Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Saturday
Jul 05th
Home arrow Sections arrow ነጋዴዎች የደረቅ ወደብ...
ነጋዴዎች የደረቅ ወደብ... Print E-mail
Sunday, 10 February 2008
ነጋዴዎች የደረቅ ወደብ ወደ መሀል አገር እንዲሆን ጠየቁ

"ኮንትሮባንድ ጉምሩክም አለ"

ፌዴራል ትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር በሞጆና ሰመራ ላይ ሊያስገነባ ያሰበው ደረቅ ወደብ የንግዱን ህብረተሰብ የበለጠ የሚያጉላላና ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ወደ መሀል አገር እንዲዛወር ነጋዴዎች ጠየቁ፡፡ በጅቡቲ ወደብም ቀልጣፋ አገልግሎት እንደሌለና ኮንትሮባንድ በጉምሩክ ውስጥም እንዳለ ጠቆሙ
ነጋዴዎቹ ይኸንን የገለፁት፣ የገቢዎች ሚኒስቴርና የንግዱ ህብረተሰብ ጥር 28 ቀን 2000 ዓ.ም በግሎባል ሆቴል ባደረጉት የግማሽ ቀን የጋራ ውይይት ላይ ነው፡፡

በጅቡቲ ወደብ ላይ ከፍተኛ መጉላላት እንደሚደርስባቸውና የማስፈፀም ችግር መኖሩን የገለፁት ነጋዴዎቹ፣ በአንድ መርከብ ላይ የተጫነን ኮንቴይነር ለማውረድ እስከ 20 ቀንና ከዚያም በላይ ጊዜ እንደሚወስድ ተናግረዋል፡፡

የተጫኑ እቃዎች ለማውረድ በሚፈጀው ቀናት የመርከብ ኪራይ እንደሚከፍሉ፣ ነገር ግን የእቃዎቹ መዘግየት አዲስ አበባ ውስጥ በጥሬ ዕቃ እጦት ፋብሪካዎች እንደሚዘጉ ገልፀዋል፡፡

ነጋዴዎቹ እንደተናገሩት፣ የደረቅ ወደ ግንባታው በአዲስ አበባ ዙሪያ ወይም በቅርብ አካባቢዎች ቢሆን የተሻለ መሆኑን ጠቁመው፣ አብዛኛዎቹ ፋብሪካዎች በዋና ከተማው ውስጥ ስለሚገኙ ከዚህ ውጭ ግንባታ ማካሄዱ ችግሩን ለማቃለል የማይችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በእለቱ ከንግዱ ህብረተሰብ ጋር በተደረገ ውይይት ባለፈው ዓመትነጋዴው አንስቷቸው የነበሩ ጥያቄዎች የአፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፣ ሪፖርቱን ተከትሎ ጥያቄዎችም ተሰንዝረዋል፡፡

"ኮንትሮባንድ በአዲስ አበባ ውስጥ ብቻ ሳይሆን በጉምሩክም ውስጥ አለ" ያሉት ነጋዴዎቹ፣ ጭነት ከጅቡቲ በቀጥታ ተጭኖ ወደ ግለሰቦች ቤት እንደሚደርስ እየታወቀ፣ ግለሰቦቹ ቢያዙም ወዲያው እንደሚለቀቁ፣ እቃ ሳይፈተሽ ሊያልፍ እንደሚችልና ህጋዊ ነጋዴዎችን ለኪሣራ እንደሚዳርጋቸው ተናግረዋል፡፡

ነጋዴዎቹ አያይዘው እንደገለፁት፣ ከቀረጥ ተመላሽ ክፍያ በኮሚቴ ነው የሚመለሰው ተብለው ከአንድ ዓመት በላይ እንደሆናቸው፣ በጉምሩክ ውስጥ ምንም ስራ እንደማይሰራ፣ ኢንፎርሜሽን በትክክል ስለማይተላለፍ፣ ከተለያየ ሰው የተለያየ መረጃ እንደሚሰጣቸው፣ ወጥ ዋጋ ባለመኖሩ ለአንድ አይነት እቃ የተለያየ  ዋጋ እንደሚነገራቸውና የተለያየ ችግር እንደሚደርስባቸው ተናግረዋል፡፡
 
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከነጋዴዎቹ የተነሱትን ጥያቄዎችና ቅሬታዎች ካዳመጠ በኋላ በሰጠው ምላሽ፣ ከቀረጥ ተመላሽ ሥርዓት ከቫት ሥርዓት ጋር የተያያዘ ስለሆነ አስቸጋሪ መሆኑን፣ ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ የቀረጥ ተመላሽ ክፍያ መስጠት መጀመራቸውን፣ ነገር ግን ያልተስተናገዱ ነጋዴዎች መኖራቸውን ገልጾ እያስተካከለ መሆኑን ገል"ል፡፡

መረጃዎች ተሟልተው ባለመምጣታቸው፣ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም ነጋዴዎቹ ማሟላት የሚገባቸውን ባለመንገሩ ችግሩ የነበረ መሆኑን ጠቁሞ፣ እንደሚስተካከል ቃል ገብቷል፡፡

በታምሩ ጽጌ
 
< Prev   Next >