Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow የኬንያ መንግስት የራማፎሳን አደራዳሪነት ተቃወመ
የኬንያ መንግስት የራማፎሳን አደራዳሪነት ተቃወመ Print E-mail
Wednesday, 06 February 2008
የኬንያ መንግስት ደቡብ አፍሪካዊው ኪሪል ራማፎሳ በአደራዳሪነት እንዳይሳተፉ ማገዱን የአሶሽየትድ ፕሬስ ዘገባ አመለከተ፡፡
የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን የኬንያ መንግስት የራምፎሳን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ከሆኑት ራይላ ኦዲንጋ ጋር የንግድ ግንኙነት እንዳላቸው በመጥቀስ በአደራዳሪነት እንዳይሳተፉ ጠይቋል፡፡

ኪሪስ ራምፎሳ በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ስርዓት በሰላም እንዲያከትም ካደረጉ ሰዎች መሃከል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ኪራስ ራምፎስ በኬንያ የሚያደርጉትን የአደረዳሪነት ሚና ማቆማቸውን ገልፀዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በኬንያ የምርጫ ግጭት የሟቾች ቁጥር ከአንድ ሺ በላይ መሆኑንና የተፈናቃዮች ቁጥር ከሦስት መቶ ሺ በላይ መሆኑን የኬንያ ቀይ መስቀል ድርጅት አስታወቀ፡፡

በሩዋንዳ በተከሰተ የመሬት ርደት ከ40 በላይ ሰዎች ሞቱ

ያለፈው እሁድ በሩዋንዳ በተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የሟቾች ቁጥር ከአርባ በላይ መሆኑን የአገሪቱን ፖሊስ በመጥቀስ ቢቢሲ ዘገበ፡፡

የመሬት ርደት አደጋው ሩዋንዳን ጨምሮ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎንና ቡሩንዲን ማጥቃቱን ተዘግቧል፡፡ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ስድስት ሰዎች በአደጋው ሲሞቱ፤ በቡሩንዲ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ መስመር ላይ ችግር ተከስቷል፡፡ የመሬት ርደት አደጋ በ፣ግሬት ሌክ፣ አገራት አካባቢ በተደጋጋሚ ተከስቷል፡፡ በአካባቢው ያለፈው የፈረንጆች ዓመት በተከሰተ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች መሞታቸው ይታወሳል፡፡

ቡሽ በአፍሪካ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆርጅ ቡሽ በአፍሪካ የአምስት ቀን ጉብኝት እንደሚያደርጉ የአሜሪካ ኤምባሲ ሳምንታዊ ሪፖርት አስታወቀ፡፡

በኤምባሲው ሪፖርት መሠረት ፕሬዚዳንት ቡሽ ከየካቲት 7 እስከ 12 ድረስ በአፍሪካ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በቤኒን፣ በታንዛኒያ፣ በሩዋንዳ፣ በጋናና በላይቤሪያ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ፕሬዚዳንት ቡሽ በጉብኝታቸው ወቅት ከአገራቱ መሪዎች ጋር በሚያደርጉት ውይይት አሜሪካ ከአፍሪካ አገራት ጋር ያላትን የግንኙነት ሁኔታ ይነጋገራሉ፡፡ በዚህም አሜሪካ ለአፍሪካ አገራት የምታደርገውን የኢኮኖሚ ዕርዳታ፣ እንዲሁም ኤች.አይ.ቪ/ኤድስና የወባ በሽታን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ የምታደርገውን  በተመለከተ ውይይት ይካሄዳል፡፡

የሩሲያ መርከብ በሶማሊያ ታገተች

በሶማሊያ ወደብ አካባቢ የሩሲያ መርከብ በባህር ላይ ዘራፊዎች መታገቷን ቢቢሲ ዘገበ፡፡

በዘገባው መሠረት ስድስት የመርከቧ ሠራተኞች በዘራፊዎቹ ታግተዋል፡፡ መርከቧ ከሩሲያ ፒተርስበርግ ወደ ስካሀሊን ደሴት እየተጓዘች እንደነበር ታውቋል፡፡ የአለም አቀፍ የባህር ትራንስፖርት ቢሮ የሶማሊያ የባህር መስመር የአደጋ ቀጠና እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በቅርቡ የአካባቢው የባህር ዘራፊዎች የጃፓንን መርከብ በማገታቸው ከሜሪካ የባህር ኃይል ጋር ግጭት መፍጠራቸው ይታወሳል፡፡
 
< Prev   Next >