Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Thursday
Aug 07th
Home arrow Sections arrow ብሔራዊ ባንክ ልማት ባንክን 7ዐዐ...
ብሔራዊ ባንክ ልማት ባንክን 7ዐዐ... Print E-mail
Sunday, 17 February 2008
ብሔራዊ ባንክ ልማት ባንክን 7ዐዐ ሚሊዮን ብር ከስረሀል አለው
ልማት ባንክ 32 ሚሊዮን አትርፌለሁ ቢልም ተቀባይ አልሆነም


ብሔራዊ ባንክ ልማት ባንክ 700 ሚሊዮን ብር መክሰሩን ጠቅሶ ለራሱ ለባንኩና ለመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ልማት ባንክ 32 ሚሊዮን ብር አትርፌለሁ በማለት ያቀረበው ሪፖርት ውድቅ ተደረገ፡፡
ብሔራዊ ባንክ ልማት ባንክ መክሰሩን አረጋግጦ ይፋ ያደረገው እ.ኤ.አ የ2ዐዐ7 ሂሳብ ከመረመረ በኋላ ነው፡፡ የብሔራዊ ባንክ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ የደረሰው ኪሳራ ገና ተጣርቶ ስላላቀ ምርመራው ሲጠናቀቅ 1 ቢሊዮን ሊደርስ ይችላል፡፡

ልማት ባንክ 32 ሚሊዮን ብር ማትረፉን በራሱ ባንክ ቦርድና ለመንግሥት የፋይናንስ ድርጅች ኤጀንሲ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ ከስረሀል የተባለውን በመቃወም “አልከሰርኩም አትርፌያለሁ” በማለት ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ግን ለባንኩና ለመንግሥት የፋይናንስ ድርጅት ኤጀንሲ በፃፈው ደብዳቤ ልማት ባንክ አትርፌያለሁ በማለት የገለፀው በደጋፊ ማስረጃ ሊታገዝ የማይችል፣ “ቀልዱን ተወው” ዓይነት እንደሆነ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ተናግረዋል፡፡

ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የብሔራዊ ባንክ ባለሙያዎች ስለኪሳራው መንስዔ ሲያስረዱ ልማት ባንክ ጤናማ ያልሆነ ብድር በመሰጠቱ፣ መጠባበቂያ ካፒታል ያልያዘ መሆኑ፣ ንብረት ሲሸጥ ከተገቢው በላይ በአነስተኛ ግምት መሆኑ፣ በልዩ ፈቃድ እያለ አክሳሪ የሆነ ብድር በመስጠቱ፣ ጤናማ ያልሆኑ ብድሮችን ጤናማ እያለ በማቅረቡ የሚሉትን በአብነት ገልፀዋል፡፡

እንደነዚሁ ባለሙዎች አባባል ልማት ባንክ 7ዐዐ ሚሊዮን ብር ከስሮ እያለ 32 ሚሊዮን ብር አትርፌያለሁ በማለት ለሰራተኞች የደሞዝ እርከን እድገት ሰጥቷል፡፡ አትራፊነቱን አስተማማኝ ለማድረግ በነፍስ ወከፍ ለሰራተኞች ቦነስ አድሏል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባለሙያዎቹ እንደ ትልቅ ችግር የሚገልፁት የልማት ባንክን ብድር በመተማመን ትላልቅ ኘሮጀክቶች ከልማት ባንክ ጋር ስ”ነት አድርገዋል፡፡ ባንኩ ግን በተጨባጭ ገንዘብ የለውም፡፡ ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ችግር ገጥሞታል፡፡

ብሔራዊ ባንክ ለባንኩና ለመንግሥት የፋይናንስ ኤጀንሲ እንደገለፀው ልማት ባንክ ያጋጠመው የ7ዐዐ ሚሊዮን ብር ኪሳራ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ በዚህም ሳቢያ ከብሔራዊ ባንክና ከመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ኤጀንሲ የጋራ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጉዳዩን በመመርመር ላይ ይገኛል፡፡

በጋዜጣው ሪፖርተር
 
< Prev   Next >