Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን የሚያቀርበው...
የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን የሚያቀርበው... Print E-mail
Sunday, 06 January 2008

የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን የሚያቀርበው አንድ ድርጅት ብቻ ነው

ከጥር 1 ቀን 2000 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆነውን የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽን ለማቅረብ በርካታ ድርጅቶች የመነሻ መስፈርት መረጃ ቢወስዱም እስካሁን መስፈርቱን አሟልቶ የሚያቀርበው አንድ ድርጅት መሆኑ ተጠቆመ፡፡

የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለስልጣን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አበበ ከበደ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኑን ለማቅረብ መረጃ ከወሰዱት ድርጅቶች መካከል እስካአሁን ለማቅረብ ዝግጁ የሆነው አንድ ድርጅት ብቻ ነው፡፡ አራት ለሚሆኑ ድርጅቶች የአስመጪነት ፈቃድ ለመስጠት በተቋቋመው የቴክኒክ ቦርድ እየታየ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

እቃውን ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነው ድርጅት አንድ መሆኑ ከዋጋ ጋር ተይይዞ ችግር አይፈጥርም ወይ ለተባለው ሲመልሱ፤ 45 በመቶ ከሚሆነው ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክስ ነፃ መሆኑ የተጠቃሚዎችን የዋጋ ጫና እንደሚቀንስ ገልፀው በዋጋ ለመደራደር ከተለያዩ አገሮች መረጃ እየተሰበሰበ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

አቅራቢዎቹ በመሳሪያው ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በ48 ሰዓታት ውስጥ ጥገና መስጠት እንዳለባቸው የገለፁት አቶ አበበ አቅራቢ ድርጅቶች ጥገና ለመስጠት ያላቸው ብቃት፣ መለዋወጫ መሳሪያዎች፣ ሰራተኞች በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸውም ገልፀዋል፡፡ ፈቃድ ያገኘው ድርጅትም ይህ ማድረግ እንዳለበት አምኖ መግባቱን አመልክተዋል፡፡

ጥገናው የአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ሰራተኛ በተገኘበት የሚከናወን ሲሆን በገቢዎች ጽ/ቤት የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኑን የሚያስተባብር የፕሮጀክት ጽቤት ተቋቁሞ ሰራተኞች ቅጥር ላይ መሆኑንንም ገልፀዋል፡፡

እንደ አቶ አበበ ገለፃ፣ በመጀመሪያ ዙር የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኑ በአዲስ አበባ በ3 ዘርፎች፤ ወርቅና ብር ሰሪዎች፣ ሆቴልና ሬስቶራንትና በሱፐር ማርኬት ዘርፎች ተግባራዊ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

የአቅራቢው፣ የአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣንና የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት አቅም ሲስፋፋና ልምድ ሲዳብር የአገሪቱ የደረሰኝ አጠቃቀም ስርዓቱን ሙሉ በሙሉ ወደ ሽያጭ መመዝገቢያ ቴክኖሎጂ ለመቀየር መታሰቡንም አቶ አበበ ገልፀዋል፡፡

የተመረጡት ሶስት ዘርፎች ገቢና ወጪያቸው ከፍ ያለ በመሆኑ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ከፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን መረጃውን በሚያስተላልፍ መልኩ በሱፐር ማርኬቶችና ሬስቶራንቶች ተግባራዊ እየሆነ በመምጣቱ መሆኑን ገልፀው በአዲስ አበባ የቴሌኮሙኒኬሽን መሠረተ ልማት የተሟላ በመሆኑ ከሌሎች ቅድሚያ ማግኘቱንም ገልፀዋል፡፡

በቀጣይ ተጨማሪ አቅራቢ ድርጅቶች እንደሚኖሩ ሲጠበቅ፤ ተጠቃሚዎች ይህን አሰራር መዘርጋታቸው ለግብርና ታክስ ብቻ ሳይሆን የንግድ ሥራዎችን ለመቆጣጠር ለመምራት የሚያስችል አቅም እንዲያዳብሩ እንደሚረዳም አቶ አበበ ገልፀዋል፡፡

አገልግሎቱን እንዲያገኙ የተመረጡት ሆቴሎች፣ ሱፐር ማርኬቶችና ወርቅና ብር ሰሪዎች ያላቸውን አቅምና የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ገልፀው፡፡ የድርጅቶች ትልቅና ትንሽነት ሳይሆን በአካባቢው ባለው የቴሌ መሠረተ ልማት በተወሰኑ ወርቅ ቤቶችና ሆቴሎች በአብዛኛዎች ሱፐርማርኬቶች አገልግሎቱን እንደሚያገኙ ተገል..ል፡፡

ከጥር 1 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው የመጀመሪያው ዙር አገልግሎት በክልሎች ተግባራዊ እንደማይሆን ገልፀው ይህም የክልሎችን የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት፣ የቢዝነስ እንቅስቃሴና የመግዛት አቅም መሰረት አድርጎ መሆኑንም አቶ አበበ ገልፀዋል፡፡

መረጃው በመስመር አልባ ቴክኖሎጂ ከአገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ጋር በመገናኘቱ የቴሌኮሙኒኬሽን መሰረተ ልማት ግንባታ መጠናከር በሁሉም አካባቢዎች ተግባራዊ የሚሆንበት ሁኔታ እንደሚፈጠርም ተናግረዋል፡፡

የሽያጭ መመዝገቢያ ማሽኑ የድርጅቶችን የሽያጭ መመዝገቢያ ሁኔታ ከአለም አቀፍ ሁኔታ ጋር ለማጣጣም ብሎም በአገራችን ለመስራት የሚመጡ ባለሐብቶች በአገራቸው ቢዝነሳቸውን የሚቆጣጠሩበትና ታክስ የሚከፍሉበት ሁኔታ ጋር ተመሳሳይ ስለሚሆን ባለሐብቶችን ለመሳብ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡

ፔትራም ኩባንያ ከ2..000 ያላነሱ ማሽኖችን ማዘጋጀቱን ገልፀው ሌሎች ኩባንያዎች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ በሚያቀርቡበት ሁኔታ ላይ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

በቤዛዊት ሥዩም

 

 
< Prev   Next >