| ሳይንቲስቶች ካንሰርን የሚገታ... |
|
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
ሳይንቲስቶች ካንሰርን የሚገታ መድኃኒት ለመሥራት እየጣሩ ነው በሰውነት ክፍል ውስጥ የካንሰርን ስርጭት ለመግታት ጥረት ቢያደርጉም የእንግሊዝ ሳይንቲስቶች አልተሳካላቸውም ያለው የቢቢሲ ዘገባ የካንሰር ሴሎችን መስፋፋት ለመግታት የሚረዳ ቴስ ከተባለ ኘሮቲን ሜና የተሠኘ ድቃይ ኘሮቲን መገኘቱን አመልክቷል፡፡ የለንደን የጥናት ማዕከል ባሳተመው ጆርናል ስለሞለኪዩል ሴሎች በሰጠው ማብራሪያ የሜና መገኘት የማስታገሻ መድሃኒት ለመስራት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብሏል፡፡ የካንሰር ሴሎች እጅግ ውስብስብና በሚከፋፈሉበት ጊዜም በቶሎ በመላ አካል የመሠራጨት ባህሪይ እንዳላቸው ዶ/ር ሌሰሌይ ወከር ጠቁመዋል፡፡ የሜና ኘሮቲን በአጥንት መገጣጠሚያዎች በብዛት የሚገኝ ሲሆን ይህ ኘሮቲን በቅልጥም መገጣጠሚያዎች የካንሰርን ስርጭት ለመግታት ይረዳል፡፡ ዶ/ሩ አያይዘው እንደገለፁት ሜና ከቴስ እስካልተነጠለ ድረስ የካንሰር ሴሎችን ለመግታት አያግዝም፡፡ በጥናቱ እንደተገለፀው በ2ዐዐ7 ብቻ 20000 ሰዎች በካንሰር ሞተዋል፡፡ ሜና ከቴስ ኘሮቲን ነጥሎ በማውጣት ተስፋ ሠጭ የካንሰር መግቻ መድኃኒት ይኖረናል ብሏል የጥናት ቡድኑ፡፡ |
| < Prev |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |