Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 25th
Home arrow Sections arrow “ዩጋንዳ 8000 ወታደሮችን ለመላክ ትችላለች”
“ዩጋንዳ 8000 ወታደሮችን ለመላክ ትችላለች” Print E-mail
Thursday, 07 February 2008
ሙሴቪኒ

በሶማሊያ እንዲሰማራ የተፈለገውን የሰላም አስከባሪ ቁጥር ዩጋንዳ ልታሟላው እንደምትችል ፕሬዚዳንት ዩሪ ሙሴቪኒ አስታወቁ፡፡
ዩጋንዳ 8000 ወታደሮች ወደሶማሊያ ለመላክ አቅም ያላት መሆኑን ሙሴቪኒ ለተመድ ዋና ፀሐፊ ባን ኪሙን የገለፁት ለአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በመጡበት ወቅት ነው፡፡

ሙሴቪኒ ጉዳዩን ከመከላከያ ከፍተኛ አመራሮቻቸው ጋር እንደሚወያዩበት ቃል እንደገቡላቸው ነው ኒው ቪዥን የተሰኘው በዩጋንዳ የሚታተመው ጋዜጣ የዘገበው፡፡

ከዋና ፀሐፊ ባንኪሙን ጋር በሸራተን ሆቴል ባደረጉት ውይይት፣ ወደ ሶማሊያ ወታደሮቸቸውን እንዲልኩ የተጠየቁት የአፍሪካ ኅብረት ሃገሮች አለመላካቸውን ሙሴቪኒ ነቅፈዋል፡፡

በገንዘብ እጥረት ምክንያት ወታደሮቻቸውን ለመላክ እንዳዳገታቸው የሚናገሩት ሃገሮችን “የእናቴ ቀሚስ አወላከፈኝ” ዓይነት ሰበብ የማቅረብ ያህል ቆጥረውባቸዋል፡፡

“ይኸ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ሶማሊያን መርዳት ለሁሉም የአፍሪካ ሃገሮች ግዳጅ እንጂ የእርዳታ መሰብሰቢያ ተልዕኮ ተደርጎ መቆጠር የለበትም”
ሙሴቪኒ ከአምባገነኑ ኢዲ አሚን አገዛዝ ዩጋንዳን ነፃ ለማውጣት ታንዛኒያ 50”000 ወታደሮች ልካ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ “በርግጥ” ይላሉ ሙሴቬኒ፣ “በርግጥ በሶማሊያ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ አቅጣጫ መኖር አለበት”    

ሙሴቬኒ በሃገራቸው ካለው በትጥቅ ትግል ከሚደገፈው ሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ ጋር የሰላም ንግግሩን በአንድ ወር ጊዜ ለመጨረስ መስማማታቸውን ለባንኪሙን ተስፋ ሰጪ ንግግር አድርገውላቸዋል፡፡

በኬንያ የተፈጠረውን ግጭት አስመልክተው በዩጋንዳ፣ በሩዋንዳ፣ በደቡብ ሱዳንና በምሥራቅ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያለውን ኢኮኖሚ እንደጎዳ ዋና ፀሐፊው አስታውሰዋቸዋል፡፡

በዚያች ሃገር ለተከሰተው ችግር መፍትሔ ለማፈላለግ ቢቻል ከኬንያ ውጭ ያሉ ገለልተኛ ዳኞችና ጠበቆች የተካተቱበት አጣሪ ኮሚሽን ማቋቋም የተሻለ እንደሚሆን ለባንኪሙን አስተያየታቸውን መስጠታቸውን ኒው ቪዥን ዘግቧል፡፡
 
< Prev   Next >