Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version

Tuesday
Dec 02nd
Home arrow Sections arrow አገልግሎት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ...
አገልግሎት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ... E-mail
Sunday, 06 January 2008

አገልግሎት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ ስንነሳ በቴክኖሎጂው ዘመናዊነት ሳይሆን በኔትወርኩ ጥራት መተማመን አለብን

አቶ አለማየሁ ገብረዮሐንስ

የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒኬሽንስ ኮርፖሬሽን እየዘረጋ ካለው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ መካከል የገመድ አልባ ስልክ ሲ.ኤም.ዲ.ኤ /ደብሊዉ.ኤል.ኤል/ አንዱ ነው፡፡ በቅርቡ 2.4 ሚሊዮን ተገልጋዮችን ለማስተናገድ አቅም ያለው ኔትወርክ ተሰርቶ ተጠናቋል፡፡ የኘሮጀክት ማኔጀሩን አቶ አለማየሁ ገብረ ዮሐንስን አነጋግረናቸዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የሲ.ኤም.ዲ.ኤ /ደብሊዉ.ኤል.ኤል/ ኘሮጀክት ፅህፈት ቤት ያጠናቀቀው ኔትወርክ ምን ያህል ብር ፈጀ?

አቶ አለማየሁ፡- 69 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ፈጅቷል፡፡ የተጠናቀቀው ኮር ኔትወርክ 2.4 ሚሊዮን አገልግሎትን ፈላጊዎችን በሚገባ የማስተናገድ አቅም አለው፡፡ በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀው ይኸው ኘሮጀክት በመላው አገሪቱ ያለውን አገልግሎት በማዕከልነት የሚያስተናግድ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ማን ሰራው?

አቶ አለማየሁ፡- ዜድ ቲ ኢ የተባለው የቻይና ቴሌኮም ኩባንያ፤

ሪፖርተር፡- ዋናው ኔትወርክ ከተጠናቀቀ ሽያጭ ለምን አይጀመርም?

አቶ አለማየሁ፡- አሁን የገነባው አቅም ትልቅ ነው፡፡ ኃላፊነቱም ከበድ ይላል፡፡ 2.4 ሚሊዮን አልግሎት ፈላጊዎችን ለማስተናገድ ስንነሳ በቴክኖሎጂው ዘመናዊነት ብቻ ሳይሆን በኔትወርኩ ጥራት መተማመን አለብን፡፡ ሥራው እንደተጠናቀቀ ዝም ብለን ርክክብ አናደርግም፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት ኘሮጀክት ሲጠናቀቅ የአገልግሎት ሽያጭ ይደረግ ነበር፡፡ የአገልግሎቱን ጥራት ሳይጣራ አገልግሎቱ ይሸጥና ተጠቃሚው ማግኘት የሚገባውን አገልግሎት ሳያገኝ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ አግባብ አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- የአሁኑ /ዘመናዊው/ ቴክኖሎጂ ሲጠናቀቅ ርክክቡ እንዴት ይከናወናል፡፡ ከቀድሞው ጊዜ የተለየ የሚያደርገው አሠራር አለ?

አቶ አለማየሁ፡- የአዲሱ ኔትወርክ ብቃትና ጥራት ይረጋገጣል፡፡ ጥራቱ ሲረጋገጥና አቅሙ አስተማማኝ ሲሆን የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡

ሪፖርተር፡- የብቃት ማረጋገጫውን የሚሰጠው ማን ነው?

አቶ አለማየሁ፡- የተሰራው /እየተሰራ ያለው/ ኘሮጀክት ለሚሊዮኖች አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡ የሚወጣበትም ክፍያ ከፍተኛ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር አማካሪዎች ይገቡበታል፡፡ ከዚህም በላይ የቀድሞ ችግራችን የመረጃ በአግባቡ አለመያዝ . . . .

ሪፖርተር፡- ቴሌ ቀደም ሲል የመረጃ አያያዝ ችግር ነበረበት?

አቶ አለማየሁ፡- ቀደም ሲል የምንረካከበው ወንበርና ጠረጴዛ ነበር፡፡ አሁን ግን እንደዚህ ዓይነት አሠራር የለም፡፡ በእኛ ኘሮጀክት አስፈላጊው የዶክመንቴሽን ፅህፈት ቤት አለ፡፡ ሥራውን የሠራው የዜድ ቲ ኢ ኩባንያ ባይኖር፣ ሥራውን በኃላፊነትና በተለያየ ደረጃ የምንመራው ኃላፊዎች ብንቀየር ወይም ሥራ ብንለቅ አዲስ የሚመጡት ሠራተኞችም ሆነ የቴሌኮም ኩባንያ ችግር አይገጥመውም፡፡ ምክንያቱም አስፈጊው ዶክመንት አለ፡፡

አማካሪዎች የኘሮጀክቱ ሠራተኞችና ባለሙያዎች ስለኔትወርኩ በሚቀርብላቸው መረጃ መሠረት አስፈላጊውን ሁሉ ምርመራ ያካሂዳሉ፡፡ በየደረጃ ሁሉም ነገር ከታየና ኔት ወርኩ አቅም እንዳለው ሲረጋገጥ የፍተሻ ሥራ ይሰራና በቴክኒክ ክፍሉ አማካይነት ሰርተፊኬት ይሰጣል፡፡

ሪፖርተር፡- ኔት ወርኩ ተጠናቆ ሥራ ያልጀመረው ለምንድን ነው?

አቶ አለማየሁ፡- ጥንቃቄ የተሞላበት የጥራት ማረጋገጥ ሥራ ለመሥራትና የሙከራ ሥራ እስኪጠናቀቅ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ሽያጭ ሲጀመር በገበያ ላይ የሚውለው አገልግሎት ቢዘረዝሩልኝ፤

አቶ አለማየሁ፡- የስልክ፣ የፋክስ፣ የኢንተርኔት፣ የጐታ፣ የኤስኤም ኤስ /የአጭር የፅሁፍ መልዕክት/፣ አካባቢን በፅሁፍና በምልክት የሚጠቁም አገልግሎት ሎኬሽን ቤዝድ ሲስተም /ኤል.ቢ.ሲ/ ፣ የገመድ አልባ የሕዝብ ስልክና የክፍያ አገልግሎት ማመቻቸትን ያጠቃልላል፡፡

ሪፖርተር፡- የጐታና የኤል ቢ ሲ አገልግሎት ቢያብራሩልን?

አቶ አለማየሁ፡- እንደ ፑሽ ቶክ አይነት ነው፡፡ በቡድን ለሚሠራ ሥራ አጋዥ ነው፡፡ እንደ ሬዲዮ መገናኛ ዓይነት ሲሆን የራሱ ቀፎ አለው፡፡ በተለይ ለመከላከያና ለፖሊስ ሠራዊት፣ ለእሳት አደጋ፣ ለትራንስፖርት ስምሪት፣ ለኮንስትራክሽን ሰራተኞች ወዘተ. ያገለግላል፡፡

ኤል ቢ ሲ /ሎኬሽን ቤዝድ ሲስተም/ በቅርቡ እንሰጠዋለን ከምንለው አገልግሎቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ አገልግሎቱን የገዛ ደንበኛ ቢጠፋ /ቢሰወር/ የት እንዳለ ማወቅ ይቻላል፡፡ ቴክኖሎጂው ደንበኛው ያለበትን ቦታ በፅሁፍና በምልክት ይጠቁማል፡፡

ሪፖርተር፡-ክፍያው እንዴት ነው?

አቶ አለማየሁ፡- የኮርፖሬሽኑ የበላይ ኃላፊዎች ሲወስኑት ይፋ የሚሆን ነው፡፡ ዝርዝር የዋጋውን መጠን መናገር ባይቻልም ከአካባቢያችንም ሆነ ባጠቃላይ በአፍሪካ ካሉ ሀገሮች ይቀንሳል፡፡

ሪፖርተር፡- የገመድ አልባ ስልክ ሽያጭ እንዴት ይከናወናል?

አቶ አለማየሁ፡- ሽያጩ የሚካሄደው በሲም ካርድ ነው፡፡ የሲም ካርዱ ናሙና መጥቶ ሙከራ ተደርጓል፡፡ ክፍያው የሚከናወነው በቅድሚያና በድህረ ክፍያ ስርዓት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ገመድ አልባና ባለመስመር ስልክ ተመሳሳይ አገልግሎት ከሰጡ በዋጋ ደረጃ ሊለያዩ ይችላሉ?

አቶ አለማየሁ፡- እንደ ባለመስመር ስልክ ዓይነት አገልግሎት ከሰጠ የዋጋ ለውጥ ሊኖር አይችልም፡፡ ገመድ አልባ ስልክ ልዩ የሚያደርገው በርካታ ጉዳዮች ስላሉት በጥቅሉ እንጂ በዝርዝር ለማቅረብ ጊዜው አይደለም፡፡

ሪፖርተር፡- ሽያጩ በቅርቡ ይጀመራል ብለው ነበር?

አቶ አለማየሁ፡- በቅርብ ቀን ይጀመራል፡፡ በዛ ቢባል አንድ ወር ቢቆይ ነው፡፡ በቅርቡ አገራችን ከሚደረገው የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ በፊት ይደርሳል፡፡

ሪፖርተር፡- ገመድ አልባ ስልክን እንደሞባይል መጠቀም ይቻላል፡፡ ይህንን አገልግሎት ለመሸጥ ቴሌ በተለይ የሰራው ሥራ አለ?

አቶ አለማየሁ፡- የገመድ አልባ ስልክ ቴክኖሎጂ ሞባይል የሚሰራውን አገልግሎት መስጠት ይችላል፡፡ በተለይም በዳታ ማስተላለፍና በታሪፍ ከሞባይል የበለጠ አገልግሎት ፈላጊውን ያረካል፡፡ ገመድ አልባ ስልክ ግማሽ ሞባይል፣ ግማሽ ባለመስመር፣ ወይም በተፈለገው መጠን የተለያዩ አገልግሎቶችን ከፋፍሎ መስጠት ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- አገልግሎቱ የሚወሰነው እንዴት ነው?

አቶ አለማየሁ፡- ደንበኞች በሚጠይቁት በፍላጐታቸው መሠረት አገልግሎት ይመቻችላቸዋል፡፡ የእኛ ድርሻ ቴክኖሎጂውን አመቻችቶ ማዘጋጀት ነው፡፡ ይህንን አዘጋጅተን ጨርሰናል፡፡ የሚቀረው ወደ ሽያጭ መግባትና ለደንበኞች አገልግሎቶቹን ማስተዋወቅ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- እንዴት ነው የምታዳርሱት?

አቶ አለማየሁ፡- በመጀመሪያው ምዕራፍ 625..000 ደንበኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 250..000 የሚሆነው ለአዲስ አበባ የተያዘ ኮታ ሲሆን ቀሪው 375..000 የሚሆነው ለሰላሳ ስምንት የክልልና የአስተዳደር ከተሞች የሚዳረስ ይሆናል፡፡ ሥራው ሲጠናቀቅ 2.4 ሚሊዮን ደንበኞች አስቀድመው የተጠቀሱትን አገልግሎትች ያገኛሉ፡፡

ሪፖርተር፡- በክልል ከተሞች አስፈላጊውን አቅም ፈጥራችኋል?

አቶ አለማየሁ፡- የቴክኖሎጂ መደጋገፍ አለ፡፡ ዋናው መቆጣጠሪያው ኮር ኔትወርክ ሴንተሩ ነው፡፡ ይህም ሆኖ አሁን የቴክኒክ መቆጣጠሪያ ሴንተሩ በሚገባ ተገንብቶ አልቋል፡፡ መሳሪያዎችም ተሟልተዋል፡፡ ቀደም ሲል የነበረብን የቢሮ መጨናነቅም ተወግዷል፡፡ በቅርቡ በሰለጠነ የሰው ኃይል በመታገዝ ወደ ሥራው እንገባለን፡፡ ኮርፖሬሽኑ በባለሙያዎችን በሰው ኃይል ያለውን እጥረት ለማስወገድ እየሰራ ነው፡፡ የስልጠና ዝግጅትና መሳሪያዎች እያሟላ ነው፡፡ የወደፊቱ አዲሱ ቴሌ እየመጣ ይመስለኛል፡፡

ሪፖርተር፡- በክልል ከተሞች ሽያጭ ለመጀመር ኘሮጀክቱ ከሠራው ድርጅት ጋር የምትሰሩት ሥራ አለ?

አቶ አለማየሁ፡- በያዝነው ኮታ መሠረት የመጀመሪያ ምዕራፍ ሽያጭ ለማካሄድ ሁለት መሟላት ያለባቸው ነገሮች አሉ፡፡ በቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን በኩል የመጨረሻ የዲዛይን ሥራ መሠራት አለበት፡፡ በመቀጠል ከኮርፖሬሽኑ ጋር በቬንደር ፋይናንስ ሰፊ ውል ገብቶ የተለያዩ የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመገንባት ላይ ያለው ዜድ ቲ ኢ ለተዘጋጀው ዲዛይን የሚሆኑ እቃዎችን አምርቶ፣ ማቅረብና አገር ውስጥ ማስገባት ከዚያም ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡ ባለኝ መረጃ መሠረት ኮርፖሬሽኑ የዲዛይኑን ሥራ አጠናቋል፡፡ የሚቀረው የማጓጓዝ ሥራ ብቻ ይሆናል፡፡

ሪፖርተር፡- ኘሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ይጠናቀቃሉ፡፡ ምክንያቱ ምንድነው?

አቶ አለማየሁ፡- በአሁኑ ሰዓት በሁሉም በኩል ከፍተኛ የሥራ መንፈስ ያለ ይመስለኛል፡፡ በእኛ ኘሮጀክት ውስጥ ያለው የሥራ መንፈስና ፍላጐት ለውጥ ለማምጣት ነው፡፡ ሁሉም ሰራተኛ በአግባቡ ይሰራል፡፡ ስለማንሰራ ነው ወደ ኋላ የቀረነው፡፡ መሥራት አለብን፡፡ ከሰራን እንለወጣለን፡፡ በአጭር ጊዜ ኘሮጀክቶች እየተጠናቀቁ ነው፡፡ ለዓመታት ያልነበሩ የአገልግሎት ዓይነቶች በብዛትም ሆነ በጥራት እየተስፋፉ ናቸው፡፡ በአጭር ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞችን ለማገልገል መቻል የሥራ ውጤት ነው፡፡ ቴሌ አሁን በጥሩ የሥራ መንፈስ ውስጥ ይገኛል፡፡

< Prev