| አዲስ የኢንሹራንስ ኩባንያ ሥራ ጀመረ |
|
|
| Wednesday, 13 February 2008 | |
|
ኢትዮ ላይፍ ኢንሹራንስ አክሲዮን ማኀበር በሚል መጠሪያ የሚታወቅ አዲስ የኢንሹራንስ ኩባንያ ሥራውን ጀመረ፡፡ በ13ዐ ባለአክሲዮኖች ባለፈው ቅዳሜ በግዮን ሆቴል የተመሰረተው የኢንሹራንስ ኩባንያ ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ የተከፈለ ካፒታል ሲኖረው፣ በህይወት እና በጤና ኢንሹራንስ ላይ ያተኩራል፡፡
በኩባንያው ምስረታ ላይ እንደተገለፀው ኩባንያው በኢትዮጵያ ከ34 ዓመታት ቆይታ በኋላ ብቸኛ የሆነ የህይወት ኢንሹራንስ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ሲሆን፣ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ አስተማማኝ የሆነ ገበያ እንደሚገኝና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ፍላጐት በአገሪቱ ውስጥ መኖሩም ተመልክቷል፡፡ በአሁኑ ወቅተ በአገሪቱ ያለው የህይወት ኢንሹራንስ ተዋፅኦ እዚህ ግባ የማይባልና ከጠቅላላው የኢንሹራንስ ሽያጭ ምጣኔም ከ5 እስከ 6 በመቶ ብቻ ድርሻ አለው፡፡ በመሆኑም ኢትዮ ላይፍ ኢንሹራንስ ኩባንያ በህይወት ኢንሹራንስ ዘርፍ ያለውን እውነታ በመቀየር ዘላቂና ራሱን የቻለ የቢዝነስ ተቋም ለማድረግ ማቀዱን አስታውቋል፡፡ "በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ካሉ ሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን ኢትዮ ላይፍ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ይህን ዘርፍ ወደ 15 በመቶ ለማሳደግ የራሱን ድርሻ እንደሚወጣ ኩባንያው በሰጠው ጋዜጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ኩባንያው በዕለቱ ሰባት አባላት ያሉት የዳይሬክተሮች ቦርድ የሰየመ ሲሆን፣ አምስቱ ግለሰቦች ሲሆኑ፣ ሁለቱ ደግሞ ኢትዮጵያ የማሽነሪዎች የኪራይ ድርጅትና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች የቁጠባና የብድር ማኀበር ናቸው፡፡ በዳዊት ታዬ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |