| በሽር ማኸታል ወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀረበ |
|
|
| Wednesday, 06 February 2008 | |
|
የቀድሞ ካናዳ ቶሮንቶ ነዋሪ በሽር ማኸታል ያለፈው አርብ በአዲስ አበባ የወታደራዊ ፍርድ ቤት መቅረቡን ስታር ዘገበ፡፡
በዘገባው መሠረት፣ ካናዳዊው በሽር ማኸታል ከአንድ ዓመት በላይ ጊዜ እስር ቤት ቆይቷል፡፡ በሽር የካናዳ መንግሥት ተጠሪዎች በሌሉበት ለፍርድ ቤቱ ቃሉን ከመስጠት መቆጠቡን የበሽርን የቅርብ ወዳጅ በመጥቀስ ጋዜጣው ዘግቧል፡፡ በዚሁም ምክንያት በሽር ወደ እስር ቤት መላኩን የበሽር የአጐቱ ልጅ ሰይድ ማኸታል ከሀሚልቶን ገልጿል፡፡ በሽር እ.ኤ.አ በ2ዐዐ6 በሶማሊያ የተከሰተውን የእርስ በርስ ግጭት በመሸሽ ወደ ኬንያ ለመግባት ሙከራ ሲያደርግ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡ ከዚያም በኋላ ወደ ሶማሊያ ተመልሶ በኢትዮጵያ መንግሥት ወደ ኢትዮጵያ እስር ቤት እንዲገባ ተደርጓል፡፡ ማኸታል የኦጋዴን አካባቢ ለማስገንጠል ከሚንቀሳቀሰው ቡድን ጋር ግንኙነት እንዳለው ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር መዋሉ ቢገልጽም ይህንን ውንጀላ በተመለከተ የበሽር የቅርብ ዘመዶቹ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌለ አስታውቀዋል፡፡ ሰይድ ማኸታል ኢትዮጵያ ከሚገኙ ዘመዶቹ ጋር ባደረገው የቴሌፎን ግንኙነት የበሽር ወቅታዊ ሁኔታ ለማወቅ መቻሉን ገልጿል፡፡ በሰይድ ገለፃ መሠረት በሽር አዲስ አበባ ለሚገኙ ዘመዶቹ በድብቅ መረጃ መላኩ ታውቋል፡፡ ሰይድ ማኸታል የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለሥልጣናት በበሽር ሁኔታ መደነቃቸውን ገልጿል፡፡ በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ጉዳዩን አስመልክተው ከኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረዋል፡፡ ሰይድ ማኸታል የካናዳ ባለሥልጣናት ምርመራው ከተጠናቀቀ በኋላ ከበሽር ጋር መገናኘት እንደሚችሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት መግለፃቸውን አስታውቋል፡፡ የካናዳ የውጭ ጉዳይና የዓለም አቀፍ ንግድ ድርጅት ቃል አቀባይ የሰይድ ማኸተልን አቤቱታ በተመለከተ ምንም ዓይነት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡ ቃል አቀባዩ የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተጠሪ ሄለና ጉርጊስ የኢትዮጵያ መንግሥት ለበሽር መኸተል አስፈላጊውን የቆንስላ አገልግሎት እንዲሰጠው ጥሪ ማቅረባቸውን አስታውቀዋል፡፡ የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰብአዊ መብት እንዲያከብር ለተጠርጣሪው የቆንስላ አገልግሎት ፍቃድ እንዲሰጥ ጫና የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም፣ "በሽር በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሆነ አረጋግጠናል" ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ በጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |