Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 20th
Home arrow Sections arrow ሚኒስትሩ በነዳጅ ላይ ከዚህ በላይ...
ሚኒስትሩ በነዳጅ ላይ ከዚህ በላይ... Print E-mail
Sunday, 10 February 2008
Image
አቶ ግርማ ብሩ
ሚኒስትሩ በነዳጅ ላይ ከዚህ በላይ ከመንግስት ድጎማ መጠበቅ ፍትሃዊ አይደለም አሉ


የነዳጅ ዋጋ መጨመር በኅብረተሰቡ ኑሮ ላይ ጫና እንዳይፈጥር ድጎማ ቢሰጥም አሁን የተከሰተውን የነዳጅ ዋጋ ሊያረጋጋ የሚችል ድጎማ መስጠት ሌሎች ዘርፎች ላይ ጫና ስለሚፈጥር ከዚህ በላይ ድጎማ መስጠት ፍትሃዊ አለመሆኑ ተገለፀ፡፡ የአለም የነዳጅ ዋጋ ከቀነሰ ማስተካከያ ይደረጋል፡፡
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ ግርማ ብሩ በአምስት ዓመቱ የዘላቂ ልማትና ድህነት ማስወገድ ፕሮግራም መደረስ ያለባቸውን ግቦችና እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ዙሪያ ባለፈው ሐሙስ ጥር 29 ቀን 2000 ዓ.ም በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ ለነዳጅና ሌሎች የኢንዱስትሪ ምርቶች ዋጋ ላይ እርምጃ በመውሰድ ማረጋጋት አንዱ ፕሮግራም ነው፡፡ ሌሎች ልዩ ትርጉም ያላቸው ዘርፎች ሳይደጎሙ ነዳጅን መደጎም የገቢ መጠናቸው ዝቅተኛ የሆነ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለማገዝ ቢሆንም አሁን በአለም ካለው የነዳጅ ዋጋ አንፃር ጭማሪውን ወደ ኅብረተሰቡ ማውረድ ግድ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ የነዳጅ ዋጋው ከሌሎች አገሮች አንፃር ፍትሃዊ መሆኑን የተናገሩት ሚኒስትሩ በጭማሪው የሚኖረው ዋጋ ከአብዛኛዎቹ አገሮች ዋጋ በግማሽ ያነሰ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በዓመት ከ2.2 ቢሊዮን ሊትር ነዳጅ ከውጪ የሚገባ ሲሆን 58 በመቶ ነጭ ናፍጣ፣ 14 እስከ 15 በመቶ ኬሮሲን፣ 10.2 በመቶ ጄት ፊውልና ቀሪው ቤንዚን ሲሆን አሁን ባለው ዋጋ ነጭ ናፍጣ ጅቡቲ ሲመጣ ከሚኖረው 8.47 ብር በመቀነስ በ6.90 እንደሚሸጥ፣ ኬሮሲን 8.69 ሆኖ 5.72 እንደሚሸጥ ጠቁመው ይህ በነዳጅ ዋጋ ድጎማ ከሚደጉሙ አገሮች አንፃር አናሳ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዘላቂ ልማትና ድህነት ማስወገድ ፕሮግራም ኢንዱስትሪውን በአጠቃላይ በ9 በመቶ ማደግ እንዳለበት የተጣለው ግብ በ1998 በ10.2 በመቶ፣ በ1999 በ11 በመቶና በ2000 እስከ አሁን በተመዘገበው የ12 በመቶ እድገት እንደሚኖር ገልፀዋል፡፡

ለአገሪቱ ልማትና ለአጠቃላይ የአገሪቱ እድገት አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል ከተባሉት ከኢንዱስትሪ ዘርፎች የባለሃብቶች በጊዜ ወደ ሥራ አለመግባትና የግብይት ችግር እንዳለ ተጠቁሟል፡፡

በፕሮግራሙ ለቆዳ ኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ በሆነው የጫማ ኢንዱስትሪ በ2002 በቀን ከ60 እስከ 70ሺ ጥንድ ጫማዎች በማምረት በአመት ከ25 ሚሊዮን ጫማ ለውጭ ገበያ የማቅረብና የቆዳ ማልፊያና ማለስለሻ ፋብሪካዎችን የማለስለስ አቅም በማሻሻል ሙሉ በሙሉ ወዳለቀ ደረጃ ማድረስ መሆኑን ጠቁመው እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2000 በአጠቃላይ በቀን 24"000 ጫማዎችን የማምረት አቅም መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡ የሌጦ ማለስለስና የመንከር አቅም በቀን 124"700 መድረሱን ጠቁመዋል፡፡

በጨርቃጨርቅና አልባሳት ዘርፍ ብዙ አቅም እያለ ብዙ ያልተሰራበት ዘርፍ መሆኑን፣ በዘርፉ በዓለም ገበያ ላይ ተወዳዳሪ የሆነ አቅም እንዲገነቡ የሠራተኛውን ምርታማነትና በፋብሪካዎች አመራር በማስተካከል በኩል ሰፊ ጥረት እንደሚጠይቅ አስታውቀዋል፡፡

በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት በ2002 ማብቂያ ከዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ወደ 500 ሚሊዮን ዶላር ለማድረስ 191 ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ መታቀዱን ገልፀው በመንግሥት ሥር የነበሩትን ድርጅቶች የተሻለ ምርታማና ተወዳዳሪ በማድረግ በኪራይ፣ በሽያጭ ወደሚሸጋገሩበት ዙሪያ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በቀሪው የፕሮግራም ዘመን በመንግሥት ሥር የሚገኙት ፋብሪካዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ግል እንደሚዞሩም ተናግረዋል፡፡ በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ተግባራዊ እየሆኑ ያሉ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች በአለም ገና ያለው ፋብሪካ በመስከረም 2001 ሲጠናቀቅ 80 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ምርት ወደ ውጪ የመላክ አቅም እንደሚኖረውና በመቀሌና በአድዋ ላይ የሚቋቋሙት ፋብሪካዎች እስከሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ እንደሚጠናቀቁ ተናግረዋል፡፡

መንግሥት እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2000 ዓ.ም በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ለተሰማሩ ባለሃብቶች 3,254.9 ሔክታር መሬት ማከፋፈሉን ጠቁመዋል፡፡

በአበባ እስከ 2002 ድረስ 2000 ሔክታር መሬትን "በግሪን ሐውስ" የማልበስ እቅድ መያዙንና ባለሃብቶች የተሰጣቸውን መሬት በፍጥነት ወደ ልማት ማዛወር እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2000 ዓ.ም ባለው ፕሮግራም 1239 ሔክታር መሬት በአበባ የመሸፈን አቅም እንደሚኖርም ተናግረዋል፡፡

በአትክልትና ፍራፍሬ በመንግስት ይዞታ ሥር ያሉ መሬቶችን ወደ ግል ለማዛወር እየተሰራ ሲሆን በዝዋይ 450 ሔክታር መሬት፣ በወይን ልማት እንዲውል ለባለሃብት መስጠቱን ተናግረዋል፡፡ በላይኛው አዋሽ አካባቢ የሚገኘውንም 15"000 ሔክታር መሬት ለአገር ውስጥና ለውጭ ባለሃብቶች እንዲወስዱ ቢዝነስ ፕላን አቅርበው በመደራደር ላይ መሆናቸውንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

የሲሚንቶ ፍላጎት በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱ ተከትሎ በ1998 ከነበረው የ1.6 ሚሊዮን ቶን አመታዊ የሲሚንቶ ፍላጎት ወደ 4.7 ሚሊዮን ቶን ለማድረስ መታቀዱን ጠቁመው እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2000 ዓ.ም 22 ፕሮጀክቶች፣ ሶስቱ የነበረውን በማስፋፋት፣ 19 አዳዲስ ፋብሪካዎችን ለማቋቋም ፈቃድ ወስደው 13ቱ በግንባታ ሂደት ላይ ሲሆኑ በ2000 በጀት ዓመት መጨረሻ 767 ሺህ ቶን በአዲስ የማምረት አቅም እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ እስከ 2001 መጨረሻ የ13 ፋብሪካዎች ሥራ ሲጠናቀቅ ከ3.2 ሚሊዮን ቶን ለማምረት መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡

በ2 ቢሊዮን ብር በጀት ለስኳር ልማት ማስፈፀሚያ የሚውሉ 2.5 ሚሊዮን ሜትሪክ ኪዩብ የሚይዙ ግቦች በተንዳሆና ቀሰም አካባቢዎች መገንባታቸውንና ያሉትን ፋብሪካዎች አቅም በማስፋፋትና አዲስ በሚቋቋመው ፋብሪካ 35ሺህ ቶን የነበረውን የስኳር አቅርቦት ወደ 1.5 ሚሊዮን ቶን የማድረስ አቅም እንደሚኖር ገልፀዋል፡፡ ከዚህም የውጭ ምንዛሬ የመፍጠር አቅም ለማሳደግና ከተረፈ ምርቱም 143 ሚሊዮን ሊትር ኢታኖል ለማምረት መታቀዱ ተጠቁሟል፡፡ የሁለቱ ግድቦች በመጪው መኸር ዝናብ የመቋጠር አቅም እንደሚኖራቸው አቶ ግርማ ገልፀዋል፡፡

የብረታ ብረት፣ ኢንጂነሪንግ፣ በኬሚካል ኢንዱስትሪ፣ በመድሃኒት ፋብሪካ፣ በጎማ ዛፍ፣ በኢንዱስትሪ ልማት ውስጥ በሚኖራቸው ድርሻ መሰረት ስትራቴጂ ጥናት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከውጪ ንግድ ከሚገኘው ገቢ የኢንዱስትሪ ምርቶች ድርሻ ከ20 እስከ 25 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን ጠቁመው በ1998 በ37 በመቶ፣ በ1999 በ20 በመቶና በ2000 ዓ.ም ስድስት ወራት በ27 በመቶ መጨመሩን ጠቁመዋል፡፡

ከአለም የንግድ ድርጅትና የአውሮፓ ማኅበረሰብ ጋር በሚደረገው ድርድር ለአለም የንግድ ድርጅት አባልነት ድርድር ለማድረግ የሚያስፈልግ ቅድመ ዝግጅት በተለይ አባል አገሮች ስለ አገሪቱ የንግድ እንቅስቃሴ ሥርዓት እንዲያውቁ የሚያስችላቸውን ሰነድ መቅረቡን በዚሁ መሠረትም ሁለት አገራት ጥያቄ መላካቸውን ተናግረዋል፡፡ ጎን ለጎን የአለም የንግድ ድርጅት አባል በመሆን በሚደረገው ድርድር ከልማት ስትራቴጂው አንፃር ፈታኝ ሊሆኑ በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ጥናት እየተደረገ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡    

የኢኮኖሚ አጋርነት ስምምነትን በሚመለከት የምንደራደረው ከምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ አገሮች ጋር በጋራ ስለሆነ በድርድሩ ልማትና እድገት ላይ በጋራ እየሰራች መሆኗንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡

በቤዛዊት ስዩም
 
< Prev   Next >