Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow ሁለት የብድርና ቁጠባ ተቋማት...
ሁለት የብድርና ቁጠባ ተቋማት... Print E-mail
Sunday, 06 January 2008

ሁለት የብድርና ቁጠባ ተቋማትከአለም 50 ምርጦች ውስጥ ተካተቱ

በብሔራዊ ባንክ እውቅና ተሰጥቷቸው የሚቀንቀሳቀሱ ሃያ ሰባት የብድርና ቁጠባ ተቋማት አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥም የአማራ፣ የደደቢት፣ የኦሮሚያ፣ አዲስና ኦሞ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ተጠቃሽ ናቸው፡፡

እነዚህ የብድር ተቋማት አነስተኛ ብድሮችን በመስጠት የሚንቀሳቀሱና አነስተኛና መካከለኛ ቢዝነሶችን ለማገዝ ሰፊ ድርሻ እንዳላቸውም ይታመናል፡፡ በየዓመቱ እየሰጡ ያሉት ብድርም እያደገ ሲሆን በተገባደደው የፈረንጆች የበጀት ዓመት እስከ ሴፕቴምበር 31,2007 ድረስ 27ቱ የብድርና ቁጠባ ተቋማቱ ከ2.8 ቢሊዮን ብር በላይ ማበደር ችለዋል፡፡ በተቋማቱ ገንዘብ እየቆጠቡ ያሉ ተገልጋዮች ቁጥርም ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደርሷል፡፡

ከኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማህበር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ 27ቱ የብድርና ቁጠባ ተቋማት 1.76 ሚሊዮን ደንበኞች አሏቸው፡፡
 
በእነዚህ ተቋማት ተበዳሪ የሆኑ ዜጎች ቁጥርም እያደገ በመምጣቱ ተቋማቱ በየበጀት ዓመቱ ለማበደር በእቅድ የሚይዙትን የገንዘብ መጠን እንዲያሳድጉም አስገድዷቸዋል፡፡

በየክልሉ ከተቋቋሙት የብድርና ቁጠባ ተቋማት የአማራና የደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋሞች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በአማራ ክልል የደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም ደግሞ በትግራይ ክልል በመንቀሳቀስ አገልግሎት መስጠት ከጀመሩም ከ8 ዓመታት በላይ አስቆጥረዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ በተመሳሳይ መልኩ ከተቋቋሙት የብድርና ቁጠባ ተቋማት ውስጥ ብዙ ተበዳሪ በማፍራትና ከፍተኛ ገንዘብ በማበደር ተጠቃሽ ሆነው ቆይተዋል፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ በቢዝነስ ንግድና በጠቅላላ ኢንቨስትመንት ዙሪያ መረጃዎችን በማጠናቀርና የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማትን ደረጃ በመመዝገብ ይፋ የሚያደርገው ፎርቢስ መጽሔት ባለፈው ሳምንት ይፋ እንዳደረገው በአለም ላይ ካሉ የብድርና 50 የገንዘብ ተቋማት ውስጥ የአማራና የደደቢት የብድር ተቋማት መካተታቸውን አመልክቷል፡፡

የኢትዮጵያ አነስተኛና ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማኅበር የተገኘው መረጃ ደግሞ ፎርቢስ ከሃምሳ ምርጥ የአለማችን የማክሮፋይናንስ ሰንጠረዥ ውስጥ ያካተታቸው ሁለቱ የብድር ተቋማት በአገር ውስጥ ያላቸው ደረጃም የመጀመሪያ እንደሆነ ያመለክታል፡፡ በመረጃው መሰረት በዘንድሮው የበጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም የ923.8 ሚሊዮን ብር፣ ደደቢት ደግሞ 939.7 ሚሊዮን ብር አበድረዋል፡፡

መጽሔቱ በአለም አቀፍ ደረጃ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ያሉ መሆኑን ጠቅሶ፣ ከእነዚህ ተቋማት ውስጥ 50 የሚሆኑትን ምርጥ ወይም በአገልግሎት ብቃታቸው መሪ ናቸው ያላቸውን በደረጃ አስቀምጧል፡፡

በመጽሔቱ የደረጃ ሰንጠረዥ መሠረት የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም በአለም የ6ኛ ደረጃን መያዙን ሲያመለክት የደደቢት ብድርና ቁጠባ ተቋም ደግሞ 31ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ አመልክቷል፡፡

በተለይ የአማራ ብድርና ቁጠባ ባሳለፍነው የፈረንጆቹ በጀት ዓመት 537..000 ተበዳሪዎችን ያፈራና 225..000 የሚሆኑ የቁጠባ ደንበኞች ያለው መሆኑን መጽሔቱ ጠቁሞ ይህም የተበዳሪና የቆጣቢ ደንበኞቹ ቁጥር ከአፍሪካ በትልቅነታቸው ከሚጠቀሱ የገንዘብ ተቋማት ውስጥ አንዱ እንዲሆን እንዳደረገው አስታውቋል፡፡

በአሁኑ ወቅት የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም 574፣ የደደቢት ደግሞ 422..394 ደንበኞች አሏቸው፡፡ ከሁለቱ ተቋማት የኦሮሚያ፣ የኦሞ /ደቡብ/ አዲስ ብድር ተቋማት ከ3 እስከ 5ኛ ያለውን ደረጃ ላይ እንደሚገኙም የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋም ማህበር ይፋ አድርጓል፡፡

እንደ ፎርቢስ ገለፃ እነዚህ የብድር ተቋማት የመጨረሻ ተወዳዳሪዎች ሆነው የቀረቡት 641 የጥቃቅንና አነስተኛ የገንዘብ ተቋማት ውስጥ ሲሆን በውድድሩ እጩ ለመሆን ተቋማቱ የገንዘብ ቁጥጥራቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን ለፎርቢስ የአማካሪዎች ቡድን በማቅረብ ከተገመገመ በኋላ ነው፡፡

በመጽሔቱ ዘገባ መሰረት ደረጃቸው መሠረት ያደረገው ጠቅላላ ብድር፣ የሥራ ማስኪያጃ ወጪያቸው፣ ብቃታቸው፣ በአበዳሪው የሚወጣው ወጪና አጠቃላይ የብሔራዊ ነፍስ ወከፍ ገቢን መሠረት አድርጎ የብድር ገቢያቸው ተሰልቶ ያላቸው የብድር ድርሻ ክፍፍሉ የሃብት መጠኑ ሁሉ ከግምት በማስገባት ነው፡፡

በፎርቢስ የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ የመጀመሪያው ደረጃ ማግኘት የቻሉት በላቲን አሜሪካና በእስያ ያሉ የብድር ተቋማት ናቸው፡፡

በመጽሔቱ ዘገባ መሰረት ከ50ዎቹ ምርጥ የብድርና ቁጠባ ተቋማት ውስጥ 8 የአፍሪካ የብድርና ቁጠባ ተቋማት የተካተቱ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ አራቱ የሞሮኮ ሁለቱ የኢትዮጵያና አንድ አንድ ደግሞ የቱኒዝያና የግብጽ ተቋማት ናቸው፡፡

በደረጃ ሰንጠረዡ መሠረት የመጀመሪያውን ደረጃ የያዘው ኤ ኤስ ኤ የተባለ የባንግላዴሽ የብድርና ቁጠባ ሲሆን በሁለተኛ ደረጃ ባንዲሃን የተባለ የሕንድ ተቋም ነው፡፡ ሦስተኛ እና አራተኛ የሆኑት ደግሞ የብራዚልና የኮሎም..ያ ተቋማት ናቸው፡፡

ሁለቱ የኢትዮጵያ የብድር ተቋማት መጽሔቱ በየዓመቱ ከሚያወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ ውስጥ ከአንድ እስከ ሃምሳ ባለው ደረጃ ውስጥ ሲካተቱ የመጀመሪያቸው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

በዳዊት ታዬ

 

 
< Prev   Next >