Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 25th
Home arrow Sections arrow የኤርትራ ተቃዋሚዎች በአረብ ሳት...
የኤርትራ ተቃዋሚዎች በአረብ ሳት... Print E-mail
Wednesday, 13 February 2008
Imageየኤርትራ ተቃዋሚዎች በአረብ ሳት አዲስ የቴሌቪዥን ስርጭት ሊከፍቱ ነው

በኤርትራ ዲሽ የሌላቸውም ስርጭቱን መከታተል ይችላሉ


የኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ኪዳን በመባል የሚታወቀው የኤርትራ መንግሥት አሥራ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት በቅርቡ አዲስ የቴሌቪዥን ስርጭት እንደሚጀምር ተገለፀ፡፡ በኤርትራ ዲሽ መስቀል ባይቻልም ስርዓቱን ሕዝቡ በየቤቱ ለማየት ይችላል፡፡
የተጋድሎ ሐርነት ኤርትራ (ጀብሃ"-ሳውራ ባይቶ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ መንግሥተአብ አስመሮም የቴሌቪዥን ጣቢያው በቅርቡ ሥራ እንደሚጀምር አረጋግጠዋል፡፡ ስርጭቱ ግን ከየት አገርና ድንበር እንደሚተላለፍ ግልፅ አላደረጉም፡፡

እንደ ኃላፊው ገለፃ ስርጭቱ እንዲጀመር የታሰበው በአረብ ሳት በኩል ሲሆን በኤርትራ ዲሽ መትከል ኘሮግራሙን ሊከታተሉት ስለመቻላቸው ተጠይቀው መልስ አልሰጡም፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት የሚያሰራጩት የቴሌቪዥን ኘሮግራም በኤርትራ እየተደረገ ያለውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ህዝቡ በይፋ እንዲመለከተውና የኘሬዚዳንት ኢሳያስ መንግሥትን "አረመኔያዊ ተግባር" እንዲረዳ ለማድረግ ነው፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለፁት አዲሱ የተቃዋሚዎች ጥምረት የቴሌቪዥን ኘሮግራም የሚተላለፈው በአረብ ሳት የአየር ኪራይ ተከፍሎ በመሆኑ ሕዝቡ ዲሽ ሳይተክል ኘሮግራሙን በቀጥታ እንዲመለከት ለኤርትራ ቅርብ የሆነ አገር ስርጭቱን ከአረብ ሳት ተቀብሎ መልሶ (ሪ-ብሮድካስት) እንደሚያስተላልፈው ተናግረዋል፡፡

ምንጮቹ ስርጭቱ የሚተላለፍበትን ለኤርትራ ቅርብ የተባለችውን አገር አልገለፁም፡፡ በአረብ ሳት የሚተላለፈው ስርጭት ተቀብሎ እንደገና ማሰራጨት የግድ በመሆኑ የትኛውንም የኤርትራ አጐራባች አገር መጠቀም የግድ ነው ብለዋል፡፡ የሀዝብ ግንኙነት ኃላፊውም ይህንኑ አረጋግጠዋል፡፡

የጥምረቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የኤርትራ ህዝብ አማራጭ የቴሌቪዥን ኘሮግራም ማግኘቱ የኘሬዚዳንት ኢሳያስን አምባገነናዊ መንግት ለማስወገድ አማራጭ ነው በማለት አስታውቀዋል፡፡ ኘሮግራሙ የካቲት ወር ሳያልቅ እንደሚጀመርም ይፋ አድርገዋል፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >