Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት...
የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት... Print E-mail
Thursday, 07 February 2008
የአዲስ አበባ ሚሌኒየም ጽ/ቤት 100 ሚሊዮን ዶላር ሊያስገኝ የሚችል ሎተሪ ሊያቀርብ ነው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሚሌኒየም ጽ/ቤት በአለም አቀፍ ደረጃ ኢንተርናሽናል ሎተሪ "The Millennium Flag International Lottery" ለገበያ ሊያቀርብ እንደሆነ ተገለፀ፡፡ ከሎተሪው ሽያጭ 100 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዷል፡፡
የዚህን ሎተሪ ፕሮጀክት ያቀረበውና ከጽ/ቤቱ ጋር ሥራውን በጋራ የሚሰራው የማን ስቴል ስክራና ኃ.የተ.የግ.ማ. ሥራ አስኪያጅ አቶ ሚካኤል አንተነህ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ለሚሌኒየም ጽ/ቤት ያቀረቡበት ፕሮጀክት እስከ 2000 መጨረሻ ድረስ እያንዳንዳቸው የ10 ዶላር ዋጋ ያላቸው 10 ሚሊዮን ሎተሪዎችን በመሸጥ 100 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት የሚያስችል ነው፡፡

የኢትዮጵያ ባንዲራ ያለው ልዩ ሎተሪ በምስጢራዊ ህትመት ለማተም እስራኤል ከሚገኝ ሱት አፍሪካ ዲቨሎፕመንት ኩባንያ ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ የሚሌኒየም ጽ/ቤቱ ከድርጅቱ ጋር በመሆን ለገበያ ለማቅረብ ያቀደው  ሎተሪ ሊበላሽ የማይችልና ምስጢራዊ ቁጥሮችን የሚይዝ ጭምር እንደሆነ የጠቆሙት አቶ ሚካኤል ሎተሪው ከሚያስገኘው ገቢ በተጨማሪ ኢትዮጵያን በማስተዋወቁ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ ከሎተሪ ሽያጭ የሚገኘውም ገቢ የሚሌኒየም ጽ/ቤት ለመስራት ላቀዳቸው ፕሮጀክቶች ይውላል፡፡

የሎተሪው እጣ ለየት ባለ መልኩ የሚዘጋጅ እንደሆነ ያስረዱት አቶ ሚካኤል ዋና ዋና ሽልማቶቹም የኢትዮጵያ ዜግነት፣ ለኢንቨስትመንት የሚሆን ቦታ፣ ለመኖሪያ ቤት የሚሆን ቦታ፣ የከተማ ቁልፍ፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ ቦታዎች ጉብኝት፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርና ፕሬዚዳንት የመጎብኘትና ሌሎች እጣዎችንም የሚያካትት ሲሆን እያንዳንዳቸው ከ20 በላይ እጣዎች እንደሚኖሩትም ተጠቁሟል፡፡

ፕሮጀክቱ በሚቀጥለው ወር ሥራ ይጀምራል፡፡ በዚህ ሳምንትም ከሚሌኒየም ጽ/ቤቱ ጋር ሥራውን ለማስጀመር የሚያስችለው ስምምነት ይፈርማል፡፡

ሎተሪው ለውጭ ዜጎች ነው የሚሸጠው፡፡ ዋናው የፕሮጀክቱ አላማ የኢትዮጵያን ገጽታ ለመለወጥ ነው፡፡ ኢንቨስተሮች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ እንደ ኢትዮጵያዊ ሆነው እንዲሰሩ ለማስቻል ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ተስማምቶ ነው ስራ የተጀመረው፡፡ በእጣዎቹ ውስጥ የኢንቨስትመንት ቦታዎች መካተታቸው የእጣው እድለኛ የሆኑ ሰዎች እንደ ኢትዮጵያዊ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንደሚያስችላቸውም አቶ ሚካኤል ገልፀዋል፡፡ ሎተሪውን በተፈለገው መጠን ለመሸጥ እንደሚቻልና የእስራኤል ኤምባሲ 50 ሺህ ሎተሪ ለመግዛትና የአሜሪካ ኤምባሲም በበኩሉ ሎተሪው በአገሪቱ ሕግ መሰረት ሊሸጥ እንደሚችል ቃል ገብቷል፡፡

የጽ/ቤቱ ዳይሬክተር  ኪሮስ ኃይለሥላሴ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በፕሮጀክቱ መሠረት የሚገኘው ገቢ ሚሌኒየም ጽ/ቤቱ በ150 ሔክታር ቦታ ላይ ለመገንባት ካሰበው የሚሌኒየም ፓርክ ለቤተመጽሃፍትና ለሌሎችም ፕሮጀክቶች ሥራ ማስፈፀሚያ የሚውል ይሆናል፡፡

ሎተሪው በጥንቃቄ እንዲሸጥ ለማድረግና ስለመሸጡ እርግጠኛ ለመሆን ማንስቲል የተባለው ኩባንያ የተለያዩ መረጃዎችና ዝግጅቶችን ያደረገ ሲሆን ከወዲሁ 50ሺህ ሎተሪዎችን ለመግዛት ቃል የገቡ አካላት እንዳሉም ተገልጿል፡፡

በአዲስ አበባ ኤምባሲ ያላቸው አገሮችም ይህንን ሎተሪ ለመግዛት እንዲችሉ ለማድረግ ለኅብረቱ ፅ/ቤት ጥያቄ ቀርቦ አዎንታዊ መልስ መገኘቱንም አቶ ሚካኤል አመልክቷል፡፡

ሎተሪው በአገር ውስጥ ለኢትዮጵያውያን የሚሸጥ ባለመሆኑ ከኢትዮጵያ ሎተሪ ጋር የሚያያዝ አይደለም፡፡ የሚሌኒየም ጽ/ቤቱም ፕሮጀክቱን እንደሚቀበልና እንደሚያስፈጽም ቢስማማም ሎተሪው በውጭ ለውጭ ዜጎች እንዲሸጥ ተደርጎ ብቻ ነው ብለዋል፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >