Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
Jul 06th
Home arrow Sections arrow ኅብረተሰቡ ፊቱን ወደ አገር ውስጥ ጫማ አዙሯል?
ኅብረተሰቡ ፊቱን ወደ አገር ውስጥ ጫማ አዙሯል? Print E-mail
Wednesday, 13 February 2008
Imageአቶ እንየው ዘለቀ የአንበሳ ጫማ አክሲዮን ማህበር ተጠባባቂ ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ አንበሳ ጫማ ከተመሠረተ 68 ዓመታትን ቢያስቆጥርም ለውጪ ገበያ ማቅረብ ከጀመረ ገና አንድ ዓመቱ ነው፡፡ ፋብሪካው በአሁኑ ሰዓት አደረጃጀቱን ለማስተካከል የውስጥና የውጪ እድሳት በማድረግ ላይ ነው፡፡ አዳዲስ ማሽኖች ተቀይረዋል፡፡ በፋብሪካው ሁኔታ ላይ አነጋግረናቸዋል፡፡ 
ሪፖርተር፡- አንበሳ ጫማ አትራፊ ነው?

አቶ እንየው፡-
አንበሳ ጫማ ለረዥም ዓመታት በኪሳራ ሲንቀሳቀስ ነበር፡፡ የጫማ ገበያ ከፍተኛ ውድድር ያለበት የሥራ መስክ ነው፡፡ በተለይ ከቻይና እየተሠሩ በሚገቡ ጫማዎች ከፍተኛ የገበያ ውድድር ነበረበት፡፡ በዚህ ሁኔታ በቀላሉ ወደ ትርፋማነት መምጣት አስቸጋሪ ነው፡፡ የሚጠቀመው የቆዳ ግብዓት ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ስለሚሄድ የሚፈለገው ጥራትና ዋጋ አያገኝም፡፡ በሁሉም በኩል ያለው ውድድር ትርፋማነቱን ይዞታል፡፡ ትርፋማ ለመሆን አደረጃጀታችን እየቀየርን ነው፡፡ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቀና ምርታማነቱ የተሻለ እንዲሆን አዳዲስ መሳሪያዎችን ለመጠቀም ጥረት እያደረግን ነው፡፡ በስድስት ወር የታየው የሚያዝናና ትርፍ ባይሆንም ወደ ትርፋማ የሚወስድ መልካም ጅምር ነው፡፡ በቀጣይ በወጪ ንግድ ውስጥ ለመግባት የአመራረት ሁኔታችን መስተካከል ስላለበት ትኩረት ሰጥተን እየሠራን ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- ከቻይና የሚገቡ ጫማዎች እንዲታገዱ ስትጠይቁ ነበር፡፡ አሁንስ ጥያቄውን ተዋችሁት?

አቶ እንየው፡-
በአገር ውስጥ ጥሩ ገበያ አለን፡፡ ሕብረተሰቡ አማላይ ግን ጥራት የሌላቸውን ጫማዎችን እያወቀ መጥቶ ወደ አገር ውስጥ ጫማ ፊቱን እያዞረ ነው፡፡ ሕዝቡ እይታ ብቻ ሳይሆን ምቾትን ጥንካሬና ጥራትን የሚፈልግበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ አንበሳ ጫማ የሚያመርታቸው ጫማዎች ጠንካራ መሆናቸውን ያውቃል፡፡ የዲዛይን ችግሮች ነበሩ፡፡ አሁን አሻሽለን ገበያ ውስጥ ለመግባት በዘመናዊ መሣሪያዎች እየሠራን ነው፡፡ ጣሊያን ካለን ደንበኛ የቴክኒክ ድጋፍ ይደረግልናል፡፡ ጫማዎቹም ፋሽን የተከተሉ እንዲሆኑ ከጣሊያን በሚመጣ ዲዛይን እየሠራን ነው፡፡ የምናመርታቸው ጫማዎች በውጭም ሆነ ለአገር ውስጥ በተመሳሳይ ዲዛይን በማቅረብ በአገር ውስጥ ገበያ ተቀባይነት እንዲኖረን እንሠራለን፡፡

ሪፖርተር፡- ለውጭ ገበያ በምታቀርቧቸው ጫማዎች ተቀባይነት አግኝታችኋል?

