Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Aug 29th
Home arrow Sections arrow ለፈጣሪ እንስገድ ወይስ ለሰው
ለፈጣሪ እንስገድ ወይስ ለሰው Print E-mail
Thursday, 07 February 2008
በሪፖርተር ጋዜጣ ጥር 25 ቀን 2000 እትም በ”እኔ የምለው” ገጽ “ባለ አደራ ጮኸ ከተራራ”“ በሚል ርዕስ የቀረበው አስተያየት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤትና ፓትርያርኩ ራሳቸውን እንዲፈትሹና ከምዕመናን ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን ይመስላል የሚለውንም ትኩረት ሰጥተው እንዲገመግሙ ይጋብዛል የሚል እምነት አለኝ፡፡
የፓትርያርኩን ምስል ከፍ ባለ ደረጃ በቢልቦርድ በየአብያተ ክርስቲያናቱ ዐውደ ምህረት መስቀል ተገቢነት የለውም ብቻ ሳይሆን የራስ ወዳዶች ባህሪ መሆኑን መታወቅ ይኖርበታል፡፡ እንዲመለኩ የሚፈልጉ ደግሞ የሃይማኖት መሪ መሆን አይችሉም፡፡ በደርግ ሥርዓት የመንግሥቱ ኃይለማርያም ምስል በየቢሮው፣ በየማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅቶች፣ ሕዝብ በብዛት በሚሰበሰብባቸው አደባባዮች ሁሉ ይሰቀል እንደነበር የሚዘነጋው ያለ አይመስለኝም፡፡ በዚህም የተነሳ ሕዝቡ በከፍተኛ ደረጃ ሲያማርር እንደነበር አይረሳም፡፡ ከሥልጣን በወረደ ማግስት ግን ምስሎቹ ከተሰቀሉበት ወርደው ተወርውረዋል፡፡ በቆሻሻ ማጠራቀሚያ ተጥለዋል፡፡ የፓትርያርኩም የቢልቦርድ ምስል ይህ ዓይነቱ ዕጣ እንደሚገጥመው አይጠረጥርም፡፡ በኋላ ከማፈር ቀድሞ መጠንቀቅ ብልህነት ነው፡፡ ምስልን ከመስቀል ይልቅ የሕዝብን ልብ ማግኘት ፀጋ ነው፡፡

አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጸምበት፣ ምዕመናን ለፈጣሪ ፀሎት በሚያደርሱበት ሥፍራ ላይ ቤተክርስቲያንን በሚከልል ደረጃ ቢልቦርድ መትከል ከፈጣሪ በላይ እኔ ነኝ የሚል መልዕክትን ይጭራል፡፡ ስለሆነም ምዕመናን ለፈጣሪ ከመስገዳችሁ በፊት ለእኔ ስገዱ የማለት ዝንባሌ ያለውም ሆኖ ሊተረጎም ይችላል፡፡

ከፓትርያርኩ ጎን ያሉት መንፈሳዊ አባቶች ሥልጣናችን እስካልተነካና ጥቅማችን እስካልተጓደለ ድረስ ግድ የለንም ያሉ ይመስላሉ፡፡

ስለሆነም የሚቀርብባቸውን አስተያየት ተቀብለው ውለው ሳያድሩ በየአብያተ ክርስቲያናቱ የተከሉትንና ምስላቸውን የለጠፉበት ቢልቦርድ ያንሱና እውነተኛ የሃይማኖት አባት ለመሆን የሚያስችላቸውን መንፈሳዊ ሥራ ያከናውኑ፡፡

(በቀለ ጌታቸው፣ ከአራት ኪሎ)
 
< Prev   Next >