| ለቤተ እስራኤላውያን መደገፊያ ገንዘብ ተፈቀደ |
|
|
| Wednesday, 13 February 2008 | |
|
የእስራኤል መንግሥት በኢትዮጵያ የተወለዱ፣ ይሁዳውያን ኑሯቸውን ለመደገፍ የሚያስችል የኢኮኖሚ እቅድ መንደፉ ተገለፀ፡፡ በእቅዱ መሰረት 870 ሚሊዮን". ሽቅል ለቤተእስራኤላውያኑ መደገፊያ እንዲውል ተወስኗል፡፡
የዚህ እቅድ አላማ ቤተ እስራኤላውያን አድልዎ የሌለበት፣ የሥራ ቅጥር፣ የከፍተኛ ትምህርት እድል እንዲያገኙ፣ ወጣት ባለትዳሮች የሚያስፈልጋቸውን ቤት መግዛት እንዲችሉና የገንዘብ ገቢያቸውንና ማህበራዊ ግንኙነታቸውን አገልግሎትን ለማሳደግ፣ በመኖሪያቸው አካባቢ ቤት ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ የሚያግዝ ሲሆን የገንዘቡ የመጀመሪያው ክፍያም ለዚሁ ተግባር እንደሚውል ጀሩሳሊም ፖስታ ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ ይሁዲዎች፣ በእስራኤል በሚደርስባቸው የዘር መድልዎ በመቃወም፣ ሰላማዊ ሰልፎችን አስተባባሪ የሆነው ጋዲ ያቫርኮንም እቅዱን የሚነድፈው ቡድን አባል መሆኑም ተጠቅሷል፡፡ እቅዱ "በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ሲፈፀም የቆየውን ስህተት ለማስተካከል" መሆኑን የሚናገሩት የኢሚግሬሽን ሚኒስትር ያቆብ አድሬ ለተግባራዊነት አፈፃፀም ሚኒስትራቸው ሃላፊነቱን ወስዷል፡፡ ሚኒስትር ኢደሪ ቤተ እስራኤላውያን ለመርዳት "የአይሁድ ኤጀንሲ" የተባለው ድርጅት ማቅረብ የሚገባውን 180 ሚሊዮን ባለመስጠቱ "ከአላማው ያፈገፈገ" ሲሉ ወቅሰውታል፡፡ የአይሁድ ኤጀንሲ ግን የሚኒስትሩን ወቀሳ አጣጥሎ፣ እስካሁን ኢትዮጵያኑን ለመርዳት ከ1 ቢሊዮን ሽቅል በላይ ማሰባሰቡን ገል"ል፡፡ "አሁንም መንግሥት በወሰደው ርምጃ ተደስተናል ቤተ እስራኤላውያንን ለመርዳት ከመላው ዓለም አይሁዶች ርዳታ ማሰባሰባችንን እንቀጥላለን" ብሏል፡፡ ከኢትዮጵያ የተወሰዱ ቤተ እስራኤላውያን በእስራኤል ትኩረት እንደማይሰጣቸውና የዘር መድልም እንደሚፈፅምባቸው በተደጋጋሚ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ከጋዜጣው ሪፖርተር |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |