው ነው፡፡

(አዲስ ልሳን፣ ጥር 21 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም.)

በአማራጭ የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ ጥናት ሊካሄድ ነው

ከሰሜን ምስራቅ ሸዋ እስከ ደቡብ ወሎ ባለው አካባቢ በሚገኙት አማራጭ የጎብኚዎች መዳረሻዎች ላይ ጥናት ሊያካሂድ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚሌኒየም በዓል አከባበር ብሔራዊ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የፅህፈት ቤቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ነፃነት አስፋው በኢትዮጵያ በሁሉም አቅጣጫዎች ታዋቂና የጎብኚዎች መስህብ የሆኑ ስፍራዎች እንደሚገኙ ጠቁመው ጥናቱም የተለያዩ የመስህቦችን መስመር ለማስፋትና ለማሳደግ እንደሚያግዝ ገልፀዋል፡፡

(ኢዜአ)

በካሚላት መህዲን ላይ የግድያ ሙከራ በፈፀሙ ተከሳሾች ላይ ውሳኔ ተሰጠ

በወይዘሪት ካሚላት መህዲን ላይ በሰልፈሪክ አሲድ አደገኛ የግድያ ሙከራ በፈፀሙ ሁለት ተከሳሾች ላይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሞትና የ2ዐ ዓመት ፅኑ እስራት መወሰኑን የፌዴራል ከፍተኛ አቃቤ ህግ ገለፀ፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ዓቃቤ ህግ የአዲስ አበባ ምድብ ችሎት ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሃንስ አበበ ሰሞኑን እንደገለፁት፤ በወይዘሪት ካሚላት መህዲን ላይ የግድያ ሙከራ ባደረጉት ተከሳሾች፤ አንደኛ ተከሳሽ ደምሰው ዘሪሁን የማነ ላይ ፍርድ ቤቱ ያለፈው ረቡዕ በዋለው ችሎት የሞት ፍርድ ወስኖበታል፡፡ በሁለተኛ ተከሳሽ ያዕቆብ ኃይሌ ኪዳኔ ላይ የ2ዐ ዓመት ፅኑ እስራት እንደወሰነበት አቶ ዮሐንስ ገልፀዋል፡፡

(ዋኢማ)

ከማዕድን ሽያጭ ከ45 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ

ባለፉት ስድስት ወራት ተመርተው ከተሸጡ ልዩ ልዩ ማዕድናት ከ45 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ ሰሞኑን የመሥሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለተፈጥሮ ሀብትና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት፤ ባለፉት ስድስት ወራት ከወርቅ፣ ከጌጣጌጥና ከከበሩ ማዕድናት ገቢው መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡

(ኢዜአ)
 
< Prev   Next >