| ዊኒሃውስ የ50ኛው አመታዊ ግራሚ... |
|
|
| Thursday, 14 February 2008 | |
ዊኒሃውስ የ50ኛው አመታዊ ግራሚ ቀዳሚ ተሸላሚአቀንቃኝ አሚ ዊኒሃውስ በ50ኛው አመታዊ ግራሚ ሽልማት በአምስት ዘርፎች ቀዳሚ በመሆን በአመቱ የግራሚ ሽልማት መንቆጥቆጧን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ዊኒሃውስ በቪዛ ችግር ምክንያት በሎስ አንጀለስ በተደረገው ስነስርዓት ተገኝታ ሽልማቶቿን ለመቀበል ባትበቃም ከለንደን ስቱዲዩ በሳተላይት ንግግር አድርጋለች፡፡ እናቷንም በማቀፍ ደስታዋን ስትገልጽ ታይታለች፡፡ የ24 ዓመቷ ዊኒሃውስ በምርጥ አዲስ አርቲስት ዘርፍ የግራሚ ተሸላሚ በመሆን ከ20 ዓመታት ወዲህ የመጀመሪያዋ እንግሊዛዊት ናት፡፡ ለአመቱ ምርጥ ቅጂ በእጩነት ከቀረቡት የቢዮንሴ “ኢሪፕሌሰብል” የፎ ፋይተርስ “ዘ ፕሪቴንደር” የሪሃና “አምብሬላ” እንዲሁም የጀስቲን ቲምበርሌክ “ዋት ጎዝ አራውንድ. . .ካምስ አራውንድ” የአሚ ዊኒሃውስ "ሪሃብ” የመጀመሪያውን ሥፍራ ይዟል፡፡ በምርጥ የሴት የፖፕ ድምጽ ብቃትም ለዕጩነት የቀረቡትን የክርስቲና አጉሊራ “ካንዲማን” የፊስት “1234” የራርጊይ “ቢግ ገርልስ ዶንት ክራይ” እና የኒሊ ፉርታዶ “ሴይ ኢት ራይት”ን በመጣል የዊኒሃውስ “ሪሃብ” በቀዳሚነት ተመርጧል፡፡ የዊኒሃውስ “ባክ ቱ ብላክ” አልበምም የአመቱ ምርጥ የፖፕ ድምጽ አልበም በመባል የአንደኝነቱን ሥፍራ አስመዝግቧል፡፡ በቅጂ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ አርቲስቶችን ብቃት ለማሳደግና ለማበረታታት በየዓመቱ በሚዘጋጀው በዚሁ የግራሚ ሽልማት፣ በምርጥ አልበም ዘርፉ ለስድስተኛ ጊዜ በእጩነት በቀረበው “ባክ ቱ ብላክ” በሚለው አልበሟ የአንደኝነቱን ደረጃ ሳታገኝ ቀርታለች፡፡ ዊኒሃውስ በሎስአንጀለሱ የ50ኛው አመታዊ ግራሚ ሽልማት ልትገኝ ያልቻለችው በለንደን የአሜሪካ ኤምባሲ የቪዛ ጥያቄዋን ውድቅ ስላደረገባት ነበር፡፡ ኤምባሲው ውሳኔውን መልሶ ቢፈትሸውም ከነበረው የጊዜ እጥረት አንፃር ለስነስርዓቱ ልትደርስ ስለማትችል ሳይፈቅድላት ቀርቷል፡፡ ከዕጽ መውሰድ ጋር በተያያዘ ብዙ ችግሮች እንዳሉባት የሚነገረው ዊኒሃውስ ከሁለት ሳምንታት በፊት ጀምሮም በካፒዩ ክሊኒክ ሕክምና መከታተል ጀምራለች፡፡ ለግራሚ ሽልማትም ንግግሯን ካደረገች በኋላ ተመልሳ ለሕክምና ወደ ክሊኒኩ እንደምትሄድ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |