| ኮሚሽኑ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ... |
|
|
| Wednesday, 06 February 2008 | |
|
ኮሚሽኑ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያለው የከተማ ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ አሳገደ
የፌደራል ሥነ ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን በአዲስ አበባ አስተዳደር ይታይ በነበረው ህገ ወጥ የመሬት አያያዝና አሰጣጥ ችግሮች ዙሪያ ባደረገው ክትትል ግምቱ ከሦስት ቢሊዮን ብር በላይ የሊዝ ዋጋ ያለው የከተማ ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲታገድ ማድረጉን አስታወቀ፡፡ እርምጃዎቹም በመሬት አስተዳደር፣ አያያዝና አሰጣጥ የነበረውን የአሠራር ችግር ለማስወገድ የአሰራር ስርዓት ጥናት በማካሄድ ለሙስናና ለብልሹ አሠራር በር የሚከፍቱ አሠራሮችን የመዝጋትና ሕግ የማስከበር ተግባሮች እንደነበሩ፣ ከሚያዚያ 1999 እስከ ታህሳስ 3ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ድረስ ከ54 ሺ 715 ካሬ ሜትር የሚበልጥ የከተማ ቦታ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲታገድ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ (አዲስ ዘመን ጥር 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም) የተሁለደሬ ወረዳ ሐይቅ ለኤኮ ቱሪዝም ሊውል ነው በደቡብ ወሎ ዞን በተሀለደሬ ወረዳ 2ሺ 3ዐዐ ሄክታር የሚሸፍነው ሐይቅ እየደረሰበት ያለውን የአፈር መከካትና ብክለት በመከላከል ለኤኮቱሪዝም ማዋል የሚያስችል ጥናት ተካሄደ፡፡ አብዛኛው አሣ አስጋሪ የሆኑ ከ2ዐ ሺ የሚበልጡ አርሶ አደሮች በሀይቁ አካባቢ እንደሚኖሩ፣ በሀይቁ መሀል ባለው መሬት ላይ ከ8ዐዐ ዓመት የሚበልጥ ዕድሜ ባለው የአባ ኢየሱስ ሞዓ ገዳም ጥቂት የማይባሉ መነኮሳትና ባህታዊያን እንደሚኖሩ፣ ከ8 ሜትር እስከ 37 ሜትር ጥልቀት ባለው ሐይቅ የኤኮቱሪዝምን በማስፋፋት የፈረስና ግመል ግልቢያና ለሎችም የአካባቢውን ህብረተሰብ ባህል ለጐብኚዎች በማቅረብ ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚችል አስታውቋል፡፡ (ኢዜአ) 33 ሕገ ወጥ ቪዲዮና ሺሻ መጠቀሚያ ቤቶች ተያዙ በጌድኦ ዞን በዲላ ከተማ 33 ሕገ ወጥ የቪይዮ ፊልም ማሳያና ሺሻ መጠቀሚያ ቤቶች እንዲዘጉ ማድጉን የዲላ ከተማ ሽግግር አስተዳደር ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡ እርምጃው የተወሰደው በከተማው እየተስፋፋ የመጣው ህገወጥ የቪዲዮና የሺሻ መጠቀሚያ ቤቶች እንዲዘጉ ህብረተሰቡ በተደጋጋሚ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት መሆኑን ፖሊስ ተናግሯል፡፡ (ዋኢማ) ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበር አካባቢ ያለባቸውን ችግር ለመፍታት መነጋገር እንዳለባቸው የመን አሳሰበች ኢትዮጵያና ኤርትራ በድንበር አካባቢ ያለባቸውን ችግር በመነጋገር መፍትሄ ማምጣት እንዳለባቸው የመን አሳሰበች፡፡ የመን ይኸንን ያሳሰበችው በየመን የኤርትራን አምባሳደር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ባነጋገሩበት ወቅት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን የሁለቱ አገሮች የድንበር ውዝግብ አስተማማኝና የተረጋጋ እንዲሆን ሁለቱም አገሮች በመነጋገርና በመመካከር መፍታት እንደሚገባቸው ገልፀዋል፡፡ በወጪ ንግድ ለተሰማሩ ባለሀብቶች የሚደረገው ማበረታቻ በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ለመሆን እያስቻለ ነው የኢትዮጵያ መንግሥት በወጪ ንግድ ለተሰማሩ ባለሀብቶች የሚያደርገው የማበረታቻ ድጋፍ የአገሪቱ ምርት በዓለም ገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆን ማስቻሉን የኢትዮጵያ የቅባት እህሎች፣ ጥራጥሬና ቅመማ ቅመም ላኪዎች ማህበር አስታወቀ፡፡ ኢትዮጵያ በግብርና የወጪ ምርት በ1998 አግኝታው የነበረው 88ዐ ሚሊዮን ዶላር በ1999 ዓ.ም. ወደ አንድ ቢሊዮን ዶላር ማደጉን፣ በወጪ ንግድ ሥራ የተሰማሩ በቂና ፈጣን ብድር አገልግሎት እንዲያኙ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱ፣ በዘርፉ ለተዘጋጁ ባለሀብቶች ሽልማት ማዘጋጀቱ፣ ከተወሰዱት የማበረታቻ እርምጃዎች መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |