Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ሰንሻይን በኤች.አይ.ቪ ወላጅ አልባ...
ሰንሻይን በኤች.አይ.ቪ ወላጅ አልባ... Print E-mail
Sunday, 10 February 2008
ሰንሻይን በኤች.አይ.ቪ ወላጅ አልባ ለሆኑ ህፃናት ት/ቤት ማስገንባት ጀመረ

ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ወላጆቻቸውን በኤች.አይ.ቪ ላጡና ለችግረኛ ቤተሰብ ህፃናት ትምህርት ቤቶች ለማስገንባት ከያዘው ዕቅድ ጋር በተያያዘ የመጀመሪያውን ትምህርት ቤት በነቀምት ከተማ ማስገንባት ጀመረ፡፡
ይኸው በነቀምት ከተማ መገንባት የጀመረው ትምህርት ቤት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ሲሆን ከአንደኛ እስከ አስረኛ ክፍል ያሉ 400 ተማሪዎችን እንደሚስተናግዱ የሰንሻይን ኮንስትራክሽን የቢዝነስ ዴቬሎፕመንትና የህዝብ ግንኙነት አገልግሎት ሃላፊ አቶ ዳኛምየለው ግርማ ገልፀዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ኤች.አይ.ቪ በይበልጥ በነቀምቴ በመስፋፋቱ ከተማዋ ትምህርት ቤቱን ለማስገንባት የተመረጠች ሲሆን የከተማዋ ከንቲባ አቶ ደረጄ ደሬሳ የት/ቤቱ መከፈት አዎንታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረውና ለሌሎችም ባለሀብቶች በተመሳሳይ መልክ ቢሳተፉ ለማህበራዊ ችግሩ ትርጉም ያለው መፍትሄ ለማምጣት እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡

የትምህርት ቤቱ ግንባታና ተያያዥ ወጪዎች አምስት ሚሊዮን ብር የሚደርስ ሲሆን ወጪውም ሙሉ በሙሉ በሰንሻይን ኮንስትራክሽን እንደሚሸፍን አቶ ዳኝምየለው ተናግረዋል፡፡

የኮንስትራክሽን ድርጅቱ ተመሳሳይ ሌሎች አራት ት/ቤቶች በመጪዎቹ ዓመታት በአማራ ክልል/ባህር ዳር/፣ በትግራይ ክልል /መቀሌና፣ በደቡብ ክልልና በአዲስ አበባ እንደሚያስገበነባ ታውቋል፡፡

እንደ አቶ ዳኛምየለው ገለፃ የኮንስትራክሽን ድርጅቱ በመጀመሪያ የትምህርት ቤቱን ግንባታ በአዲስ አበባ ለማካሄድ ለሚመለከተው ክፍል ትምህርት ቤት የሚገነባበት ቦታ ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥያቄ ቢቀርብም ምላሽ ባለማግኘቱ ግንባታው በነቀምት ከተማ ጀምሯል፡፡

ይህ ኩባንያው በራሱ ተነሳሽነት የወሰደው እርምጃ በአገሪቱ ያለውን የማህበራዊ ችግር ለመፍታት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት መሆኑን አቶ ዳኛምየለው ገልፀዋል፡፡

በጋዜጣው ሪፐርተር
 
< Prev   Next >