| በኤስ ኤ ቢዝነስ ሴንተር ባዛር ተከፈተ |
|
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
ቦሌ አካባቢ በሚገኘው የኤስ ኤ ቢዝነስ ሴንተር አቀናጅነት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ልዩ የገና በዓል ኤግዚቢሽንና ባዛር ተከፍቷል፡፡
ዓርብ ታህሳስ 25 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. የተከፈተው ይህ ባዛር የገና በዓልን አስመልክቶ ነጋዴውንና ሸማቹን ለማገናኘት ¾cu c=J” u›”É u=´’e c?”}` ¨<eØ ÁK< SÅwa‹ እንዲህ ባሉ በዓላት ወቅት ለደንበኞች እውነተኛ ቅናሽ በማድረግ እንዲገለገሉ የሚያስችል አዲስ አሠራር መሆኑም ተገልጿል፡፡ የኤስ ኤ ቢዝነስ ሴንተር ህንፃ ሥራ አስኪያጅ አቶ አህመድ አሊ በመክፈቻ ሥነ - ሥርዓቱ ላይ እንደተናገሩት፣ በህንፃው ውስጥ ተከራይተው የሚሠሩ ነጋዴዎችን ከሸማቹ ጋር በማገናኘት የንግድ እንቅስቃሴያቸውን ለማበረታታት ያለመና እግረ መንገዱንም ሥራ ከጀመረ ስድስት ወራት አካባቢ ያስቆጠረውን ህንፃ ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ሥራ አስኪያጁ አክለው እንደገለፁት የጋራድ ባለቤት በሆኑት አቶ ሣልሃዲን አቡበከርና አቶ አብዱል ሃሚድ አቡበከር የተገነባውና ከጌቱ ኮመርሻል ጐን የሚገኘው የኤስ ኤ ቢዝነስ ሴንተር ህንፃ ባለ 13 ፎቅ የሆነ የገበያ ማዕከል ነው፡፡ ህንፃው ከ82 በላይ የተለያዩ የንግድ ሱቆችና 61 ቢሮዎችን በውስጡ ይዟል፡፡ በሀገራችን ውስጥ ኤግዚቢሽንና ባዛሮችን ከኤግዚቢሽን ማሳያ አዳራሾች ውጭ ማድረግ የተለመደ ባይሆንም ኤስ ኤ ቢዝነስ ሴንተር ከህንፃው ሥር ባዛር በመክፈት ፈር ቀዳጅ ሆኗል፡፡ በባዛሩ ተሣታፊ የሆኑትና የፖፒስ ኰሌክሽን ባለቤት አቶ ደረጀ ነጋሽ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንደገለፁት፣ በሕንፃው ውስጥ ተከራይተው የሚሠሩ ነጋዴዎች የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ሸማቹ በተፈጠረው ቅናሽ ተጠቅሞ የሚፈልገውን ዕቃ እንዲገዛ ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡ አቶ ደረጀ እንዳሉት ከ15 እስከ 2ዐ በመቶ የሚደርስ ቅናሽ ተደርጓል፡፡ ከህንፃው ውጭ ያሉ ነጋዴዎች በማይሣተፉበት በዚህ ባዛር የሙዚቃና የፋሽን ሾው ትርዒቶች ቀርበዋል፡፡ በባዛሩ አልባሳት፣ የስጦታ ዕቃዎች፣ ኮስሞቲክስ፣ የቤት ዕቃዎች፣ የሴትና የወንድ ጌጣጌጦች እና የመሳሰሉት ለገበያ ቀርበዋል፡፡ ባዛሩ እስከ ዛሬ እሑድ ታህሳስ 27 ድረስ ይቆያል፡፡ በደመቀ ከበደ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |