| ለብሄራዊ ባንክ የተጭበረበረ ወርቅ... |
|
|
| Sunday, 10 February 2008 | |
![]() ሚኒስትር ግርማ ብሩ ብሄራዊ ባንክ በሀሰተኛ ወርቅ ግዢ መጭበርበር የደረሰበት በነበረው የአሰራር ክፍተት መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ግርማ ብሩ ለሪፖርተር ገለፁ፡፡ አሰራሩ ላይ ለውጥ እንደተደረገም አመልክተዋል፡፡ ሚኒስትሩ እንዳስታወቁት ቀደም ሲል ባንኩ ወርቅ ይረከብ የነበረው ከራሱ ከነጋዴው ነበር፡፡ ነጋዴው ራሱ ወርቁን አስመርምሮ ለባንኩ ያስረክባል፡፡ በዚህ የአሰራር ክፍተት የተጠቀሙ ባንኩ ላይ የማጭበርበር ድርጊት ፈፅመዋል፡፡ ማጭበርበሩን ፈፅመዋል በሚል በቁጥጥር ሥር የዋሉትን አስመልክቶ ..ወንጀሉን ማን ፈፀመው፣ እንዴት ተፈፀመ የሚለው እየተጣራ ስለሆነ ምርመራው ሲጠናቀቅ ይፋ ይሆናል.. በማለት ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ክፍተት የፈጠረውን አሰራር በመቀየር በአሁኑ ወቅት ወርቁን የሚመረምረው ላቦራቶሪና የባንኩ ተወካዮች በአንድነት ንጹህ ወርቅ ለመሆኑ የተመሰከረለትን ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ እንዲያስረክቡ የሚያደርግ አሰራር መጀመሩን አቶ ግርማ አመልክተዋል፡፡ በሌላ በኩል ባንኩ የራሱ የሆነ የመመርመሪያ ማዕከል እንዲኖረው መታሰቡንም ገልጸዋል፡፡ ሃያ የሚደርሱ ግለሰቦችና ባህላዊ ወርቅ አምራች ማህበራት ወርቅ በማቅረብ ላይ መሆናቸውን ያስረዱት ሚኒስትሩ ..የተወሰኑ ስላጭበረበሩ ሌሎች በህጋዊ መንገድ የሚሰሩ ሳይደናገጡ ስራቸውን መስራት አለባቸው.. ብለዋል፡፡ በሌላ ዜና በቅርቡ የተደረገው የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ከአንድ ዓመት ከአንድ ወር በኋላ የተደረገ መሆኑን አቶ ግርማ አስታውቀዋል፡፡ ሚኒስትሩ እንዳሉት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ በየጊዜው ስለሚጨምር ማስተካከያ መደረግ የነበረበት በየሦስት ወሩ ነበር፡፡ መንግሥት ጭማሪ ሳያደርግ ከዓመት በላይ የቆየው የተፈጠረውን የኑሮ ውድነት ግንዛቤ ውስጥ በመክተት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ባላፈው አንድ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ለነዳጅ ድጎማ ብቻ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጓል፡፡ በአሰግድ ተፈራ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |