Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow ታኮ ጫማዎች ለወሲብ ህይወት ይረዳሉ
ታኮ ጫማዎች ለወሲብ ህይወት ይረዳሉ Print E-mail
Wednesday, 13 February 2008
ከፍታ ያላቸው ታኮ ጫማዎችን መጫማት የሴቶችን የወሲብ ህይወት እንደሚያሻሽለው ከኢጣሊያ የወጣ ምርምር ማመልከቱን ቢቢሲ አስታወቀ፡፡

ኢጣሊያዊው ዶክተር ማሪያ ስሩቶ እንደሚሉት ከሆነ 2 ኢንች ከፍታ ያለው ታኮ ጫማ ማድረግ የዳሌ አጥንት ጡንቻ የተሻለ ጥንካሬ እንዲኖረው ያደርጋል፡፡

የዳሌ አጥንት ጡንቻ በወሲብ እንቅስቃሴ ወቅት ለእርካታ ይረዳል፡፡ ከ5ዐ ዓመት በታች ዕድሜ ባላቸው 66 ሴቶች የተደረገው ጥናት 2 ኢንች ርዝመት ያለው ታኮ ጫማ የሚጫሙ ታኮ የሌላቸው ጫማ ከሚጫሙት ሴቶች በተሻለ ሁኔታ ቅርፃቸው የተስተካከለ ይሆናል፡፡

ሴቶች የሰውነት ማጠንከሪያ ልምምድ ለማድረግ ችግር አለባቸው፡፡ ስለዚያ በዳሌ አካባቢ ያለውን የሰውነት ክፍል ለማጠንከር ረጅም ታኮ ጫማ ጠቃሚነት አለው እንደዶክተር ማሪያ፡፡

“እንደ ብዙ ሴቶች ከፍተኛ ታኮ ያላቸውን ጫማ እወዳለሁ፡፡ ለጤንነትም ጠቀሜታ እንዳላቸው ማወቅም ጥሩ ነው. . . “ይላሉ ዶክተር ማሪያ፡፡

ሰማያዊ ፅጌረዳ

በጃፓን የውስኪ አምራቶች የሚሰሩ ሳይንቲስቶች ፅጌረዳ መፍጠራቸውን ይፋ አደረጉ፡፡ በአሜሪካና በአውስትራሊያ የተሰሩት ሰማያዊ ፅጌረዳዎች በማዳቀል የተፈጠሩ መሆኑም ተዘግቧል፡፡

የካምፓኒው ቃል አቀባይ አስህቶ ኦሳካ እንደገለፀው ምርቱን ከ2ዐዐ8 ጀምሮ በገበያ ላይ ለማቅረብ እቅድ ተይዟል፡፡ ፅጌረዳውን በዚህ መንገድ ለመስራት 14 ዓመታት ፈጅቶባቸዋል፡፡

ፅጌረዳዎቹን የሚገዙት ከፍተኛ ገቢ ያላቸው እንደሚሆኑም እንጠብቃለን፡፡ ልዩ በዓል ሲኖር የሚሰጥ ስጦታም ቢሆን ደስ ይለናል.. ሲሉ አሱህቶ ኦሳካ ተናግረዋል፡፡

“ባለሙያዎቹ ሰማያዊ ፅጌረዳ መስራት የማይቻል አድርገው ስለቆጠሩት በጥንካሬ ሰርተን እንደሚቻል አሳይተናል . . . “ ይላሉ ኦሳካ፡፡

የድካም መድኃኒት በተለይ ለልብ ህመምተኞች

የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን አባላት ከማንኛውም እንቅስቃሴ በኋላ በሰዎች ላይ የሚታየው የመድከም ስሜት የሚከሰተው በእንቅስቃሴ ወቅት ካልሲየም በጡንቻዎች ውስጥ ስለሚሰርግ ነው ብለዋል፡፡ ለዚህም ብለው የሰሩት መድኃኒት የልብ ድካም ያለባቸውን ሰዎች ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡

በዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች የተቀመመው መድኃኒት በእንቅስቃሴ ወቅት ወደ ጡንቻ የሚሰርገውን ካልሲየም በመዝጋት ሰዎች ለድካም እንዳይጋለጡ ያደርጋል፡፡ መድኃኒቱ በአይጥ መሞከሩን የሚያብራሩት አጥኚዎቹ ውጤቱም የሰመረ ነው ብለዋል፡፡

የካልሲየም ወደ ጡንቻ መስረግ በተለይ የልብ ህመም ላለባቸው ሰዎች ዋነኛው የድካም ምንጭ ነው የሚሉት ተመራማሪዎች የመድኃኒቱ መቀመም በተለይም ህመምተኞቹን ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

ናሽናል አካዳሚ ኦፍ ሳይንቲስትስ በድረ ገፁ ላይ ያሳተመው ጥናት እንደሚለው መድኃኒቱ የሰው ልጆችን የድካም ምልክት ሊያቃልል ይችላል የሚል ተስፋ አሳድሯል፡፡

