Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow ሕንድ ለአፍሪካ ምርቶች የቀረጥና...
ሕንድ ለአፍሪካ ምርቶች የቀረጥና... Print E-mail
Wednesday, 13 February 2008
ሕንድ ለአፍሪካ ምርቶች የቀረጥና የኮታ ነፃ አሠራርን ፈቀደች

ሕንድ የቀረጥና ኮታ ነፃ ገበያ አሠራርን ለአፍሪካ ምርቶች ፈቀደች፡፡ ፈቃዱ የተሰጠው በቀጣይ የሕንድ የዘይት ኩባንያዎች በአፍሪካ ኢንቨስትመንት ውስጥ ተሳታፊ ለመሆን የሚያደርጉበትን ጥረት ለማገዝ እንደሆነ ኒውስ ቫይን ዘግቧል፡፡
በቀጣይነትም በሕንድና በአፍሪካ አህጉር መካከል ያለውን የኢንቨስትመንት ግንኙነት ከነዳጅ ዘይት መፈለግና ማምረት ጀምሮ እስከ መካከለኛና አነስተኛ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለማካሄድ መታቀዱም ተገል"ል፡፡

ሕንድ የቀረጥ ነፃና የኮታ ነፃ አሠራር ሂደትን ሆንግ ኮንግ ውስጥ በተካሄደው የ"ጉቦም" ንግድ ድርጅት ስብስባ ወቅት በወጣው መመሪያ መሠረት ሲሆን መመሪያው ታዳጊ አገሮችን ለማገዝና በዓለም ገበያ ያለውን ያልተመጣጠነ እድገት ለመቀነስ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ተገል"ል፡፡

ሕንድና ቻይና በአፍሪካ ውስጥ ያላቸውን የኢንቨስትመንት መጠን ለማሳደግ ትንቅንቅ ላይ ሲሆኑ ሁለቱም አገሮች ራሳቸውን የአፍሪካ ወዳጆች አድርገው ያስቀምጣሉ፡፡ ሕንድ ከአፍሪካ በ2006/7 ወደ አገርዋ ያስገባቸው የምርት መጠን በግምት 8.3 ቢሊየን ይደርሳል፡፡ ሕንድ ከአፍሪካ ያስገባችው ምርት መጠን ከጠቅላላው ምርት የ7 ከመቶ ድርሻ ሲኖረው ከአፍሪካ ወደ ሕንድ የተላከው የገበያ ድርሻም በ54 በመቶ ማደጉም ተገል"ል፡፡

ከአፍሪካ ጋር የምታደርገው የግብይት መጠን ዕድገት እንዲያመጣ እየሠራች እንደሆነና ከአፍሪካ ጋር የነበራት የገበያ ልውውጥ በ2006/7 ከ80 በመቶ ዕድገት በማሳየት 20 ቢሊዮን መድረሱ ተጠቁሟል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሕንድ መንግሥት አፍሪካ ጋር ያለው የገበያ ትስስር እያደገ በመሄዱ አገሪቷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የገበያ ድርሻ ለማስፋፋት ጠቃሚ መሆኑ ታምኖበታል፡፡

የታዳጊ አገሮችን የንግድ እንቅስቃሴ ለማጠናከር ከኮታ ነፃ የሆነ ገበያ በመፍቀዷ ሕንድ የመሪነት ቦታ ሊያሰጣት የሚችል እንደሆነም የሕንድ የንግድ ሚኒስትር መግለጫ ያመላክታል፡፡

ሕንድ ከአፍሪካ ጋር ያላትን የቆየ ግንኙነት ለማሳደግ የተጠቀመችው ቻይና ስታደርገው እንደነበረው በኢኮኖሚ ዲፕሎማሲና በዕርዳታ ላይ የተመሠረተ እንደሆነ ተገል"ል፡፡ ከአፍሪካ ጋር የተሻለ ግንኙነት እንዲኖር በአዲስ መልክ በአፍሪካ ብቻ የሚሆን ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ፖሊሲ ማዘጋጀቷም ተገል"ል፡፡

በተለይ ኦ.ኤን.ጂ.ሲ ቪዴስ ሊትድ፣ ኦይል ኢንዲያ ሊትድ፣ ኢንዲያን ኦይል ኮርፕ ሊትድ የተባሉ ሦስቱ የነዳጅ ኩባንያዎች በ14 የአፍሪካ አገሮች በኢትዮጵያ፣ ሊቢያ፣ ናይጄሪያ፣ አልጄሪያ፣ አንጎላ፣ ሱዳን፣ ግብፅ፣ ጋቦን፣ ኮንጎ፣ ቻድ፣ ካሜሮን፣ ቱኒዚያ፣ ጋና እና ሞዛምቢክ ለመሰማራት ዝግጅት እያደረጉ መሆኑም ተገል"ል፡፡

ከሕንድ የንግድ ሚኒስቴር የወጣው መረጃ እንደሚጠቁመው፤ የነዳጅ ኩባንያዎቹ በአፍሪካ የሚኖራቸውን ኢንቨስትመንት በተመለከተ ቅድመ የፖሊሲ ረቂቅ ቀረፃዎችን በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡

በ2007 ዓ.ም ከሚያዚያ እስከ መስከረም የተመዘገበው መረጃ እንደሚጠቁመው ከናይጄሪያ፣ ከደቡብ አፍሪካ፣ ጊኒ እና አንጎላ የተላኩ ብዙ ምርቶች ሕንድ ገብተዋል፡፡ ወደ ሕንድ ከገቡት የአፍሪካ ምርቶች መካከል ከናይጄሪያ፣ አንጎላና ጊኒ የነዳጅ ዘይትና ማዕድናት ሲሆኑ ከደቡብ አፍሪካ ደግሞ ማዕድን መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >