| የውጭ ምንዛሬ ችግርን ለማቃለል... |
|
|
| Wednesday, 13 February 2008 | |
![]() የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ሮበርት ዞሊክ ኢትዮጵያ ያለባትን የውጭ ምንዛሬ ችግር ለማቃለል የዓለም ባንክ አዲስ የእገዛ እስትራቴጂ ለማውጣት ከቦርዱ ጋር እንደሚነጋገር ገለፀ፡፡ ከሁለት ወራት በኋላ መፍትሄ እንደሚያገኝም የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት ሮበርት ዞሊክ ገልፀዋል፡፡ ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ በተካሄደው የአፍሪካ ሕብረት 10ኛው መደበኛ ስብሰባ ላይ በተሳተፉበት ወቅተ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የሆነ እድገት እያስመዘገበች መሆኗን ገልፀው ይህን ለማጠናከር አዲስ የእገዛ ስትራቴጂ ለማውጣት ከዓለም ባንክ ቦርድ ጋር እንደሚነጋገሩ በሁለት ወራት ውስጥ መልስ እንደሚያገኝም ጠቁመዋል፡፡ አገሮች የሚያሳዩት ብቃት ከዓለም የልማት ማህበር ፕሮግራም የተለየ ብድርና እርዳታ እንደሚያገኙ ገልፀው ኢትዮጵያ እያሳየች ባለው ጥሩ ብቃት ከመቶ ሚሊዮን ዶላር በላይ እገዛ በእርዳታ ወይም በአነስተኛ ወለድ የሚታሰብ ብድር እንደሚሰጣትም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የዓለም ባንክ በሚያደርግላት ድጋፍ በየትኛው የልማት አካባቢ ውጤታማ የሆነ እድገት አሳይታለች ለተባለውም ሚስተር ዞሊክ፣ "ኢትዮጵያ በተመረጡና በተለያዩ አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን በሁሉም ውጤታማ መሆኗን አሳይታለች፤ የኢትዮጵያ የልማት ስትራቴጂና አቅጣጫዎች ለሌሎች አገሮች ልምድ ለማስተላለፍ የሚያስችል" ነው ብለዋል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር ባደረጉት ውይይትም በኢትዮጵያ ባሉ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በስፋት መወያየት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ እያስመዘገበች ያለውን እድገት ለማገዝ ጥሩ አጋሮች ለመሆን ምን ማድረግ እንደሚገባቸው እያሰቡ መሆኑን ተናግረው በዋናነት የኢትዮጵያ መንግሥት እድገቱ ሁሉንም አካባቢዎች ያቀፈ እንዲሆን አመራርን ወደ ታች በማውረድ በኩል ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ በኢትዮጵያ ያለው የእድገት ሁኔታ ጠንካራ እንደሆነ የተናገሩት ፕሬዚዳንት ዞሊክ ከኢትዮጵያ ጋር በሚኖረው ማናቸውም ጉዳዮች ጠንካራ ግንኙነት እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |