| ከመኝታ የሚቀሰቅስ ሮቦት ተሠራ |
|
|
| Sunday, 06 January 2008 | |
|
የጃፓን ሳይንቲስቶች ሰዎችን ከእንቅልፍ ቀስቅሶ ቁርሳቸው መድረሱን የሚጠቁም ሮቦት መሥራታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ሮቦቱ እንደ ሰው ልጅ የለሰለሱ እጆች ያሉት ሲሆን፣ ዳቦ ሳይቆርስ ማቀበል ይችላል፡፡ በእጆቹ በመነካካትም የተኙ ሰዎችን የመቀስቀስ አቅም አለው፡፡ የዋሴዳ ዩኒቨርሲቲ መካኒካል ኢንጂነር የሆኑት ፕሮፌሰር ሺጌኪ ሱንጋኖ እንደተናገሩት በአሁኑ ዘመን ሮቦቶች ጠንካራና ለስላሳ ሊሆኑ ይገባል፡፡ ይህንን የሚያሟሉ ..ቲዋንዲ 1.. የተባሉ ሮቦት ሰርተዋል፡፡ ቲዋንዲ 1 የዕድሜ ባለፀጐች በሚኖሩበት አካባቢ እንዲያገለግል ሆኖ የተዘጋጀ ሲሆን በ2015 ለገበያ እንደሚቀርብ ፕሮፌሰሩና ቡድናቸው ገልፀዋል፡፡ |
| < Prev | Next > |
|---|
| Home |
| Sections |
| Forums |
| Reporter - English Ver. |
| Register |
| Contact Us |