Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 25th
Home arrow Sections arrow የአዲስ አበባ ገበያ ከብዙ በጥቂቱ
የአዲስ አበባ ገበያ ከብዙ በጥቂቱ Print E-mail
Wednesday, 13 February 2008
ለተለያዩ አገልግሎትና ፍጆታዎች የሚውሉ ምርቶች ዋጋ አሁንም በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር ላይ ይገኛል፡፡ በተለይ የምግብ ምርቶች ዋጋ እስከ 40 በመቶ የሚደርስ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ እንደ ብረት ያሉ ምርቶች የዋጋ ጭማሪ ብቻ ሳይሆን እጥረትም እያሳዩ ነው፡፡

ሰሞኑን ባደረግነው የገበያ ቅኝት አብዛኛዎቹ ምርቶች የዋጋ ለውጥ የታየባቸው ሲሆን ሰሞኑን በአዲስ መልክ የተደረገው ጭማሪ ከነዳጅ ዋጋ ጋር በተያያዘ እንደሆነ ተረድተናል፡፡

በተለይ ባለፉት ሁለት ዓመታት ምግብ ነክ ምርቶች መካከል ከፍተኛ የዋጋ ለውጥ የታየበት አንዱ የምግብ ዘይት ነው፡፡ ከሁለት አመታት በፊት በአማካይ 30 ብር ይሸጥ የነበረ የታሸገ የምግብ ዘይት በአሁኑ ወቅት ከ60 እስከ 62 ብር ደርሷል፡፡ አንደኛ ደረጃ ጤፍ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ከ450 እስከ 500 ብር ለረጅም ጊዜ ደግሞ በአማካይ በ550 ብር ሲሸጥ ቆይቶ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ዋጋው ከፍ እያለ በመምጣት ካለፈው ሣምንት ጀምሮ በአማካይ 680 ብር ደርሷል፡፡

በሌሎች እህሎች ላይም ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአንድ ኩንታል ላይ ከ30 እስከ 70 ብር የሚደርስ ጭማሪ እንደታየባቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

በአማካይ ሰባት ብር ይሸጥ የነበረው ምስር ክክ ሰሞኑን 11 ብር ሆኗል፡፡ አንድ ኪሎ ድንች ከ5 እስከ 6 ብር በመሸጥ ላይ ነው፡ የሳሙና ዋጋ ከፍተኛ ለውጥ እያሳየ ነው፡፡ ሦስት ብር የነበረው አራት ከአምሣ፣ አንድ ብር የነበረው ሁለት ብር ወዘተ. ሆኗል፡፡ በአማካይ አንድ ኪሎ ላይ 7 ብር የሚደርስ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ ከአራት ብር እስከ 4.50 ይሸጡ የነበሩ የአገር ውስጥ የፓስታ ምርቶች አሁን 5.50 በመሸጥ ላይ ናቸው፡፡ የውጭ ፓስታ ምርቶች ግን ከአገር ውስጥ ምርቶች በበለጠ የዋጋ ጭማሪ ታይቶባቸዋል፡፡ 6 ብር ይሸጡ የነበሩ የውጭ ፓስታዎች አሁን 9 ብር ደርሰዋል፡፡ በተመሣሣይ ሁኔታ በአንድ ኪሎ ስኳር ላይ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ከሁለት ብር በላይ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፡፡

ምግብ ነክ የሆኑ ምርቶች የዋጋ መጨመር በሌሎች አገልግሎቶች ላይም የዋጋ ለውጥ እንዲከሰት ምክንያት ሆኗል፡፡ ሆቴሎች፣ ኬክ፣ ምግብ ቤቶችና ካፊቴሪያዎችን ካለፈው ሳምንት ጀምሮ አዳዲስ ዋጋ ለጥፈዋል፡፡

ከሻይ ጀምሮ አዲስ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል፡፡ እንደ ቤቱ ደረጃ ከ25 ሳንቲም ጀምሮ የዋጋ ለውጥ ታይቷል፡፡ ሉካንዳ ቤቶችም በአንድ ኪሎ ሥጋ ላይ ከ4 እስከ 8 ብር የሚደርስ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል፡፡

ከምግብ ነክ ዕቃዎች ሌላ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የታየባቸው የኮንስትራክሽን እቃዎች ናቸው፡፡ ከኮንስትራክሽን ዕቃዎች በተለይ ብረት ከፍተኛ ዋጋ ጨምሯል፡፡

አንድ ፍላት አይረን 40ቦ8 የሆነ ብረት ከ320 ብር በላይ ደርሷል፡፡ ይህ ዋጋ ከአንድ ዓመት በፊት በጅንአድ 256 ብር ገደማ እንደነበር ተገል"ል፡፡ ከወራት በፊትም ይህ ዋጋ 280 ብር አካባቢ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል፡፡

በሌሎች የብረት አይነቶችም እንደየ መጠንና አይነታቸው ከ20 በመቶ ያላነሰ ጭማሪ ታይቷል፡፡ በብረት ዋጋ መጨመር ብቻ ሣይሆን በተፈለገው መጠን ማግኘት እንዳልተቻለ ያነጋገርናቸው ኮንትራክተሮች ገልፀዋል፡፡

የብረትና የዋጋ ጭማሪ በተመለከተ ከአቃቂ ብረታ ብረት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በአሁኑ ጊዜ የጨመረ ቢሆንም አሁን ባለው የፋብሪካው ምርት ላይ ምንም የዋጋ ጭማሪ ባይደረግም በተወሰኑ የብረት አይነቶች ላይ ግን አምስት በመቶ ጭማሪ መደረጉን ለመረዳት ተችሏል፡፡

ሲሚንቶ ተመልሶ ዋጋው እያደገ መጥቷል፡፡ አዲስ አበባ ላይ ከውጭ የሚገባ አንድ ኩንታል ሲሚንቶ ከ170 እስከ 177 ብር እየተሸጠ ነው፡፡ የሙገር ሲሚንቶ ብዙ ገበያ ላይ ባይገኝም ነጋዴዎች 170 ብር እየሸጡት ነው፡፡ ይህ ዋጋ ከጥቂት ሳምንት በፊት የውጭ ሲሚንቶ የመሸጫ ዋጋ ከ145-150 ብር ነበር፡፡ በነሐሴ 1999 ዓ.ም የማዕከላዊ ስታስቲክስ ኤጄንሲ አውጥቶት በነበረ ሪፖርት የጥራጥሬ ዋጋ 31 በመቶ፣ የዳቦና የተዘጋጁ ምግቦች በ21.9 በመቶ፣ የዘይትና የቅባት እህሎች በ41.5 በመቶ የወተትና የወተት ተዋፅኦ 23.3፣ በመቶ የቅመማ ቅመም ዋጋ 108.3 በመቶ ማደጉን ገልፆ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት ይህ አሃዝ በሚያስደንቅ ፍጥነት እያደገ ነው፡፡ የዘይትና የቅባት እህሎች ዋጋ ካለፈው ዓመት ሐምሌ ወር ጋር ሲነፃፀር ከ45 በመቶ በ14 ብልጫ አሳይቷል፡፡

በመኪና ጎማዎች ዋጋ ላይም ጭማሪ እየታየ ነው፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃ የጎማ ማምረቻ ጥሬ ዕቃ ዋጋ እየተወደደ በመምጣቱ ከውጭ የሚገቡ ጎማዎች ምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ እያስከተለ መሆኑንም ያገኘነው መረጃ ያስረዳል፡፡

ያነጋገርናቸው የጎማ አከፋፋይና ሻጮች እንደገለፁት ካለፉት ሁለት ሣምንታት ወዲህ ከውጭ እየገቡ ያሉ ጎማዎች ዋጋ እየጨመረ ነው፡፡

በተለይ ከኢንዶኔዥያ የሚመጡ የትላልቅ ጎማዎች የዋጋ ከ35 ብር በላይ ዋጋ ጭማሪ አሳይቷል፡፡ የሌሎች አገሮች ጎማዎችም ተመሳሳይ በሆነ መልኩ የዋጋ ለውጥ ታይቶባቸዋል፡፡

የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን ተከትሎ አሁንም ዋጋ ይጨምራሉ የሚል ስጋት ያላቸውም አሉ፡፡ 185ሣ14 መጠን ያላቸው ጎማዎች ቀደም ብሎ ከ590-600 ብር ይሸጡ የነበሩ ሲሆን አሁን ግን ይህ ዋጋ ከ630 ብር በላይ ሆኗል፡፡ ትላልቅ የጭነት ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙባቸው ጎማዎች ከሌሎች ጎማዎች በበለጠ የዋጋ ጭማሪ ተደርጎባቸዋል፡፡

ከማታዶር አዲስ ጎማ ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው ከሆነ ደግሞ፣ ሰሞኑን የዋጋ ጭማሪ አለመደረጉንና ከታህሳስ ሰባት ጀምሮ አዲስ ዋጋ ወጥቶ ተግባራዊ ሆኗል፡፡

አዲስ የወጣው ዋጋም እንደ የጎማ አይነቶቹ የሚለያይ ሲሆን ትልቁ ጭማሪ 10 ብር መሆኑን ያስረዳል፡፡

ለፋብሪካው የዋጋ ጭማሪ ምክንያት የሆነው የጥሬ ዕቃ መወደድና ለዕቃዎቹ ማጓጓዣ ይከፈል የነበረውበማደጉ ነው፡፡ የማታዶርን ጎማ ከሚያከፋፍሉ መደብሮች ያገኘነው መረጃ እንደሚያስረዳው፣ 12ሣ30 መጠን ያላቸው ትላልቅ ጎማዎች በ2352 ብር እየተሸጡ ነው፡፡ 560ሣ3 የሚባሉት ለትናንሽ ተሽከርካሪዎች የሚውሉ ሲሆኑ 287 ብር ይሸጣሉ፡፡

በዳዊት ታዬ
 
< Prev   Next >