Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 25th
Home arrow Sections arrow የአቶ ተመስገንና የአቶ መሀመድ...
የአቶ ተመስገንና የአቶ መሀመድ... Print E-mail
Sunday, 10 February 2008
የአቶ ተመስገንና የአቶ መሀመድ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ተጠየቀ

የአቶ ተመስገን ዘውዴና የአቶ መሀመድ አሊ መሀመድ ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ጥያቄ ማቅረቡ ተገለፀ፡፡
የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ ሳሳሁልህ ለሪፖርተር እንደገለፁት የሁለቱ የፓርላማ አባላት ያለመከሰስ መብት እንዲነሳ የተጠየቀው በቅንጅት ስም የተመዘገቡ ንብረቶችንና ለፓርቲው ስራ የተሰጣቸውን ቢሮ እንዲያስረክቡ ተጠይቀው ተግባራዊ ባለማድረጋቸው ነው፡፡

አቶ ተመስገንና አቶ መሀመድ የፓርላማ ተመራጭ በመሆናቸው ቅንጅት ላቀረበላቸው ህጋዊ ጥያቄ መልስ ባለመስጠታቸው በቀጥታ ክስ ለመመስረት እንዲቻል ከአፈ ጉባኤ ተሾመ ቶጋ ጋር መነጋገራቸውን አቶ ሳሳሁልህ አስረድተዋል፡፡

ለፓርላማ የቀረበው ያለመከሰስ መብት መነሳት ጥያቄ መልስ እስኪሰጥ ድረስ ቅንጅት በሁለቱ የፓርላማ ተመራጮች ላይ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ክስ መመስረቱን ከፀሐፊው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል፡፡

እንደ አቶ ሳሳሁልህ ገለፃ በፖሊስ የተመሰረተው ክስ ለማንቀሳቀስ የፓርላማው የሕግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ውሳኔ ይጠበቃል፡፡

በተያያዘ ዜና የአሜሪካ ኤምባሲ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ህጋዊ እውቅና መስጠቱን የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አየለ ጫሚሶ ገልፀዋል፡፡

አቶ አየለ ጫሚሶ በአንዳንድ መገናኛ ብዙሃን የአሜሪካ ኤምባሲ የቅንጅት ለአንድነት ለዴሞክራሲ ፓርቲ ህጋዊ ተጠሪ አቶ አየለ አለመሆናቸውን ኤምባሲው እንደገለፀ ተደርጎ መዘገቡን አስታውሰው፤ "ድርጊቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችንና የአሜሪካ መንግሥትን ለማጣላት ሆን ተብሎ የተቀናበረ ነው" ብለዋል፡፡ በማያያዝም ኤምባሲው ለፓርቲዎችና ለፓርቲ መሪዎች ደረጃ የመመደብ ተግባር ላይ ፈፅሞ እንደማይሳተፍ ማረጋገጡን ተናግረዋል፡፡

በተሾመ ንቁ
 
< Prev   Next >