Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow "ብሔራዊ ራዕይ አስቀምጠን...
"ብሔራዊ ራዕይ አስቀምጠን... Print E-mail
Sunday, 10 February 2008
Image
አቶ ፍቅሬ ኃ/መስቀል
"ብሔራዊ ራዕይ አስቀምጠን ካልሠራን ልማት ሊመጣ አይችልም"

አቶ ፍቅሬ ኃ/መስቀል
የኤፍ.ኬ.ኖርዌይ የአፍሪካ ተወካይ
    
አቶ ፍቅሬ ኃይለ መስቀል የተወለዱት (በቀድሞው አጠራር) በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ሂርና ከተማ ነው፡፡ አንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አሰበ ተፈሪ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐረር መድኃኒዓለም ትምህርት ቤት ተከታትለዋል፡፡
በቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዩኒቨርሲቲን በቢዝነስ አስተዳደር ከተመረቁ በኋላ፣ ቀጥለው ወደ ጣሊያን ሀገር አምርተው በኢኮኖሚክስ የማስተርስ ዲግሪ ተቀብለዋል፡፡ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢንስፔክተርነት በ1959 ዓ.ም. ጀምረው እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅነት ደርሰዋል፡፡ ከአንድ ዓመት በላይ ተወካይ ዋና ሥራ አስኪያጅም ነበሩ፡፡ በየደረጃው የክፍሎችና ዋና ክፍሎች ኃላፊም በመሆን ሠርተዋል፡፡

በመቀጠል የተቀላቀሉት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ማኔጀር ሆነው ሲሰሩ ድርጅቱ ለኡጋንዳ ቢሮው ዓለም አቀፍ ሠራተኛ ለመቅጠር ማስታወቂያ ሲያወጣ ተወዳድረው ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኑ፡፡ በኡጋንዳ በመስራት ላይ ያሉትን ሥራ እንዴት እንደተቀላቀሉና ለኢትዮጵያም እያደረጉት ስላለው የልማት አስተዋፅኦ አውግተውናል፡፡

አምስት ዓመት ተኩል ሰርተው፣ የዛሬ ሰባት ዓመት ጨርሰው ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት ሲወስኑ የኖርዌይ መንግሥት የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ያቋቋመው ፣ፍሬድስኮኘሴ ' የተሰኘ ተቋም በአፍሪካ ፅህፈት ቤቱን ለማቋቋም እንዳሰበ ሰሙ፡፡ ተቋሙ በአፍሪካ ፅህፈት ቤቱን ለማድረግ ያሰበው በኡጋንዳ ስለነበርም የድርጅቱ ተወካይ ሆነው እንዲቀጥሉ በቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት ቀጠሉ፡፡

፣ፍሬድስኮኘሴ፣ በ2000 እ.ኤ.አ የተቋቋመ ሲሆን በአፍሪካ የራሱ ድርጅት የለውም፡፡ አቶ ፍቅሬ የራሳቸውን ድርጅት አቋቁመው ድርጅቱ ለሳቸው ድርጅት ውክልና ሰጥቶ ነው ሥራው የሚከናወነው፡፡

የፍሬድስኮኘሴ ዋና ተግባር የኖርዌይ መንግሥት ለታዳጊ ሀገሮች የሚሰጠው እርዳታ አንድ አካል ሆኖ የሀገራቱን ልማት ማፋጠን ነው፡፡ የእርዳታው ዓይነት የሰው ኃይል ልማት (ሂውማን ሪሶርስ ዴቨሎኘመንት) ሲሆን ተመሳሳይ የሆነ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች (በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ያሉ) የባለሙያ ልውውጥ እንዲያደርጉ ማስቻል ነው፡፡ በልውውጡ የሚሳተፉ ባለሙያዎች በሚሄዱበት ሀገር ያለውን ዕውቀት ይቀስማሉ፣ ያላቸውን ያካፍላሉ፡፡ ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ ለላካቸው ድርጅት ዕውቀታቸውን/አዳዲስ አሰራሮችን ያስተላልፋሉ፡፡

በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ በድርጅቱ ድጋፍ በሚደረገው ልውውጥ ዘርፍ ከሚሳተፉት ሕክምና፣ ጋዜጠኝነት (በመገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማኀበርና በኢትዮጵያ አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰሩ ጋዜጠኞች ማኀበር የሚሳተፉበት"፣ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር፣ በህፃናት ላይ የሚሰሩ ተቋማት ዋና ዋና ናቸው፡፡ ተሳታፊ ድርጅቶቹ አስራ ሦስት ናቸው፡፡

