Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow በኢትዮጵያ የሚገኙ 27 ከፍተኛ...
በኢትዮጵያ የሚገኙ 27 ከፍተኛ... Print E-mail
Wednesday, 13 February 2008
በኢትዮጵያ የሚገኙ 27 ከፍተኛ የቡና ቀማሾች የሕ (የኳሊቲ)  ደረጃ  ፈቃድ አገኙ

ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ የኪው"ኳሊቲ) ደረጃ የቡና ጥራት መርማሪዎችን አሰልጥና አስመረቀች፡፡
አሜሪካ የሚገኘው ኮፊ ኳሊቲ ኢንስቲትዩት፣ ቡት ኮፊ ኮንሰልቲንግ እና ዩ ኤስ አይድ ሲንትራክ ከቡና ጥራትና መቆጣጠር ማዕከል ጋር በመተባበር በሰጡት ስልጠና ባለፉት ሶስት ወራት ጊዜያት ውስጥ 27 ከፍተኛ የቡና ቀማሾች የኪው (ኳሊቲ) ደረጃ ፈቃድ አግኝተዋል፡፡ የቡት ኮፊ ኮንሰልቲንግ ኤንድ ትሬኒንግ አማካሪ አቶ ዳንኤል ሙሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት ከፍተኛ የቡና ቀማሾቹ የኪው (ኳሊቲ) ደረጃ ፈቃድ ማግኘታቸው ኢትዮጵያ ጥራት ያለው ቡና በብዛት ወደ ውጭ እንድትልክ ያስችላታል፡፡

እንደ አቶ ዳንኤል ገለፃ ስልጠናቸውን አጠናቅቀው ባለፈው ሳምንት የተመረቁት  ኢትዮጵያውያኖች የቡና ጥራት መርማሪዎች የኪው ደረጃ ፈቃዳቸውን ከማግኘታቸው በፊት ለ23 ቀናት ተከታታይ ፈተና ተሰጥቷቸዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በዓለም ላይ የኪው (ኳሊቲ) ደረጃ ፈቃድ ያላቸው የቡና ቀማሾች 315 ብቻ ናቸው፡፡ ኮሎምቢያ 89፣ ጃፓን 54፣ ኤልሳልቫዶር 33፣ ኮስታሪካ ደግሞ 27 የኪው ደረጃ የቡና ቀማሾች አሏቸው፡፡ ባለፈው ህዳር ወር 12 የቡና ቀማሾችን አሁን ደግሞ 15 የቡና ቀማሾችን ያስመረቀችው ኢትዮጵያ በአለም ደረጃ ከኮስታሪካ ጋር በ4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በኃይሌ ሙሉ
 
< Prev   Next >