አቶ እንየው፡-
በምንልካቸው ምርቶች የጥራት ጉድለት የለብንም፡፡ ብዙ ጫማዎችን ልከናል፡፡ ያለው ቅሬታ በተባለው ጊዜ አለማድረስ ነው፡፡ ጫማዎቹ በውጪም ተቀባይነት አላቸው፡፡ ይህን ምርት በይበልጥ ለአገራችንም ለማድረስ እየሠራን ነው፡፡ አሁንም ከቻይና ጫማዎች ይገባሉ፡፡ ሕብረተሰቡ አይቷቸው ጥራታቸውን አውቆ ወደ አገር ውስጥ ጫማ ፊቱን አዙሯል፡፡ አሁን በአንዳንድ ሱቆቻችን እጥረት አለ፡፡ ፕሮጀክታችንን አጠናቅቀን የተሻለ አቅርቦት እንዲኖር እንሠራለን፡፡ ሕብረተሰቡ እንዲቆሙ አድርጓቸዋል፡፡ ሆኖም ከሕንድና ከቱርክ የሚመጡ ጥራት ያላቸው ጫማዎች በጣም ተወዳዳሪ ናቸው፡፡

ሪፖርተር፡- የማስፋፊያ ሥራው ወጪ በማን ይሸፈናል?

አቶ እንየው፡-
ከኢንዱስትሪ ልማት ፈንድ ከወለድ ነፃ በተፈቀደልን 16.5 ሚሊዮን ብር የማምረቻ መሥሪያዎችን ገዝተን የመሣሪያ ተከላውን እያጠናቀቅን ነው፡፡ በየካቲት ወር መጨረሻ ሥራውን ሙሉ በሙሉ እንጀምራለን፡፡ የገዛናቸው የማምረቻ መሳሪያዎች ዘመናዊ ናቸው፡፡ የዋና ፋብሪካውን መሳሪያዎች ሙሉ በሙሉ ቀይረናል፡፡ ዱሮ በስፌት ክፍል ያልነበረው የኮንቬየር ሲስተም ተዘርግቷል፡፡ የሶል ማምረቻ የለንም ማለት ይቀል ነበር፡፡ አሁን ዘመናዊሁለት የሶል ማምረቻዎችን ገዝተናል፡፡ በቀን በስምንት ሰዓታት በአጠቃላይ 3000 ጥንድ ጫማዎችን ለውጪ ገበያ ለማቅረብ በሚያስችል አቅም ተደራጅተናል፡ ወደ ፈረቃ ስናሳድገው በቀን 6000 ጫማ ማምረት ይቻላል፡፡ የፋብሪካውን ሌይአውትም ሆነ የማምረቻ መሳሪያውን በአዲስ ይዘት አስተካክለናል፡፡ በተለይ ሌይአውትም አደረጃጀት በጣሊያን ባለሙያዎች የተዘጋጀ ነው፡፡  

ሪፖርተር፡- የዘርፉ ችግር ምንድን ነው?

አቶ እንየው፡-
በጫማ ዘርፍ ቆዳ በሚፈለገው ጥራትና መጠን አይገኝም፡፡ ዘርፉ ማንኛውም ሰው በአነስተኛና መካከለኛ አቅም ሊገባበት የሚችል ዓይነት በመሆኑ ከፍተኛ ውድድር አለ፡፡ በርካታ ጫማዎች ከውጪ ስለሚገቡ ከፍተኛ ውድድር አለ፡፡ ለጫማ ማምረቻ አስፈላጊ የሆኑት (አክሰሰሪስ) ጥቃቅን ውስጣዊ ግብዓቶችን የሚያመርት ፋብሪካ የለም፡፡ ከውጪ ለማስገባት በጉምሩክ አሠራር ጊዜን ይጠይቃል፡፡ በግዢው ሂደት ኮንቴይነር መሙላት አለበት፡፡ ለዚህ የሥራ ማስኬጃ እጥረት አለ፡፡ ለጫማ ሥራ ሁሉም ግብዓት ተሞልቶበት አንዷ ብትጎድል ማምረት አይቻልም፡፡ እያንዳንዱ ፋብሪካ በራሱ ለማሰልጠን ጊዜ ይፈጃል፡፡ የረዥም ጊዜ ልምምድ ይጠይቃል፡፡ ባለሙያ ገበያ ላይ አይገኝም፡፡ የማሰልጠኛ ተቋሙ ያሰለጥናል ግን ቁጥራቸው ውሱን ነው፡፡ ከጫማ ሴክተሩ ጋር ተመጣጣኝ አይደለም፡፡ ዘርፉ ዘርፈ ብዙ ችግር አለበት፡፡ በግብዓትም ሆነ በገበያ ፈታኝ ነው፡፡

ሪፖርተር፡- ሰፊ የቆዳና የሌጦ ሃብት እያለ የቆዳ ችግር መፈጠሩ ለምንድነው?

