Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow "የብሔራዊ ባንክ አሰራር በቴክኖሎጂ...
"የብሔራዊ ባንክ አሰራር በቴክኖሎጂ... Print E-mail
Wednesday, 13 February 2008
"የብሔራዊ ባንክ አሰራር በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ችግር ፈጥሯል አላልንም"

የኢትዮጵያ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማኅበር


ሪፖርተር ጋዜጣ እሁድ ታህሳስ 2ዐ ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የውጭ ምንዛሬን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይለስላሴ ከበደን በመጥቀስ ያወጣው ዜና በቃለ ምልልስ ከተሰጠው መግለጫ ጋር ሲገናዘብ የተጋነነ፣ ሚዛናዊነት የሌለውና አንዳንዴም በቃለ ምልልሱ ፈፅሞ ያልተባለ እንደሆነ በመጥቀስ ማህበሩ እርምት እንዲደረግ ጠይቋል፡፡
የኢትዮጵያ የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማህበር እርምት እንዲደረግባቸው የዘረዘራቸው ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡

1.    "የብሄራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አሰራር በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ችግር ፈጥሯል" የሚለው ርዕስ የማህበሩ ሥራ አስኪያጅ ያልተናገሩትና የማህበሩን አመለካከት የሚወክል ባለመሆኑ፤
2.    "በብሄራዊ ባንክ ያለው አሰራር ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ ስፍር ቁጥር የሌለው የመፃህፍት እርዳታ እንዳይደርስ እንቅፋት መፍጠሩን ለሀገሪቱ ትምህርት ቤተች ተናግረዋል" የሚለው ፅሁፍ የሚገልፀው ማህበሩ የውጭ ምንዛሬን ጠይቆ ለማግኘት ረጅም ጊዜ ይወስድበታል የሚል ሳይሆን የብሄራዊ ባንክ አጠቃላይ አሰራር የሚተች በመሆኑ፤
3.    "ሥራ አስኪያጁ የባንኩ አሰራር እንቅፋት መፍጠሩን ለሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች ተናግረዋል" የሚለው ፅሁፍ በተሰጣቸው ቃለ ምልልስ ውስጥ ያልተነገረ በመሆኑ፤
4.    የውጭ ምንዛሬ በማጣት ምክንያት ማህበሩ ሳያገኝ የቀረው አምስት ኮንቴይነር መፃህፍት ሳይሆን አምስት ኮንቴይነር ኮምፒዩተር በመሆኑ፤
5.    "አንዳንድ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ያለ የሌለ ኃይላቸውን አማጠው ቢሰሩም ከመንግሥት የሚፈልጉትን ትብብር እንደማያገኙ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል" የሚለው የተሸራረፈና ትክክለኛ እውነታውን የማይገልፅ መሆኑን በመጥቀስ ማህበሩ እርምት እንዲደረግ ጠይቋል፡፡

ከአዘጋጁ

"የብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሬ አሰራር በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ችግር ፈጥሯል" የሚለው ርዕስ የማህበሩን ሥራ አስኪያጅ ያልተናገሩትና የማህበሩን አመለካከት የማይወክል መሆኑን፣ "ሥራ አስኪያጁ የባንኩ አሰራር እንቅፋት መፍጠሩን ለሀገሪቱ ትምህርት ቤቶች ተናግረዋል" በሚለው ፅሁፍ ላይ ደግሞ ስህተት መሰራቱን እየተቀበልን ማህበሩ ማረሚያ እንዲደረግባቸው ላቀረባቸው ሌሎች ዝርዝር ነጥቦች አንባቢዎቻችን ግንዛቤ እንዲያገኙ ይረዳ ዘንድ ሙሉ ቃለ ምልልሱን እንደሚከተለው አቅርበነዋል፡፡

ሪፖርተር፡- የውጭ ምንዛሬን በተፈለገው መጠን አለማግኘት የኢትዮጵያ እውቀትና ቴክኒዮሎጂ ሽግግር ማኀበር በእርዳታ ከውጭ በሚያመጣቸው መፃህፍትና ኮምፒዩተር እንዳያገኝ እንቅፋት ፈጥሮበታል የሚል መረጃ ሰምተን ነበር፡፡ ስለዚህ ጉዳይ የሚገልፁልን ነገር አለ?

አቶ ኃይለስላሴ፡- ከትምህርት የበለጠ ልማት የለም፤ መንግሥት ትኩረት ሰጥቶ የሚንቀሳቀስበት ነው፡፡ ስለዚህ ገንዘቡ ደግሞ እንደትላልቅ ፋብሪካዎች በሚሊዮኖች የሚቆጠር አይደለም፡፡ ለትራንስፖርት የሚሆን ለምሳሌ አንድ ኮንቴነር ለማውጣት ከአራት እስከ አምስት ሺ ዶላር ነው የሚፈጀው፡፡ ሃምሳ ሺ ቢፈቀድ መገመት ትችላለህ ስንት ኮንቴነር ሊመጣ እንደሚችል፡፡ እና ይሄ ለመንግሥት ይሄን ያህል የሚያሳስበው በሚሊዮን የሚጠየቅ ገንዘብ ስላይደለ ልንከለክል አይገባም፡፡ በዚያ ላይ ከሦስት ከአራት ከአምስት ከስድስት ወር በኋላ ልመና ሀያ ሺ ሰላሳ ሺ ዶላርን ውሰዱ ይሉናል፡፡ አንድ ኮንቴነር ሁለት ኮንቴነር ከመጣ በኋላ እንደገና ይቆማል፡፡ ያ ትንሽም ሆኖ በየአመቱ በጠየቃችሁት ጥያቄ መሠረት አሥር ኮንቴነር ካመጣችሁ፣ ለአስር ምን ማለት ነው አምሳ ሺ ዶላር ማለት ነው፡፡ አምስት ኮንቴነር አሥር ኮንቴነር መጣ ማለት ግን በየአንዳንዱ ሦስት መቶ ሀምሳ ሺ ዶላር ለአገር ገባ ማለት ነው፡፡ እና በአሥር ስታባዛው ወደ 3.5 ሚሊዮን ዶላር ማለት ነው፡፡ ከዚህ ጋር አመዛዝናችሁ ቀዳዳውን እናንተ መፍታት ትችላላችሁ፤ ይሄ ሁሉ ወደ ፓርላማ መሄድ የሚገባው ትልቅ ጉዳይ አይደለም ነው የምንለው፡፡

ሪፖርተር፡- ብሔራዊ ባንኩ ምን ምላሽ ሰጣችሁ?

አቶ ኃይለስላሴ፡-
መመሪያ የለንም አስፈቅዱ፡፡ ከበላይ አካል ከጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ መመሪያ ይድረሰን፡፡ እናንተ እንደምትጠቅሙ እናውቃለን፡፡ ደግሞ መፅሀፍ ሲመጣ ኮምፒዩተር ሲመጣ እንጋብዛቸዋለን፡፡ የሰጣችሁን ገንዘብ አንዳንዴ ይሰጠናል አይደለም? በዓመት አንድ ጊዜ ወይ ሁለት ጊዜ ይለቁልናል፤ ሀምሳ ሺ ስልሳ ሺ ዶላር በሚመጣው በዚያው ገንዘብ ቆጥበን የምናመጣውን ኮምፒዩተሮች ለትምህርት ቤቶች ሲሰጡ ትምህርት ቤት ላይ አገልግሎት ላይ ሲውሉ ኑና ተመልከቱ ብለን በርክክብ ከነስርዓቱ እንጋብዛችዋለን፡፡ የእኛ ቤተመፃሀፍትንም የእኛን ኮምፒውተር ሴንተርም መጥተው ያያሉ፡፡ እና በጣም ይገረማሉ፡፡ በግለሰብ ደረጃ ማለት ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ከዚህ በፊት ይሄ የውጭ ምንዛሬ ስላልተፈቀደላችሁ ወይም ስለዘገየባችሁ የቀረ ብዙ መፃህፍት አለ?

አቶ ኃይለስላሴ፡-
እንዴ ቁጥር አለው እንዴ? ስፍር ቁጥር የለውም፡፡ አሁን ለምሳሌ በአጭሩ ልንገርህ፤ አሁን አምስት ኮንቴነር ኮምፒዩተር ከእንግሊዝ አገር ለሚሌኒየሙ አስፈቀድን፤ ሌላው ህብረተሰብም በየአቅሙ አስተዋፅኦ እያደረገ ነው፡፡ እኛም በዚህ ዓላማችን ተመስርተን ድሮ ከምናስመጣው በተለየ ሁኔታ እርዱን ብለን የሚሌኒየሙ የአፍሪካ ጉዳይ መሆኑ፣ የአንድ አገር ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ደረጃ ሁሉ የተፈቀደ የተከበረ በዓል መሆኑን፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዩናይትድ ኔሽንም የአፍሪካ ሚሌኒየም ተብሎ መጠራቱ ትክክል መሆኑን፣ ይህን ሁሉ አስረድተን ወጥተን ቃላት ተንዘባዝበን እሺ ምንድነው የምትፈልጉት? መፅሀፍት፤ እንልክላችኋለን፡፡ አሁን ኮምፒዩተር ኤይድ ኢንተርናሽናል የተባለው ከእንግሊዝ በአጭር ጊዜ ውስጥ አምስት ኮምፒዩተር እንልካለን፤ መላኪያውንም ላኩ አለን፡፡ ለመረከብ፡፡

ሪፖርተር፡- አምስት ኮምፒዩተር ነው ወይስ አምስት ኮንቴነር?

አቶ ኃይለስላሴ፡-
አምስት ኮንቴነር ነው፡፡ ይሄ እንደደረሳችሁ ደግሞ በሚቀጥለው ሦስት ወር ውስጥ ሌላ አምስት እንልካለን አሉ፡፡ እንግዲህ ለዚያ የሚያስፈልገንን ገንዘብ ተምነን ለባንክ አቀረብን፡፡ በነሀሴ ወር ማለት ነው በ1999፡፡ እስከአሁን መልስ የለውም፡፡ እና በብዙ ውትወታ በኋላ ሄደን ስንጠይቅ የበላይ ኃላፊዎች ማወቅ አለባቸው፡፡ መመሪያም የለንም፤ እንደዚህ ዓይነት አለማችሁን እናውቃለን፤ የተከበረ አላማ ነው እንደግፈዋለን፡፡ ጥቅም ላይ የሚውለውም ለልጆች እንደሆነ ለትምህርት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ እነዚህ እቃዎች ደግሞ በአገር ውስጥ ውድ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ መፅሀፍቱን ከገበያ እንግዛ ቢባል ኮምፒዩተሩን ከነጋዴ እንግዛ ቢባል ምን ያህል ለአገሪቱ ከፍተኛ ወጪ እንደሚያስከትል እናውቃለን፤ ግን መመሪያ የለንም ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ሥለዚህ አሁን ምንም መፍትሄ የለም? በየገዜው የሚመጣ እርዳታ በየጊዜው እየተቋረጠ . . .

አቶ ኃይለስላሴ፡
- ይመጣል፣ ይሰጡናል፣ ስለማንወስደው ወደ ናይጄሪያ ይሄዳል፤ ወደ ደቡብ አፍሪካ ይሄዳል፤ ወደ ግብፅ ይሄዳል፤ ወደ ኬንያ ይሄዳል፡፡ እነሱ ሌላው ቀርቶ መርከቦቻቸው ለምሳሌ አንዳንድ አገሮች እነኬንያ ናይጄሪያ የራሶቻቸው መርከብ ወደዚያ አገር ሲንቀሳቀሱ እርዳታ አለው ብለው (የእነሱ በመንግሥት ደረጃ የተያዘ ነው) ሲነግሯቸው ከሌላ እቃ ጋር አብሮ ተያይዞ ይመጣል፡፡ መፅሀፉም ኮምፒዩተሩም፡፡ የእኛ ሺፒንግ ላየን ከለንደን አልፎ ሌላም ይሄዳል፡፡ ሲሄድና ሲመለስ ከአሜሪካ አገር አምስት ስድስት ኮንቴነር ማምጣት ጠብታ ማለት ነች፡፡ አንድ ኮንቴነር ለመርከብ ጠብታ ነች፡፡ ሊመጣ ይችላል፡፡ ይህን የሚያስተናብረው እርግጥ ባንክ አይደለም፤ ትህርት ሚኒስቴር አቅም ግንባታ ሚኒስቴር ብዙ አሉ ይህ የሚመለከታቸው፡፡

ሪፖርተር፡- ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ለመነጋገር አልሞከራችሁም?

አቶ ኃይለስላሴ፡-
(ሳቅ) ትምህርት ሚኒስቴርን በዚህ ልነግርህ አልችለም፡፡ አስቸጋሪ ነው፡፡ የሚሰማም የለም፡፡

ሪፖርተር፡- ምን መደረግ አለበት ብለው ያስባሉ?

አቶ ኃይለስላሴ፡-
ምን መደረግ አለበት? በየመስኩ ይታወቃል፡፡ ይህን ለማገናኘት የሞከርነው ከዲያስፖራው ጋር ነው፡፡ ይህንን የሚሰሩልን ዲያስፖራዎች ናቸው፡፡ እዚያው ሆነው ተሯሩጠው ወይ ከመደበኛ ትምህርታቸው ወይም ሥራቸው ውጭ በየኮሌጁ በየርዳታ ሰጪ ድርጅት ደጅ እየጠኑ ለኢትዮጵያ መፃህፍት ያሰባስባሉ፡፡ እንግዲህ እንዲህ ዓይነት ኮንቴነር አግኝተንላችኋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት ኮምፒዩተር ተገኝቶላችኋል፡፡ መላኪያውን ላኩ፡፡ እነሱ እቃውን ሰጥተው መላኪያውንም አይሰጡም፡፡ ሌላው ሀገር በፓርትነር ሺኘ ነው የሚሰራው፡፡ እኛ ዘጠና ፐርሰንቱን ስንችል እናንተ አሥር ፐርሰንቱን ቻሉ ይባላሉ፡፡ ይሰራሉ፡፡ ተባብረው አስተባብረው የላኩልንን መፅሀፍ መቀበል አቃተን ብለን እናስረዳለን፡፡ ያው ስብሰባ ይካሄዳል፤ ፅሁፍ እናቀርባለን መግለጫ ይሰጣል፤ በሬዲዮ በቴሌቪዥን እናስነግራለን፡፡ ያው በእናንተ በኩል እንኳን ሦስት አራት ጊዜ ተነግሯል፡፡ ምንድነው ችግራችሁ? ምንድነው የምትፈልጉት የሚል የለም፡፡ ደብዳቤም እንፅፋለን፡፡ ዳይሬክትድ የሆነ ለትምህርት ሚኒስቴር ፅፈናል፡፡ ለአቅም ግንባታ ሚኒስቴር ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አሁን የቀረን ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ብቻ ነው፡፡ እኛ መደረግም ያለበት ይሄ ነገር ጠቃሚ ከሆነ ባለቤት ሊኖረው ይገባል፡፡ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶቹ በተግባር የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ፣ ግማሹ ለራሱ ጥቅምም የሚሰራ አለ፡፡ በመንግሥታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ስም ብዙ ገንዘብ ይመጣል ግን አገሪቱ ደግሞ ያን ያህል አትጠቀምበትም፡፡ ይሄ ይታወቃል፡፡ ግማሹ ደግሞ የሌለውን አቅሙን አሟጥጦ በኤች አይ ቪ ኤድስ በጤና በትምህርት የሚሰራ አለ፡፡ እንዚህን ለይቶ የማወቅ የመንግሥት ጉዳይ ነው፡፡ ማን ምን ይሰራል? እርዳታ ብናደርግ መንግሥትን ነው እኮ የምናግዘው፡፡ አይደለም? ለዚህ የዚህ ድርጅት አቅሙ ቢጠናከር ይሄን ይሄን ቀዳዳ ሊሸፍን ስለሚችል በተጠና መልኩ ዝም ብሎ እሱ በጠየቀው ሳይሆን ኘሮግራሙ እያቀረበ፣ እያሰማ፣ እያስፈቀደ ገንዘብ ይሰጠው፡፡ የሚፈልገውን ገንዘብ ደግሞ በትክክል ሥራ ላይ ማዋሉ ቁጥጥር ይደረግ፡፡ ያቀረባቸው መፃህፍት ለማን እንደተሰጡ ሪፖርት ያቅርብ፡፡ ኮምፒዩተሮች የት እንዳዋሉ፤ ምን ውጤት እንዳስገኙ ለውጡ ምን እንደሆነ፤ ይህንን በጋራ መስራት እንችላለን፡፡ እኛንም ያተጉናል፡፡ መንግሥትም እናተጋለን፡፡ በጋራ እንሰራለን፡፡
 
< Prev   Next >