ከዚህ ቀደም የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት የድካም ምክንያቱ ከባድና ተደጋጋሚ እንቅስቃሴዎችን ማድረግና የላክቲክ አሲድ በጡንቻዎች ውስጥ መጠራቀም ነበር፡፡

ንቅሳት ክትባቶችን ለማስተላለፍ

ከዚህ ቀደም ንቅሳት የሚታወቀው የሰው ልጆች ባህል መገለጫ በመሆን ነበር፡፡  በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታትም ባህል ሆኖ ቆይቷል፡፡

የጀርመን ሳይንቲስቶች ያደረጉት ጥናት እንደሚያመለክተው ደግሞ ንቅሳት ወደር የማይገኝለት የክትባት ማስተላለፊያ ዘዴ ሊሆን እንደሚችልም ነው፡፡

በአይጦች ላይ በተደረገ ጥናት ለበሽታ ተከላካይ ህዋሶች ጥሩ ምላሽ በመስጠት አመርቂ ሆኖ የተገኘው ንቅሳት ያለበት ሥፍራ ነው፡፡

እንደ አጥኚዎቹ ከሆነ ንቅሳት ለሰው ልጆች ክትባቶችንም ሆነ አንዳንድ የካንሰር ዓይነቶችን ጨምሮ የመርፌ ህክምናዎችን ለመስጠት ጠቃሚ መንገድ ሊሆን ይችላል፡፡

አሜሪካ ከስፔስሻትል ጋር በተያያዘ አራት “የቻይና ሰላዮችን” አሰረች

አሜሪካ ሚስጥራዊ የመከላከያ መረጃን ወደ ቻይና አሰራጭተዋል በሚል አራት ቻይናዊያንን ማሰሯን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከታሳሪዎቹ አንዱ የሆነው የ72 ዓመቱ አዛውንት የቀድሞ ቦይንግ ኢንጅነር የተከሰሰው ስለ አሜሪካ ስፔስሻትልና ሌሎች የህዋ ምርምር ኘሮግራሞች ወደ ቻይና መረጃ አስተላልፏል በሚል ነው፡፡

የአሜሪካ የፍትህ ክፍል ቃል አቀባይ “ጉዳዩ የአሜሪካ ብሄራዊ ደህንነት ላይ ትልቅ አደጋ ነው” ብለዋል፡፡

በቻይና የተወለዱት የ72 ዓመቱ ቹንግ በስምንት ጉዳዮች ክስ ይጠብቃቸዋል፡፡ የአሜሪካ የፍትህ ክፍል ቃል አቀባይ እንደተናገሩት ከሆነ አንዳንድ የውጭ መንግሥታት የአሜሪካ የንግድ ማስጥሮችን በማግኘት ለአገራቸው ወታደራዊ አቅም ማሳደጊያ ሊጠቀሙበት ይችላሉ፡፡

ቹንግ የተከሰሱትም የቦይንግን የንግድ ሚስጥር ከስፔስ ሻትል ጋር በማገናኘት፣ ሲ-17 ወታደራዊ ማመላለሻ አውሮኘላን እንዲሁም የዴልታ አይ ቪ ሮኬት ሚስጥሮችን ቻይናን ተጠቃሚ ለማድረግ አስተላልፈዋል በሚል ነው፡፡

በህዋ ኢንዱስትሪው ለ30 ዓመታት ያህል ያገለገሉትና የአሜሪካ ዜግነትን ያገኙ ቹንግ በተለይ በሮክ ዌይ ኢንተርናሽናል የቦይንግ ስፔስ ሻትል ኘሮግራም ውስጥ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራቸው፡፡

የበራሪ ተሳቢ ቅሪተ አካል በቻይና ተገኘ

ከ3ዐ ሴንቲ ሜትር ያነሰ ክንፍ ያላት የትንሽ በራሪ ተሳቢ እንስሳ ቅሪት አካል በቻይና መገኘቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አጥኚዎች እንዳሉት የ12ዐ ሚሊዮን ዓመታት እድሜ ያለው ተሳቢ እንስሳ ቅሪተ አካል የሚያመለክተው እንስሳው የሞተው በህፃንነቱ እንደነበር ነው፡፡

የቻይናና የብራዚል አጥኚዎች እንደተናገሩት ከሚሊዮን ዓመታት በፊት ይኖሩ ከነበሩት የበራሪ ተሳቢ እንስሳት አሁን የተገኘው ቅሪተ አካል ልዩ ተፈጥሮዎች የነበሩትና በመጠኑም በጣም ትንሽ ነው፡፡

“የበራሪ ተሳቢው ቅሪተ አካል እንደሚያመለክተው ከዝርያዎቹ በተለየ መልኩ እግሩ የተቆለመመ መሆኑን ነው፡፡ ይህም እንስሳው አብዛኛውን ጊዜውን በዛፍ ላይ ያሳልፍ እንደነበር ያሳያል” ሲል የናሽናል አካዳሚ ኦፍ ሳይንስ ጆርናል ዘገባ ያስረዳል፡፡

 
< Prev   Next >