| የክፍያ ቴሌቪዥን ተጠቃሚዎች... |
|
|
| Wednesday, 13 February 2008 | |
![]() ሚስተር ጁሊያኖ ማኪንቶ በኢትዮጵያ ከ1.5 ሚሊዮን ባለቀለም ቴሌቪዥኖች ሲኖሩ የክፍያ ቴሌቪዥን አገልግሎት ተጠቃሚ የሆኑት ከ10 ሺህ እንደማይበልጡ ተገለፀ፡፡ በአፍሪካ ከሚገኙት 40 ሚሊዮን የባለቀለም ቴለቪዥን ተጠቃሚዎች 1 በመቶ የሚሆኑት ብቻ አገልግሎቱን ያገኛሉ፡፡ የጂቲቪ የክፍያ ቴሌቪዥን አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተርና መስራች ሚስተር ጁሊያኖ ማኪንቶ የጂቲቪ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በማስመልከት ሰኞ የካቲት 3 ቀን 2000 ዓ.ም በሸራተን አዲስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በኢትዮጵያ የክፍያ ቴሌቪዥን ተጠቃሚዎች ቁጥር አነስተኛ መሆን ለዚህም ዋጋው ከፍተኛነትን በምክንያትነት ገልፀዋል፡፡ ጂቲቪ የክፍያ ቴሌቪዥንን ሕብረተሰቡ መግዛት በሚችልበት አቅም ለማቅረብ ማቀዱን የገለፁት ሚኒስትር ጁሊያኖ በሌሎች የአፍሪካ አገሮች እነደሚደረገው ሁሉ ለኢትዮጵያ ስፖርት ድጋፍ ለማድረግ ከፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች ጋር መነጋገራቸውንም ጠቁመዋል፡፡ የቀጥታ የስፖርት ዝግጅቶች፣ ወቅታዊ የሆኑ ፊልሞችን፣ የሙዚቃ፣ የዜና ቻናሎችን ለሕፃናት የካርቶን ፊልሞችን ያቀፉ ቻናሎችን ተግባራዊ ማድረጋቸው ተገል"ል፡፡ በአሁኑ ሰዓት አስራ ሰባት ቻናሎች መክፈታቸውን ገልፀው እስከ ግንቦት መጀመሪያ ተጨማሪ 30 ቻናሎችን ለመክፈት መታቀዱንም ገልፀዋል፡፡ ጂቲቪ የባርክሌይን ፕሪምየርሊግ ሲያስተላለፍ የቆየ ሲሆን ከሚቀጥለው ሲዝን ጀምሮ ኤፍ ኤ ካፕን ለአፍሪካ ማድረስ ይጀምራል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከአውሮፓ እግር ኳስ የጣሊያን ሴሪ ኤን፣ የጀርመን ቡንደስ ሊጋንና የፈረንሳይ ካፕን በመላው አፍሪካ ሲያሰራጭ ቆይቷል፡፡ የሜትሮ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር የሕዝብ ግንኙነትና የማርኬቲንግ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዲኒር አብዱላሂ በበኩላቸው ጂቲቪ ቀደም ባሉት ጊዜያት ኢትዮጵያ የነበራትን የረሃብና አስከፊ ገፅታ በመቀየር በኩል ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ገልፀው በአፍሪካ ዙሪያ የሚያጠነጥን ጂ አፍሪክ የተሰኘውና በቀጣይነት የሚከፈተው የጂቲቪ ቻናል የአፍሪካ እሴትን ለማስተዋወቅ እንደሚረዳ ገልፀዋል፡፡ በቤዛዊት ሥዩም |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |