Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow በሶማሊያ ለተገደሉት ስደተኛ...
በሶማሊያ ለተገደሉት ስደተኛ... Print E-mail
Sunday, 10 February 2008
በሶማሊያ ለተገደሉት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን ኃላፊነት መውሰዱን አልሻባብ አስታወቀ

በሰሜናዊ ሶማሊያ ወደብ ባለፈው ሀሙስ 20 ኢትዮጵያዊያንን ለገደለውን የቦምብ ጥቃት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው የሚባለው እስላማዊ ወታደራዊ ክንፍ ኃላፊነቱን እንደሚወስድ ማስታወቁን ሮይተር ዘገበ፡፡
የአካባቢው ባለሥልጣናት እንደሚሉት ደግሞ ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ምሽት በቦሳሶ ወደብ 1ዐዐ ሰዎችን ያቆሰለውን ፍንዳታ ያደረሰው አልሸባብ የሚባለው ወታደራዊ ኃይል ነው ብለዋል፤ በአካባቢው ኢትዮጵያውያን ይበዛሉ፡፡

የኢትዮጵያ ጦር ከእስላማዊ ኃይሎች ሽምቅ ተዋጊዎች ጋር የሚዋጋውን የሶማሊያን የሽግግር መንግሥት በመርዳት ላይ ሲሆን አማፅያኑ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የእስላማዊ ሶማሊያና የክርስቲያን ጐረቤት ሀገር ኢትዮጵያን ልዩነት ለመጠቀም ይጥራሉ፡፡ ጥቃቱ የተፈፀመው በግማሽ ነፃ ግዛት ከሆነችው ሰሜናዊ ፑንት ላንድ ግዛት ሲሆን አካባቢው በአንፃራዊ ሰላማዊ ቦታ ሲሆን የኘሬዚዳንት አብዱላሂ ዩሱፍ እና ደጋፊዎቹ መምሪያ ነው፡፡

ሮይተር የአልሸባብን ድረ ገፅ ጠቅሶ እንደዘገበው ጥቃቱ የኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ ኢላማ ያደረገ ሲሆን የወታደሮቹ ልጆችና ሚስቶች ተገድለዋል፡፡

"ይህ የረጅም ጊዜ ጠላታችን የሆኑት ኢትዮጵያውያን ለተቀበለችውና የፑንትላንድ አስተዳደር የምናስተላልፈው መልዕክት ነው" ብሏል አልሸባብ፡፡

የፑንትላንድ ባሪ ግዛት አስተዳዳሪ ሙሴ ዩሱፍ ጌሌ፣ የአልሸባብ ወታደራዊ ሀይል ለቦንብ ጥቃቱ ተጠያቂ እንደሆነና ነገር ግን ኢላማውን መሳቱን ፖሊስ ማረጋገጡን ገልፀናል፡፡

"የጥቃቱ ሰለባዎች እንደታሰበው ኢትዮጵያዊያን ወታደሮች አልነበሩም፡፡ ወደ የመን ለመሻገር የሚሞክሩና የእለት እንጀራቸውን እዚህ ፑንት ላንድ ለማግኘት የሚጥሩ ድሀ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንጂ" በማለት ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡

ብዙ ኢትዮጵያውያን በቦሳሶ ወደብ በኩል ወደ የመን ለመሻገር ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሶማሊያዊያንና ኢትዮጵያዊያን በጀልባ ባህሩን ለማቋረጥ ሲሞከሩ ህይወታቸውን ያጣሉ፡፡ በብዙ አጋጣሚ ጀልባው ይሰምጣል፡፡

እ.ኤ.አ በ2ዐዐ6 አጋማሽ ሞቃድሾን ተቆጣጥሮ የነበረው የአልሸባብ ወታደራዊ እስላማዊ ሀይል ሶማሊያን በኢትዮጵያ ወታደሮች ተሸንፎ እስኪባረር ድረስ በእስላማዊ ሼሪአ ህግ ስር እንድትውል አድርጎ ነበር፡፡

"አልሸባብ በፑንት ላንድ ሰላም እንዳይኖር ሀሳብ ቢኖረውም ይህ አይሳካም" ብለዋል ጌሌ፡፡

ፑንትላንድ ከኢትዮጵያና ከአሜሪካ ድጋፍ ታገኛለች፡፡ የደህንነት በባለሥልጣናቱ አልሸባብን የእርዳታ ሰራተኞችን ገድሏል በማለት እየወነጀሉት ነው፡፡ የንፁሀን ዜጎችን ሞት፣ የቦንብ ጥቃት፣ የህፃናት ጭፍጨፋ የፖሊስ ጣቢያ ጥቃት እንዳቀናበረ የሚነገርለት ሰሆን ባለፈው ዓመት ብቻ በሶማሊያ ብቻ 6,500 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን 600,000 ከሞቃድሾ ተሰደዋል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >