| “የቢ.ፒ.አር ዓላማ ሰራተኛ መቀነስ... |
|
|
| Sunday, 17 February 2008 | |
![]() አቶ ተፈራ ዋልዋ አቶ ተፈራ ዋልዋ ፌደራል አቅም ግንባታ ሚኒስቴር መሰረታዊ የአሰራር ለውጥ ጥናት (ቢ.ፒ.አር) ሰራተኞችን ከሥራ ማፈናቀልና ማባረር ሳይሆን የሠራተኛውን አቅም እየገነቡ ወደ ተለያዩ የሥራ ስምሪት ማሰማራት መሆኑን የፌደራል አቅም ግንባታ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ተፈራ ዋልዋ የካቲት 7 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፅህፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገለፁ፡፡ ሚኒስትሩ እንደገለፁት በጥናቱ ወቅት የሚገኙ አላግባብ የተወዘፉ አሰራሮች ሲስተካከሉ ብዙ ሰራተኞች ሊቀነሱ እንደሚችሉ፣ ነገር ግን የጥናቱ ዓላማ ከሥራ ለማፈናቀል አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአቅም ግንባታ ኘሮግራም የ2ዐዐዐ ዓ.ም. ዕቅድ የግማሸ ዓመት ሥራ አፈፃፀም፣ በአምስት ኘሮግራሞች ላይ ማለትም በሲቪል ሰርቪስ ማሻሻል ኘሮግራም፣ በፍትህ ማሻሻል ኘሮግራም፣ በኢንፎርሜሸን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ኘሮግራም፣ በምህንድስና አቅም ግንባታ ኘሮግራምና የገጠር ወረዳዎች መልካም አስተዳደር አቅም ግንባታ ኘሮግራም አፈፃፀምና የወደፊት አቅጣጫ ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት አጥጋቢ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡ በእቅድና አፈፃፀም በኩል በፌደራልና በክልል በተመረጡ ቁልፍ የመንግሥት ተቋማት ስር ነቀል የሆነ ለውጥ ማምጣት መቻሉን፣ የለውጥ አስቀጣይ የሆኑ የጥናትና የምርምር ተቋማትን ጠብቆ ማቆየት፣ ለውጥ አራማጅና ለውጥ ተግባሪ ሙያተኞችን ማፍራትና ለትላልቅ ለውጦች አስፈጊ የሚሆኑ የውጭ ተቋማትነና ሙያተኞችን ማግኘት የሚቻልበትን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሲሰራ መቆየቱን አቶ ተፈራ ተናግረዋል፡፡ የሥድስት ወራት ሥራ አፈፃፀምን በተመለከተ ሚኒስትሩ እንደገለፁት፣ ጥናቱ በጣም አስቸጋሪ እንደነበር፣ ነገር ግን ይኸንን አስቸጋሪ የለውጥ ሂደት በማለፍ የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር፣ የግብርናና ገጠር ልማት ሚኒስቴር፣ የማስታወቂያ ሚኒስቴር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወደ ሙከራ ተግባር መግባታቸውንና እስከ ዓመቱ መጨረሻ ሙሉ በሙሉ በትግበራ ላይ እንደሚሰማሩና ሌሎችም ወደ ትግበራ ሙከራ እንደሚገቡ ያላቸውን ተስፋ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡ ክልሎችን በተመለከተ ሚኒስትሩ እንደተናገሩት፣ “ክልሎችን በሁለት ከፍለን እናያቸዋለን፡፡ የተሻለ አቅም ያላቸው፣ ጥናት አድርገው ወደ ሙከራ የገቡና (ኦሮሚያ፣ አማራ፣ ትግራይና ደቡብ”፣ የጥናት ሥራዎቻቸውን በመስራት ላይ ያሉ (ሐረርና ድሬዳዋ”፣ በታዳጊ ክልሎች ያሉ (ቤኒሻንጉል ጉምዝ፣ አፋር፣ ሶማሌና ጋምቤላ) ገና ወደ ሥራ ያልገቡ” በማለት አብራርተዋል፡፡ ኢንፎርሜሽንና ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አቅም ግንባታን በተመለከተ ሚኒስትሩ እንደገለፁት፣ ዘርፉ የሚመራበት ፖሊሲና ስትራቴጂ አዘጋጅተው በማቅረብ መጽደቁን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ማበረታቻ ስርዓት ተዘጋጅቶና በመንግሥት ፀድቆ የትግበራ ዝርዝር በማዘጋቸት ላይ መሆናቸውን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ ከህንድና ከተለያዩ አገሮች ጋር በመሆን በአገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲዎች የሙከራ ትግበራው መቀጠሉን፣ ወደ መላው አፍሪካ ለማሸጋገር ከአፍሪካ ህብረት ጋር ለመሥራት ኘሮጀክቱ በተሳካ ሁኔታ እየተፈፀመ እንደሚገኝ አቶ ተፈራ ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ላሉት 22 ዩኒቨርሲቲዎች በቴክኖሎጂው የተደገፈ ላይብረሪ እንደሚቋቋም፣ በኮምፒውተር የተገናኘ በመሆኑ በየትኛውም ቦታ ሆነው ተማሪዎች መጠቀም የሚችሉ መሆኑንና ከሌሎች አገሮች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሚገናኙበትና የሚጠቀሙበት ኘሮጀክቶች በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተግባራዊ እንደሚሆን ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ በታምሩ ጽጌ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |