Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow የኮሜሳ አገራት የኤሌክትሪክአቅም በ8በመቶ ያድጋ
የኮሜሳ አገራት የኤሌክትሪክአቅም በ8በመቶ ያድጋ Print E-mail
Sunday, 10 February 2008
በኢትዮጵያ ሱዳን እየተካሄደ ያለው ኘሮጀክት በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ አገራት መካከል ያለውን የ31"000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ አቅም በስምንት በመቶ እንደሚያሳድገው ተጠቆመ፡፡
የኬንያው ቢዝነስ ዴይሊ ዘገባ እንደሚያመለክተው የአካባቢ አገራቱ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦትና መሠረተ ልማትን በማሻሻል ለሚኖረው አስተዋፅኦ 1 ቢሊዮን ሽልንግ (14.7 ሚሊዮን ዶላር) በላይ ለመስጠት አቅዷል፡፡

ኘሮጀክቱ በአስራ ዘጠኝ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ አገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) በኢኮኖሚያቸው የሚኖረው የኃይል አቅርቦት ለማረጋገጥ ያቀደ መሆኑም ተገልጿል፡፡

የኮሜሳ ዋና ሴክሬታሪ ኢራስቱስ ሙዋንቻ እንዳሉት ኘሮግራሙ አባል አገራቱ በጋራ ልማት እንዲሳተፉና ሁሉም ዜጋ በተመጣጣኝ ዋጋ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኝ ያግዛል፡፡

በኬንያና ኢትዮጵያ 1"875 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም የሚፈጥር ጥናት መጠናቱን ጠቁመው ይህ ኬንያ አሁን ካላት 4ዐዐ ሜጋ ዋት በ4ዐ እጥፍ እንደሚበልጥ ተጠቁሟል፡፡ ሥራው በመጪው ሚያዚያ በሞያሌ አካባቢ እንደሚጀመርም ተገልጿል፡፡
 
የምስራቅ አፍሪካ ፓወር ፑል በኮሜሳ ኘሮጀክት ሥራ ሰባት አገሮችን ለማገናኘት ማቀዱ ተገልጿል፡፡ ዋና ፀሐፊው እንዳሉትም የኃይል ኘሮጀክቱ በመንግሥትና የግል ባለሐብቶች የጋራ ትብብር ይሰራል፡፡ ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ከምትገነባቸው ሦስት የኃይል ማመንጫ ግድቦች በ2ዐ1ዐ ከ1155 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም ሲኖራት ሱዳን መራዊ በምትገነባው የውኃ ኃይል ግድብ እስከ 2ዐዐ8 መጨረሻ 125ዐ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡

የኃይል ማገናኛው በዛምቢያ፣ ታንዛኒያና ኬንያ፣ ኬንያና ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ ጅቡቲ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን እየተካሄደ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
 
< Prev   Next >