Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow በባህር ጠለቅ ኬብል የመቋረጥ አደጋ...
በባህር ጠለቅ ኬብል የመቋረጥ አደጋ... Print E-mail
Sunday, 10 February 2008
በባህር ጠለቅ ኬብል የመቋረጥ አደጋ ምክንያት ተከስቶ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት ችግር ተቀረፈ

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በሱዳን የባህር ጠለቅ ኬብል በኩል አድርጎ ከአለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎት ጋር የሚገናኝበት ባለ 155 ሜጋቢት አቅም ያለው ባለባህር ጠለቅ የኢንተርኔት ሊንክ ኬብል በሜዲትራንያን አካባቢ የደረሰበት አደጋ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡
ኮርፖሬሽኑ ለሪፖርተር ጋዜጣ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በአብዛኛው የመካከለኛው ምስራቅና በህንድ አካባቢ በሚገኙ አገራት ዘንድ ተከስቶ የነበረው የኢንተርኔት አገልግሎት የፍጥነት መቀነስ ችግር በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ተቀርፏል፡፡

ለወደፊቱ በተመሳሳይ አደጋ ምክንያት በሀገራችን የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥና የፍጥነት መቀነስ ችግር እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ የገለጸው ኮርፖሬሽኑ ለአለም አቀፍ መገናኛው የሚጠቀምበትን የሳተላይት ሊንክ አሁን ካለበት 50 ሜጋቢት በሰኮንድ ወደ 200 ሜጋቢት ለማሳደግ ማቀዱን ገል..ል፡፡

በጅቡቲ በኩል አሁን ያለው የ34 ሜጋቢት በሰኮንድ አቅም ወደ 155 ሜጋቢት በሰኮንድ ለማስተላለፍ ወደሚያስችል አቅም ለማሳደግ የሚደረገው ጥረትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮርፖሬሽኑ አክሎ ገል..ል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >