| የፒካሶ የሥዕል ሥራዎች ተዘረፉ |
|
|
| Sunday, 10 February 2008 | |
|
በሚሊዮን የሚቆጠር ዩሮ ሊያወጡ የሚችሉ ሁለት የፓብሎ ፒካሶ የሥዕል ሥራዎች ከስዊዝ ኤግዚቢሽን መሰረቃቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ቅቦች የተሰረቁት በዙሪክ አቅራቢያ በሚገኘው ትንሹ የፓፍልኮን ከተማ የአርቲስቶች ሥራዎች ታይተው ዝግጅቱ ካበቃና ከተዘጋ በኋላ ነው፡፡ የፒካሶ ሥራዎች የሆኑት የዘይት ቅቦች፣ የፈረስ ጭንቅላትና ብርጭቆ እንዲሁም ከሸክላ የተሠራ የውሃ መያዣ ለኤግዚቢሽኑ የቀረቡት ጀርመን ከሚገኘው ስፕሪንግል ሙዚየም በትውስት መጥተው ነበር፡፡ የሙዚየሙ ኃላፊዎች የተሰረቁት የፒካሶ ሥራዎች የሚያወጡትን ትክክለኛ ዋጋ ከመግለፅ ተቆጥቧል፡፡ ፖሊስ በበኩሉ የሌቦቹን ማንነት ለማወቅ ክትትሉን ቀጥሏል፡፡ በመርማሪ ፖሊሶች ጥርጣሬ እቃው ሊሰረቅ የቻለው ሌቦቹ ሙዚየሙ ከመዘጋቱ በፊት ራሳቸውን በሙዚየሙ ውስጥ ደብቀው ነው፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |