| ተጨማሪ የቅንጅት አባላት ከእስር ተለቀቁ |
|
|
| Sunday, 10 February 2008 | |
|
ምርጫ 97 ተከትሎ በተፈጠረ አለመግባባት ምክንያት ከታሰሩት የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባላት መካከል 26 መፈታታቸውን የአገር ሽማግሌዎች ገለፁ፡፡
የአገር ሽማግሌዎች ለሪፖርተር በላኩት መግለጫ እንዳስታወቁት እስረኞቹ የተፈቱት ቀደም ሲል እንደተደረገው መንግሥት ምህረት በማድረጉ ነው፡፡ መንግሥት ያደረገውን ይቅርታ እንደሚያደንቁ የገለፁት የአገር ሽማግሌዎች መግለጫ በተመሳሳይ መልኩ በማረሚያ ቤት የሚገኙ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች በተመሳሳይ መልኩ ይፈታሉ የሚል እምነት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡ ከእስር የተፈቱት የቅንጅት አባላት ዮሴፍ ገ/እግዚያብሄር ይልማ፣ ጌታዬ ወዳጄነው ጎበዜ፣ ዮናስ መኮንን መንግስቴ፣ እንዳልካቸው ተስፋው፣ ጋሻው ግርማ ገ/ጻዲቅ፤ አያሌው ጥላሁን፣ ዘነበ ዙላ፣ ዑስማን ሱሌማን፣ ሽመልሽ አሰፋ አርጋው፣ ብሩክ ታደሰ ወረታ፣ አሸናፊ ዮሐንስ ሀይሌ፣ ፍቃዱ ግርማ፣አዲሱ ባዴቻ፣ አጥላባቸው አያሌው፣ ክንዴ አያሌው፣ ፋሲል አማረ፣ ቱራ ጂማ፣ ትዕዛዙ ከድር፣ አሸናፊ ማሞ በላቸው፣ ግዛቸው ግርማ ጨርበ፣ ፍሬዘር ገ/ኪዳን ተክሉ፣ ኤርሚያስ ሽፈራው፣ ፍሬዘር ጉያ፣ ጌታቸው ሄኖክ፣ ብርሃኔ ካሳዬ፣ ኤልያስ አዱኛ ናቸው፡፡ የአገር ሽማግሌዎች በአገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ከአገር ውጪ ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችንና መንግሥትን ለማስታረቅ እንደሚንቀሳቀሱ መግለፃቸው አይዘነጋም፡፡ በኢትዮጵያ ሰላምና ፍቅር እንዲሰፍን ጥረት እያደረጉ የሚገኙት የአገር ሽማግሌዎች ኦነግና መንግሥትን ለማስማማት ጥረት መጀመራቸውን ፕሮፌሰር ኤፍሬምን ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ በአሰግድ ተፈራ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |