Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 28th
Home arrow Sections arrow የተመድ ሰላም አስከባሪ በኢትዮጵያ...
የተመድ ሰላም አስከባሪ በኢትዮጵያ... Print E-mail
Wednesday, 13 February 2008
የተመድ ሰላም አስከባሪ በኢትዮጵያ ምድር እንዲቆይ ፈቃድ አገኘ

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ሰላም አስከባሪ በራሷ ምድር እንዲቆይ መፍቀዷን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ሰላም አስከባሪው በኢትዮጵያ ምድር እንዲቆይ የተፈቀደው ከአስመራ ኤርትራ ያገኝ የነበረውን ነዳጅ እንዲቋረጥ በማድረጓ ነው፡፡

ሰላም አስከባሪው በሰፈረበት የሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ (ኤርትራና ኢትዮጵያ) ለመቆየት ጊዜውን ለስድስት ወራት ያራዘመ ቢሆንም ከአስመራ ያገኝ የነበረውን የነዳጅ ፍጆታ እንዳያገኝ በመከልከሉ ምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ አልታወቀም፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለተመድ ዋና ፀሐፊ ባንኪ ሙን፣ “ሰላም አስከባሪዎቹ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ መቆያ ቦታ ይሰጣቸዋል” በማለት እንዳረጋገጡላቸውና ኢትዮጵያ ውስጥ በሚቆዩበት ጊዜ አስተዳደራዊ ሥራን እንጂ ሌላ እንቅስቃሴ እንደማያደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን በመጥቀስ ሬውተርስ ዘግቧል፡፡

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከውጭ ብድርና ዕርዳታ 7 ቢሊዮን ብር አግኝታለች

ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ከውጭ እርዳታና ብድር ሰባት ቢሊዮን ብር ማግኘቷን የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ አገሪቱ በግማሽ በጀት ዓመቱ የ869 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር የእዳ ቅነሳ ተደርጎላታል፡፡

ከተገኘው የውጭ ሃብት ውስጥ 3 ነጥብ 48 ቢሊዮን ብር ብድር፣ ቀሪው 3 ነጥብ 16 ቢሊዮን ብር ደግሞ እርዳታ ነው፡፡ ከዓለም አቀፍ ተቋማት 5 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር የተገኘ ሲሆን ቀሪው የ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከልማት ተባባሪ መንግስታት የተገኘ ነው፡፡

አዲስ እርዳታ ከሰጡት የልማት ተባባሪ መንግሥታት መካከል ስዊድን፣ አየርላንድ፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጃፓን፣ ቻይና፣ ሕንድና ኔዘርላንድ መሆናቸውን፣ ከዓለም አቀፍ ተቋማት መካከል ዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር፣ የአውሮፓ ኅብረትና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ተጠቃሽ መሆናቸውን፣ የተገኘው የውጭ ሃብት አብዛኛው ለግብርናና ገጠር ልማት፣ ኃይል ማመንጫ፣ ለጤና፣ ለትምህርት፣ ለመንገድ፣ ለውሃና ለሌሎች ክፍለ ኢኮኖሚዎች ፕሮግራሞች ማስፈፀሚያ እንደሚውል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡

(ኢዜአ)

ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ ማር ተመረተ

በኢሊባቡር ዞን ከ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኪሎ ግራም በላይ የማር ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የማር ምርቱ የተገኘው ከ560 ሺህ ያህል ባህላዊ፣ የሽግግርና ዘመናዊ ቀፎዎች መሆኑን፣ የዘንድሮው የማር ምርት ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት /የስድስት ወር/ በአንድ ሚሊዮን ኪሎ ግራም ብልጫ እንዳለውና የምርት እድገቱ የታየው አርሶ አደሮች በዘርፉ በስፋት መሳተፋቸው እንደሆነ፣ ከማር ምርት ጎን ለጎን 118ሺ ኪሎ ግራም ሰም አዘጋጅተው ለገበያ ማቅረባቸውን ገልጿል፡፡

(ዋኢማ)

በአፍሪካ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ኮንፈረስ ላይ ኢትዮጵያዊ ባለሃብት ንግግር ያደርጋሉ

የካቲት 14 ቀን 2000 ዓ.ም ለንደን ላይ በሚካሄደው የ2000 የአፍሪካ ኢንቨስትመንትና ፋይናንስ ኮንፈረንስ ላይ ኢትዮጵያዊ ባለሀብት ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ ንግግር ያደርጋሉ፡፡

በዕለቱ ኮንፈረንሱን በሊቀመንበርነት ከሚመሩትና ከዋና ተናጋሪዎች አንዱ መሆናቸውን አፍሪካ ኮንፈረንስ ኤፍ ዶት የተባለ ድህረ ገጽ ዘገበ፣ ኮንፈረንሱ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገራት ያለው በኢንቨስትመንት እይታና በማክሮ ኢኮኖሚክ ማዕቀፍ የሚዳደስ ሲሆን የአፍሪካ ካፒታል ማርኬት፣ የአፍሪካን የባንክ ዘርፍ፣ መሰረተ ልማት፣ ማዕድን፣ የማምረቻ ፋብሪካዎችና አገልግሎቶች በሚሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይካሄዳል ሲል ዘግቧል፡፡   

(ኢዜአ)

የፌደራል ፀረ ሙስና ኮሚሽን አዲስ አሰራር መዘርጋቱን አስታወቀ

የፌደራል ሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የሙስና ወንጀል ጥቆማዎች አቀባባል፣ አመዘጋገብና ውሳኔ አሰጣጥን ቀልጣፋ፣ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያለበት ለማድረግ የሚያስችል አዲስ አሰራር መዘርጋቱን አስታወቀ፡፡

አዲሱ አሰራር የሙስና ወንጀል መርማሪውና አቃቤ ሕጉ አንድ የምርመራ ሥራ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እየተመካከሩ የሚሰሩበት አዲስ አሰራር በመዘርጋት የምርመራ ሂደቱ ውጤታማ የሚሆንበት መንገድ መፍጠር እንደሚያስችል ገልጿል፡፡

 (ዋልታ)
 
< Prev   Next >