አቶ እንየው፡-
ብዙ ጊዜ ያላለቀለትን ቆዳ ቆሻሻውን ብቻ በማላቀቅ የሚለኩ  ፋብሪካዎች ቁጥር ይበዛል፡፡ የተዘጋጀ ቆዳ የሚያቀርቡት ቁጥር አናሳ ነው፡፡ የተዘጋጀ ቆዳ የሚያመርቱትም ከተመሳሳይ ገበያ ቆዳውን ስለሚያገኙት በውድድሩ እየተዳከሙ ነው፡፡ በዚህ ላይ የፖሊሲ ውሳኔ አዋጅ ወጥቷል፡፡ የቆዳ ፋብሪካዎች አቅም ለማጠናከር የተዘጋጀ ቆዳ አቅርቦት ሊጨምር ይችላል፡፡

ሪፖርተር፡- የሠራተኞች ምርታማነት ምን ደረጃ ላይ ነው?

አቶ እንየው፡-
ሠራተኛው የሥራ ፍላጐት፣ የሥራ ልምድ አለው፡፡ ነገር ግን አደረጃጀቱ በጣም ኋላ ቀር ስለነበር ጥሩ አልነበረም፡፡ ምርታማነቱ የሠራተኛው ችግር ብቻ ሳይሆን አደረጃጅቱና ግብዓት በበቂ ሁኔታ አለመገኘት ተፅዕኖ ሲያሳድር ቆይቷል፡፡ ይህን በመቀየር በተለይ በስፌት የኮንፊየር ሲስተም ዘርግተናል፡፡ ሲስተሙ ተንቀሳቃሽና በተለያየ ሂደት የሚያመርቱ ሠራተኞች ስለሚኖሩ የአንዱ ሠራተኛ አለመሥራት ሥራውን ስለሚያጓትት ምርታማነትን በመጨመርም ሆነ ሠራተኞችን በመቆጣጠር ትልቅ እገዛ ይኖረዋል፡፡ የአንበሳ ጫማ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ዘርፍ ምርታማነት ላይ ብዙ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ለሥራው ምቹ ሁኔታ መፍጠር ምርታማነትን ያሳድጋል፡፡
 
ሪፖርተር፡- በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ የተወዳዳሪ አቅምን ለመገንባት በሚል ወደ ግል ባለሐብቶች እየተዛወረ ነው፡፡ የአንበሳ ጫማ ሁኔታ ምን ደረጃ ላይ ነው?

አቶ እንየው፡-
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሁሉም ወደ የግል መዞራቸው አይቀርም፡፡ አንበሳ ጫማ ከአሁን በፊት ወደ ግል ለማዞር ጨረታ ወጥቶ ነበር፡፡ የተሳካ አልመሰለኝም፡፡ ፋብሪካዎች ሕይወት ዘርተው በተሻለ አደረጃጀት ሊሠሩ የሚችሉበት አቅም እንዲገኙ ተደርጓል፡፡ ጥሩ አጋጣሚው የፋብሪካዎችን አቅም በብቃት ለማደራጀት ያለው እንቅስቃሴ ነው፡፡ መንግሥት ፖሊሲው ስለሆነ ወደ ግል ሊያዞረው ይችላል፡፡ ነገር ግን የባለቤትነት ለውጥ እንጂ በሠራተኛውም ሆነ በሥራው ላይ ተፅዕኖ ላይፈጥር ይችላል፡፡ የተወዳዳሪነት አቅም መገንባት እስከቻለ ድረስ ባለቤቱ ማንም ቢሆን ለውጥ አይፈጥርም፡፡  

ሪፖርተር፡- ደንበኞቻችሁ እነማን ናቸው?

አቶ እንየው፡
- አሁን ያለን ጣሊያን አገር የሚገኝ ላኖቫ አደልኪ የተባለ አንድ ትልቅ ኩባንያ ነው፡፡ የራሱ ጫማ ፋብሪካ ያለው ነው፡፡ ትዕዛዝ ይሰጠናል፤ ቴክኒካል ድጋፍ ያደርግልናል፡፡ በመጠነኛ ደረጃ የወታደር ጫማ ወደ ደቡብ ሱዳን እየላክን ነው፡፡

ሪፖርተር፡- አንድ ደንበኛ ብቻ መሆኑ አላነሰም?

አቶ እንየው፡-
በአንድ ደንበኛ ላይ ትኩረት ማድረጉን ለመቀየር አስበናል፡፡ ሌሎች ሸማቾችን እየፈለግን ነው፡፡ ይህ የአደረጃጀት ዘዴያችን አንዱ የገበያ መፈለጊያ ዘዴ ነው፡፡ ሁልጊዜ ደንበኞች ይመጣሉ፡፡ አቅማችንና አደረጃጀታችንን ሲያምኑበት ብቻ ነው ትዕዛዝ የሚሰጡት፡፡ ስለዚህ ወደ ፊት ደንበኞች ይኖሩናል፡፡

ሪፖርተር፡- ለውጭ ገበያ ማቅረብ የጀመራችሁት መቼ ነውን?

አቶ እንየው
፡- ለውጪ ገበያ ማቅረብ የጀመርነው በ1999 ዓ.ም የበጀት ዓመት አጋማሽ ላይ ነው፡፡ ከዚያ በፊት የምናመርተው ለአገር ውስጥ ትኩረቱ ለወታደራዊና ሠራተኛ የደንብ ጫማ ነበር፡፡ በተወሰነ መልኩ ለልጆችና ለሴቶች ጫማ እናመርት ነበር፡፡ ወደ ውጪ ለመላክ የሚያስችለንን ሁኔታ በማጥናት ገበያ በማፈላለግ ወደዚህ ለመግባት ከደንበኛው ጋር 13"000 የጫማ የላይኛውን ሽፋን ላክን፡፡ ይህን ብታስተካክሉ የሚል ምክር ተሰጠን፡፡ የላክነው ጫማ በጥራቱ ተቀባይነት ስላገኘ ያለቀለት ጫማ መላክ ትችላላችሁ በሚል ያለቀለት ምርት ትዕዛዝ ተሰጠን በዚያ ግማሽ የበጀት ዓመት አምስት ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ላክን፡፡ በዚህ ዓመት 6 ወር 7 ሚሊዮን ብር ልከናል፡፡ በቀጣይ የተሰጠን እቅድ ብዙ ነው፡፡ ባለን አቅም ብቻ ስለሠራን የእቅዳችንን 65 በመቶ ብቻ ሠርተናል፡፡ አቅዳችንን ለማሟላት እንሠራለን፡፡

ሪፖርተር፡- የፋብሪካዎቹን አቅም ለአገር ውስጥና ለውጪ ገበያ በሚል የከፋፈላችሁበት ሁኔታ አለ?

አቶ እንየው፡-
ዋናውን ፋብሪካ ሙሉ በሙሉ ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ጫማዎችን እንዲሠራ አድርገን አደራጅተናል፡፡ በቀጣይ በፈረቃ ለአገር ውስጥ ገበያ የምናቀርብ ይሆናል፡፡ ቄራ የሚገኘውን ፋብሪካ የቀድሞ ፋብሪካዎችን ዕቃ አደራጅተን የደንብ፣ የሥራና ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉ ጫማዎችን እያመረትን ነው፡፡ ዋና ፋብሪካው 3 ሺህ ጥንድ ጫማዎችን ሁለተኛው ፋብሪካ 1500 ጫማዎችን የማምረት የዲዛይን አቅም አለን፡፡

ሪፖርተር፡-  የትራንስፖርት ዋጋ ለጫማው በውጪ ገበያ ላይ የዋጋ ተፅዕኖ አያሳድርም?

አቶ እንየው፡-
ጫማዎችን የምንልከው በመርከብ ነው፡፡ በዋጋ ደረጃ ትንሽ ነው፡፡ ትልቁ ችግር በሚፈለገው ፍጥነት አይደርስም፡፡ ጫማ የፋሽን ገበያ ስለሆነ ፈጥኖ መድረስ ይፈልጋል፡፡ ደንበኞች የገዙትን ጫማ በፍጥነት ማሠራጨት ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ ችግር አለብን፡፡ የተዘጋጁ ጫማዎችን የምንልከው ጅቡቲ ድረስ ነው፡፡ ወጪውን ሸፍነው በአየር እንድንልክ ይጠይቁናል፡፡ የላይኛውን ሽፋን ሰፍተን እንልካለን፡፡ ይህ ክብደት ይቀንሳል፡፡ ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀውን በአየር ለመላክ በጣም ውድ ነው፡፡ 
 
< Prev   Next >