ወደፊት አቅጣጫውን በሦስት ዘርፎች ማለትም በሥርዓተ ፆታ፣ አካባቢ ጥበቃ እና ሰላምና መረጋጋት ላይ ያተኮረ እንዲሆን ይፈልጋሉ፡፡ በአፍሪካ ከ24 በላይ ኔትወርኮች በተመሳሳይ ዓላማ ላይ የሚሰሩ ድርጅቶች ጥምረቶች ሲኖሩ ባለፈው ሰባት ዓመት ከ4ዐዐ የሚበልጡ ባለሙያዎች ልውውጥ ተደርጓል፡፡

በኢትዮጵያ ከ24 በላይ ልውውጥ ሲኖር ኘሮግራሙ የተጀመረው ከአምስት ዓመታት በፊት ነው፡፡ በኢትዮጵያ ተሳታፊ ድርጅቶች ቁጥር አሁን እየጨመረ ቢሆንም አናሳ ነው፡፡ በኡጋንዳ 45 ተሳታፊ ድርጅቶች አሉ፡፡ ልውውጡ በፍላጐት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ድርጅቶቹ ራሳቸው ፣በዚህ ኔትወርክ መሳተፍ እንፈልጋለን ' ካላሉ ፍሬድስኮኘሴ ኘሮግራም ውስጥ አይገቡም፡፡

ግለሰቦችንና ሀገርን ለመጥቀም ብሎም ዘላቂ ልማትን ማምጣት የሚቻለው በሰው ኃይል ልማት በመሆኑ የልምድ ልውውጥ ኘሮግራሙ እዚህ ላይ ያተኮረ ነው፡፡ እስካሁን በልውውጡ ተሳታፊ የሆኑ ሰዎች አንድ ዓመት ሌላ አገር ከሠሩ በኋላ ዕድገት ያገኛሉ፡፡ ጥሩ ደረጃ ይደርሳሉ፡፡ በሚያደርጉት አስተዋፅኦም ድርጅቶችን ብሎም ሀገርን ይጠቅማሉ፡፡
 
በኢትዮጵያ ረጅም ጊዜ በመሳተፍ የሚታወቀው የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ሴቶች ማህበር ሲሆን ከአራት ሀገራት ማለትም ዩጋንዳ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያና ዛምቢያ ጋር ሴት ጋዜጠኞችን ይለዋወጣል፡፡ ድርጅቶቹ የፈጠሩት ኔትወርክም እንደ ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና ህፃናት ባሉ ጉዳዮች ላይ ተቀናጅተው ሌሎች ኘሮጀክቶችን በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰሩትም ተባብረው አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ይሰራሉ፡፡ ሰዎችን ማግባባትና በአንድ ዓላማ ዙሪያ ማሰለፍም የኘሮግራሙ ሌላ አላማ ነው፡፡

በልምድ ልውውጡ የሚገጥሙ ተግዳሮቶች በግለሰቦች ደረጃ ያሉ የቋንቋ፣ የባህል ልዩነት ሁኔታ አንድ ሲሆን በተቻለ መጠን በማዘጋጃ ስልጠናዎች ይታገዛሉ፡፡ የመስሪያ ፈቃድ የማግኘት ችግር የነበረ ሲሆን በተሻለ በኘሮግራሙ በየዓመቱ ሂደት እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ ተሳታፊዎቹ ክፍያቸው በፍሬድስኮኘሴ መሆኑ ሲታወቅና ሥራ እንደማይሻሙ ሲገነዘቡም ሂደቱን ያቃልሉላቸዋል፡፡

ልማት ሰፋ ያለ ፅንሰ ሀሳብ ነወ፡፡ በሀገራችን የተለያየ ኮንስትራክሽን ግንባታ በአጠቃላይም ዕድገት አለ፡፡ ዕድገት ስላለ ልማት አለ ግን ለማለት አይቻልም፡፡ ልማት ማለት ከታች እስከ ላይ ያለውን ሀብት በተመሳሳይ መልኩ ስርጭት ማድረግ ማለት ነው፡፡ በአፍሪካ ሀገራት ዕድገት አለ፡፡ የዕድገቱ ተቋዳሾች ማናቸው? ሲባል ብዙውን ጊዜ የውጪ ሰውና ጥቂቶች ናቸው፡፡ ተራው ህዝብ የነፍስ ወከፍ ገቢው ሲያድግ ልማት ይባላል፡፡ ልማትን ለማምጣት ብዙ መሰራት አለበት፡፡

ሁሉም ሰው በአንድ የሚሰራበት ራዕይ ያስፈልገዋል፡፡ ከዋሻው ባሻገር ጭላንጭል ካልታየ፣ ለአንድ ዓላማ መጓዝ ሲቻል ወደልማት መሄድ ይቻላል፡፡ በሀገራችን አንድ ራዕይ ብሔራዊ ራዕይ ኖሮን በተለያየ መንገድ ወደዚያ ለመድረስ ብንሠራ ልማት ይመጣል፡፡ ይህንን ማድረግ ካልቻልን ሀገሪቱ ልታድግ አትችልም፡፡

በቤተልሔም ነጋሽ
 
< Prev   Next >