Lost Password? No account yet? Register
  • Increase font size
  • Decrease font size
  • Default font size
  • default color
  • red color
  • green color

Reporter - Amharic Version     

Friday
Jul 04th
Home arrow Sections arrow ተጨማሪ የተጭበረበረ ወርቅ ተያዘ
ተጨማሪ የተጭበረበረ ወርቅ ተያዘ Print E-mail
Sunday, 17 February 2008
ፌደራል ፖሊስ በአደራ ያስቀመጠው ወርቅ ብረት ሆኖ ተገኘ

ወደ ኬንያ ሊጫን የነበረ ወርቅ የተጭበረበረ መሆኑ በመረጋገጡ አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡ ተጠርጣሪው ወርቅ በሚል ብሄራዊ ባንክ ሲከፍል የቆየውን ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ልክፈል ማለታቸውን የሪፖርተር ምንጮች አስታወቁ፡፡ ፌደራል ፖሊስ ብሔራዊ ባንክ በአደራ ያስቀመጠው ከ36 ኪሎ በላይ ወርቅ ብረት ሆኖ ተገኘ፡፡
ባለፈው ሳምንት ወርቅ ተብሎ ከታሸገ በኋላ እንደተለመደው ብረት ሆኖ የተገኘው የተጭበረበረ ወርቅ ከብሔራዊ ባንክ ወርቅ እየተባለ ክፍያ ሲፈፀምለት ነበር፡፡

ባንኩ ከስልሳ ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ ፈፅሞበታል የተባለው የተጭበረበረ ወርቅ ብረት መሆኑ ሲረጋገጥ ባለንብረቱ (ኤክስፖርተሩ) በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ገንዘቡን ለመመለስ ፈቃደኛ እንደሆኑ ታውቋል፡፡

ጉዳዩን አስመልክቶ የፌደራል ስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ አሰፋ ተጠይቀው መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡

በተመሳሳይ ዜና ወደ ጅቡቲ በህገወጥ መንገድ ሲሄድ ተያዘ የተባለው ወርቅ በአደራ ከተቀመጠ በኋላ ሲመረመር ወርቅ እንዳልሆነ ታወቀ፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያዘ ከፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር የዋሉ አባል አሉ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንስታወቁት ወደ ጅቡቲ ሲጓዝ ወለንጪቲና መተሃራ መካከል የተያዘው ወርቅ የፌደራል ስነ ምግባር ፀረ ሙስና ኮሚሽን ክስ መስርቶበት ሲከራከርበት የቆየ ነው፡፡

በኮንትሮባንድ ከአገር ሊወጣ ሲል ተደርሶበት በተጠቀሰው ቦታ ተያዘ የተባለው ወርቅ በፌደራል ፖለስ አማካይነት ለብሔራዊ ባንክ በአደራ እንዲቀመጥ የተሰጠ ነበር፡፡

የፌደራል ፖሊስ በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት እንዲሰጥ ተጠይቆ ጉዳዩ በምርመራ ላይ ያለ በመሆኑ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ እንደማይሆን በህዝብ ግንኙነት ክፍል በኩል ገልጿል፡፡

በኮንትሮባንድ ከተያዘና ለባንክ በአደራ እንዲቀመጥ ከተሰጠ በኋላ ወርቁ ሲመረመር የተጭበረበረ መሆኑን የገለፁት ምንጮች የፌደራል ፖሊስ ኤግዚቢተር ወርቁን በወቅቱ ሲያስረክቡ ትክክለኛ ወርቅ ለመሆኑ ማረጋገጫ የተሰጣቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም መጀመሪያ ወርቅ ነው የሚል ማስረጃ የተሰጠውና ብሔራዊ ባንክ በአደራ ያስቀመጠው ከ36 ኪሎ በላይ ወርቅ እንዴትና ማን ሊቀይረው ቻለ? የሚለው ወንጀሉን ውስብስብ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ ወርቁ እንዲመረመር ያደረገው ጉምሩክ እንደሆነም ታውቋል፡፡

ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ የብሔራዊ ባንክ ገዢ የሆኑትን አቶ ተክለወልድ አጥናፉን በስልክ ለማግኘት ሞክረን አልተሳካልንም፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ኃላፊዎች ማብራሪያ ለመስጠት አልፈቀዱም፡፡

ቀደም ሲል ሁለት መቶ ሚሊዮን ብር የሚገመት የተጭበረበረ ወርቅ ወደ ውጪ ለመላክ እሽጉ ሲከፈት ባሌስትራ ሆኖ መገኘቱን፤ በዚህም ከፖሊስ፣ ከብሔራዊ ባንክ ከደህንነት፣ የተጭበረበረ ወርቅ አቅርበዋል በሚል የተጠረጠሩና ከተጠርጣሪዎች ጋር በመተባበር ንብረት አሸሽዋል በሚል በቁጥጥር ሥር የዋሉ መኖራቸውን፣ ወንጀሉም በአገር ላይ የተቀነባበረ ውስብስብ ወንጀል መሆኑን የፌደራል ፖሊስንና አግባብ ያላቸውን ተቋማት ጠቅሰን መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

በአሰግድ ተፈራ
 
< Prev   Next >