Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Sunday
May 18th
Home arrow Sections arrow የተወሰኑ የተመድ ወታደሮች በኤርትራ...
የተወሰኑ የተመድ ወታደሮች በኤርትራ... Print E-mail
Sunday, 17 February 2008
የተወሰኑ የተመድ ወታደሮች በኤርትራ ስንቅና ነዳጅ ተቋርጦባቸዋል

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ ቢፈቅድም የኤርትራ መንግሥት ስንቅና ነዳጅ እንዲቋረጥ በማድረጉ የተወሰኑት በኤርትራ ውስጥ መቆረጣቸውን ቢቢሲ ዘገበ፡፡
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ባስተላለፈው መግለጫ መሠረት ወታደሮቹ ኤርትራን ለቀው መውጣት አልቻሉም፡፡ የኤርትራ መንግሥት በአካባቢው ለተሰማራው የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል የምግብና የነዳጅ አቅርቦት በማቋረጡ፤ ተመድ ወታደሮቹ ኤርትራን ለቀው ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡

በዚህም ኤርትራን ለቀው እንዲወጡ የተፈቀደላቸው ስድስት ተሽከርካሪዎች ብቻ መሆኑን ተመድ ገልጿል፡፡

በተመድ የሠላም ማስከበር ክፍል ተጠሪ ጄን ማሪ ጉሄኖ “ኤርትራ የተመድ ወታደሮች በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ በመቶዎች የሚቆጠሩ የተመድ ወታደሮች የኤርትራን ድንበር ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ መግባት እንዳልቻሉ የገለፁት ተጠሪው፤ “ጉዳዩ በአፋጣኝ መፍትሔ የሚሻ ነው” ብለዋል፡፡

ባለፈው አርብ የአስቸኳይ ጊዜ ስብሰባ ያደረጉት የተመድ የፀጥታ ምክር ቤት አሥራ አምስት አባል ሀገራት ወታደሮቹ የገጠማቸው የእገታ ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኤርትራ አምባሳደር አርአያ ደስታ ኤርትራ ለወታደሮቹ የሀይል ፍጆታ የሚሆን አቅርቦት እንደሌላት ገልፀው፤ “የፀጥታው ምክር ቤት መግለጫ አሳፋሪ ነው” ሲሉ አስታውቀዋል፡፡ “የፀጥታው ምክር ቤት ኤርትራ ተጠቂ ሳለች ተጨማሪ ጥቃት እየሰነዘረ ነው፡፡ ይህም አሳፋሪ ነው” ሲሉ አምባሳደር አርአያ ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት የተመድ የሠላም አስከባሪ ወታደሮች ወደ ኢትዮጵያ ቢገቡ አስፈላጊውን አቅርቦት እንዲሁም ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡

የተመድ ዋና ፀሀፊ ባንክ ኢሙን በበኩላቸው ኤርትራ የሰላም አስከባሪ ኃይል አባላት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጊዜያዊ ሰፈራ እያሰናከለች መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >