| ከወርቅ ማጭበርበር በተያያዘ... |
|
|
| Sunday, 10 February 2008 | |
|
ከወርቅ ማጭበርበር በተያያዘ ተጠርጥረው የታሰሩት ተሸለሙ
በብሄራዊ ባንክ በተፈፀመ የወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው የታሰሩት የኑር ህንፃ ባለቤት አቶ ኑረዲን መሀመድ ከፍተኛ ግብር ከፋይ ተብለው ተሸለሙ፡፡ በተሰማሩበት የአከራይ ዘርፍ ከፍተኛ ግብር ከፋይ ተብለው ጥር 27 ቀን 2000 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የምስክር ወረቀት የተሰጣቸው አቶ ኑረዲን በአዲስ አበባ መስተዳድር ከልደታ ክ/ከተማ ግብር ከፋዮች ውስጥ ከ1997 እስከ 1999 ባሳዩት የገቢ ማሳወቂያ ወቅት፣ በተሰማሩበት የንግድ ዘርፍ ከፍተኛ ግብር ከከፈሉት መካከል በ5ኛ ደረጃ አግኝተዋል፡፡ መስተዳድሩ ለተጠርጣሪው ግለሰብ በሰጠው የምስክር ወረቀት ባለሀብቱ በገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 286/94 መሰረት ለሌሎች አርአያ ሆነው እንዲቀጥሉ ጠይቋል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተከናወነው የሽልማት ዝግጅት ከየክፍለ ከተማው ከፍተኛ ግብር ለከፈሉ ግብር ከፋዮችና በ2000 በጀት ዓመት በመጀመሪያው 6 ወራት በገቢ ዕቅድ አፈፃፀማቸው የተሻለ ክንውን ላላቸው ክ/ከተሞች ሽልማት ተሰጥቷል፡፡ በእለቱ በቦታው ተገኝተው ሽልማቱን የሰጡት ከንቲባ ብርሃነ ደሬሳ ናቸው፡፡ ከወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ጥር 5 ቀን 2000 ዓ.ም በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ ኑረዲን ሽልማቱን በአካል ተገኝተው ለመውሰድ ባለመቻላቸው እርሳቸውን ወክለው ባለቤታቸው ተቀብለውላቸዋል፡፡ በብሄራዊ ባንክ ከተፈጸመ የወርቅ ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ተጠርጥረው መታሰራቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ከነዚህም መካከል በወርቅ ኤክስፖርት ስራ ተሰማርተው የሁለተኛ ደረጃ በማግኘት በውጪ ንግድ ቀን ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እጅ ሽልማት የተቀበሉት ይገኙበታል፡፡ በኃይሌ ሙሉ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |