| ባለሥልጣኑ ከ107 ሚሊዮን ብር በላይ... |
|
|
| Sunday, 10 February 2008 | |
|
ባለሥልጣኑ ከ107 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ
የፌዴራል አገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የመቀሌ ቅርንጫፍ ከተጨማሪ እሴት ታክስና ከሌሎች የገቢ ምንጮች 107 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ፡፡ የተሰበሰበው ገቢ ከአምናው ተመሣሣይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ21 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ ብልጫ ያለው ሲሆን፣ በተለይም የግብር ከፋዮች የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ በመክፈል የጀመሩት ጥረት አበረታች መሆኑን፣ በክልሉ ከተሰበሰበው ገቢ 77 በመቶ ከተጨማሪ እሴት ታክስ መገኘቱን፣ ግብር ለመክፈል የሚያንገራግሩ ነጋዴዎች አገራዊ ግዴታቸውን አውቀው ከመንግሥት ጋር እንዲተባበሩ ተገል..ል፡፡ (ዋልታ) ለአምስት ዞኖች ከ200ሺ ኩንታል በላይ የምግብ እህል ተከፋፈለ በሶማሌ ክልል ባለፉት ሦስት ወራት ዝናብ አጠር በሆኑ አምስት ዞኖች ለሚገኙ ተረጂዎች ከ200ሺ ኩንታል በላይ የምግብ እህል በእርዳታ ማከፋፈሉን የክልሉ አደጋ መከላከልና ዝግጁነት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ካለፈው ጥቅምት ጀምሮ ለተረጂዎች እርዳታው የተከፋፈለው በፊቅ፣ ደጋሀቡር፣ ሞርዴር፣ ቆራ ሄና፣ ጎዴ ዞኖች በተለያዩ ምክንያቶች ለምግብ እህል እጥረት ለተጋለጡ 641 ሺ 970 ወገኖች መሆኑን፣ ፌዴራል መንግሥትና ከዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች የተገኘው 214ሺ 694 ኩንታል እህል ከማዕከላዊ መጋዘን (ድሬዳዋ) እና በ186 ማከፋፈያ ጣቢያዎች አማካኝነት መሆኑ ተገል..ል፡፡ (ዋልታ) የሥጋ ደዌ ተጠቂዎችን ለመታደግ በርካታ ፕሮጄክቶች እየተሰሩ ነው በኢትዮጵያ የሥጋ ደዌ ተጠቂዎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ደረጃ በደረጃ ለማቃለል ከመንግሥትና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በተገኘ ሁለት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር የሚበልጥ በጀት የተለያዩ ፕሮጄክቶች በመከናወን ላይ መሆናቸው የብሄራዊ ማህበሩ ፕሬዚዳንት አስታወቁ፡፡ ተጠቂዎቹ በሽታው ከሚያደርስባቸው ስቀይ በተጨማሪ ከፍተኛ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር እየደረሰባቸው መሆኑን፣ ችግሮቹን ለመፍታት ብሄራዊ ማህበሩ ከተለያዩ ፕሮጄክቶን ቀርፆ ሥራ ላይ እያዋለ መሆኑ ታውቋል፡፡ (ኢዜአ) ከ155ሺ ኩንታል በላይ የበርበሬ ምርት ተሰበሰበ በሀዲያ ዞን በዘንድሮው የምርት ዘመን ከ155ሺ ኩንታል በላይ የበርበሬ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡ ምርቱ የተሰበሰበው በምርት ዘመኑ ታርሶ በበርበሬ ተክል ከለማው ከስር ሺህ ሄክታር መሬት ላይ መሆኑን፣ ካለፈው ዓመት የምርት ዘመን ጋር ሲነፃፀር 34 በመቶ ብልጫ እንዳለው፣ የተሻለ ሲሰበሰብ የተቻለው የበርበሬ ዋጋ በመጨመሩ አርሶ አደሩ ተክሉን በስፋት በማልማቱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ (አዲስ ዘመን ጥር 30 ቀን 2000 ዓ.ም) የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ሊሰጥ ነው ከቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ተመራቂ ተማሪዎች ከሚቀጥለው ነሐሴ ወር ጀምሮ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና እንደሚሰጣቸው የአቅም ግንባታ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የመጀመሪያው የሙያ ማረጋገጫ ፈተና በስድስት የሙያ ዘርፎች ለሰለጠኑ 200 ተማሪዎች ይሰጣል፡፡ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ፕሮግራሙ ዓላማ ለገበያ ብቁ የሆኑ ባለሙያዎች ብቃት ለማበልፀግና ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ለማሸጋገር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን፣ በአዲሱ የአሰራር መመሪያ መሠረት ተማሪዎች ከሁለት ዓመት የሥራ ልምድ በተጨማሪ ሚኒስቴሩን የሚሰጣቸውን የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ማለፍ እንደሚጠበቅባቸው ገል..ል፡፡ (ኢዜአ) |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |